TG Telegram Group & Channel
❤️ የአማኑኤል ልጆች ❤️ | United States America (US)
Create: Update:

እንኳን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጥንተ ስቅለት መታሰብያ ዓመታዊ በአዓል አደረሳችሁ።
••
ፍቅር ምን እንዳደረገው ተመልከቱ ፤ በአርያም ካለው ከእሳት አዳራሹ ስቦ በቤተልሔም ዋሻ በከብቶች በግርግም አስተኛው። ብርሃንን እንደ ልብስ የሚጎናጸፈው እርሱን በበለሳን ቅጠል እንዲጠቀለል አደረገው። ዘመን የማይቆጠርለትን አምላክ ጽንስ ፣ ሕፃን ፣ ልጅ ፣ ጎልማሳ አደረገው።
••
ፍቅር ... በአባቱ የሚወደደውን አንድያ ልጅ በአይሁድ ዘንድ የተጠላ አደረገው። በመላእክት የሚመሰገነውን ጌታ በፈሪሳውያን መሪር አንደበት እንዲሰደብ አደረገው። ፈታሒውን ዳኛ እጆቹን ታስሮ የሰውን ፍርድ ፍለጋ እንዲንከራተት አደረገው። ፍቅር በኩሩቤል ጀርባ ለሚቀመጠው አምላክ የመስቀል ዙፋን አበጀለት። የመቃብር አልጋም አዘጋጀለት።
••
ፍቅር የእግዚአብሔርን ልጅ ሐፍረትን ንቆ በፊቱ ስላለው የምእመናን ደስታ እርቃኑን እንዲሰቀል አደረገው! መድኃኒት በምትሆን ሕማሙ ከኃጢአት በሽታ ሁላችንንም ይፈውሰን!
••
👉🏼 መጋቢት 27 ጥንተ ስቅለት
••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://hottg.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM

>>Click here to continue<<

❤️ የአማኑኤል ልጆች ❤️

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)