TG Telegram Group & Channel
ርጢን ሚዲያ ( Ritin Media ) | United States America (US)
Create: Update:

የክርስቶስ ማዳን እና የቅዱሳን ምልጃ

ሰው መድኅን ክርስቶስ ላይ ያለው መረዳት እምነቱን እና በዓለም ላይ ያለውን አኗኗር ይወስነዋል፡፡ የክርስቶስም ማዳን ዓለም ሳይፈጠር በልበ ሥላሴ የታሰበ እና የተመከረ የዘለዓለማዊ ፍቅር አምላካዊ ሥራ ነው፡፡ ሰው የተፈጠረውም በእግዚአብሔር ምሳሌ በመሆኑ፤ በዚህ አምላካዊ የማዳን ሥራ ላይም በጸጋ በመሳተፍ አምላኩን እየመሰለ ይኖራል፡፡ ልዑል እግዚአብሔር ሰውን ለማዳን እንደሚወድ (እንደሚፈቅድ)፤ በእርሱ አምሳል የተፈጠረውም ሰው እንዲሁ ሌላው እንዲድን ይወዳል (ይጓጓል)፡፡ በቅድስና ከእግዚአብሔር ይሳተፋል፡፡ ያለ ፍቅር ቅድስና የለምና፡፡ በዚያውም ሰው መሆኑን አጽንቶ በጸጋ እግዚአብሔር ይጠብቃል፡፡ አሁን እያሰብን ያለነው ቅዱሳት መጻሕፍት ስለሚናገሩለት ህያው ሰው (ማቴ 8፡ 22)፡፡ አሁን እያሰብን ያለነው ስለ እውነተኞቹ ሰዎች፤ ስለ ቅዱሳን ነው፡፡ ሰው መሆን እግዚእብሔርን መምሰል ነው ያልነው፤ በእርሱ የማዳን ሥራ ውስጥም በጸጋ መሳተፍን የሚያጠቃልል ነው፡፡ የድኅነት ምክንያት መሆን፤ ፍቅርና ትሕትናን በዓለም ላይ ማስፋት፤ ክፋትን መታገል እና ሌሎችም ተሳትፎው ምን እንደሆነ የሚያመለክቱ ናቸው፡፡ እኒህ ሁሉ ሰው ብቻውን የሚያደርጋቸው አይደሉም፤ በእግዚአብሔር ጸጋ እና ረድኤት ያደርጋቸዋል እንጂ፡፡ ሰው መውደድን ይወዳል፤ መፍቀድን ይፈቅዳል፤ እግዚአብሔር ማዳኑን ያደርጋል፡፡

የቅዱሳን ምልጃ በክርስቶስ አካል ውስጥ የሚደረግ የአባላት (የብልቶች) ትክክለኛ ሥራ ነው፡፡ የአካል ክፍሎች በትክክል ለተፈጠሩበት ዓላማ ሲሠሩ ማለታችን ነው፡፡ ብልቶች ሳይነጣጠሉ በሚሠሩት ሥራ አንዱ አካል በትክክል ይኖራል፡፡ እኒህን ጉዳዮች ማስተዋል የክርስቶስን ማዳን እና የቅዱሳንን ምልጃ ግንኙነት ለመረዳት ይጠቅማል፡፡ የክርስቶስ ማዳን እና የቅዱሳን ምልጃ ከሁለት አንዱን እንድንመርጥ የሚያስገድዱን፡ እንደ ሁለት ትይዩ መስመሮች (መንገዶች) አይደሉም፡፡ ከኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ውጪ ያሉ ሰዎች ይህን "የትይዩ መስመር አስተሳሰብ ሞዴል" ጥቂት ለማይባሉ ኦርቶዶክሳውያን ያጋቡ ይመስላል፡፡ በዚህ ምክንያት “ስለ ቅዱሳን ማስተማር ክርስቶስን ማደብዘዝ አይሆንም ወይ?”፤ “ሰው የሚድነው በክርስቶስ ቤዛነት ነው ወይስ በቅዱሳን ምልጃ?” … እና የመሳሰሉት ለሰዎች መልስ የሚሹ ዋና ጥያቄዎች ሆኑ፡፡ ነገር ግን “የአስተሳሰቡን መንገድ” ጥቂት እንመርምረው፡፡ የመድኅን ክርስቶስ ማዳን እና እርሱን የሚመስሉት ቅዱሳን ምልጃ “ወይስ” በሚል በትይዩ እና በአማራጭ የሚታሰብ ጉዳይ ነውን? ቅዱስ ወንጌል ከዚህ የተለየ እሳቤ አለው፡፡ ጌታ ደቀ መዛሙርቱን ሲሰበስብ እያንዳንዱን “ተከተለኝ” እያለ ወደ መንግሥቱ ወንጌል ጠርቷቸዋል (ዮሐ 1፡ 44)(ዮሐ 21፡ 19)(ማር 2፡ 14)(ማር 10፡ 21)፡፡ ለጊዜው በእግር ተከተለኝ ማለቱ ሲሆን፤ ፍጻሜው ደግሞ በግብር (በሥራ) ምሰለኝ ማለቱ ነው፡፡ መንገዱ እርሱ ነው፤ መንገዱንም የሚመራ መርቶም ወደ አባቱም መንግሥት የሚያስገባም እርሱ ነው፡፡ እርሱን የተከተሉ ቅዱሳን ከእርሱ ኋላ ናቸው እንጂ ከእርሱ ትይዩ አይደሉም፡፡ እርሱ በአምላካዊ ሥልጣኑ የሚሠራውን እነርሱ በጸጋ እየሰሩ፤ እርሱን በሥራቸው እየመሰሉት ከኋለው እስከማታልፍ መንግሥቱ ይከተሉታል (ፍጻሜ የሌለው እስከ እንደሆነ ልብ ይሏል)፡፡ እርሱን እየተከተሉት የሚፈጽሙት ምልጃ በመንገዱ (በሃይማኖት) ውስጥ ላሉ ለንስሐ እና ቅድሳቱ ሁሉ መቀበያ ምክንያት ነው፡፡ ከክርስቶስ ማዳን ጋር የሚተባበር ነው፡፡ ጌታ ተከተሉኝ ብሎ ደቀ መዛሙርቱን ካስከተለባት ከአንዲቱ መንገድ በበደል የወጣውን በምልጃ ምክንያት ወደ ራሱ ማዳን ይመልሰዋል፡፡ ለዚህም በቸርነቱ ብዛት ቃልኪዳንን ወደ እርሱ ለቀረቡት (ለቅዱሳን) ቃል ኪዳንን ይሰጣል፡፡ በበደል የራቀው በቅዱሳን ምልጃ ሲመለስ፤ ዐመጸኛው ዲያብሎስ ያፍራል፤ በቅዱሳን ዘንድ ደስታ ይሆናል፤ እግዚአብሔር ይህን ሁሉ ስለፈቀደ (በቸርነቱ) ስላደረገ ይመሰገናል፤ በዚህም ሕይወት ይበዛል፤ ሞት ይሰደዳል (ይጠፋል)፡፡

>>Click here to continue<<

ርጢን ሚዲያ ( Ritin Media )

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)