TG Telegram Group & Channel
👉 ᴘʀᴏᴍɪsᴇ AIRDROP 👑 | United States America (US)
Create: Update:

ሰካራሙ መነኩሴ
በአቶስ ተራራ ላይ በካሬስ የሚኖር አንድ መነኩሴ ነበር።  በየቀኑ ይጠጣ ነበር፣ ከዚያም በመነኮሳትና በመንፈሳዊ ተጓዦች "pilgrims" ላይ ችግር ይፈጥራል....ይኽንን እያደረገ ሰነባበተ...በገዳሙ የሚኖሩ መነኮሳት በሙሉ በሰካራምነቱ ስለሚያውቁት "ሰካራሙ መነኩሴ" በሚል ነበር የሚያውቁት...ከጥቂት ጊዜ በኋላ ይኽ መነኩሴ አረፈ።
በሞተም ጊዜ ከመነኮሳት መካከል የተወሰኑት ወደ አባ ፓይሲየስ ዘአቶናዊው ፈጥነው ሄዱና በደስታ ሆነው የገዳሙ ችግር አሁን ማብቃቱን ነገሩት "ሰካራሙ በመሞቱ"።
አባ ፓይሲየስ ስለ መነኩሴው ሞት አስቀድሞ ያውቅ ነበር፤ የመላእክት ጭፍሮችም የመነኩሴውን ነፍስ ለማግኘት ሲመጡ አይቶ ነበር። እነዚያም መነኮሳትና መንፈሳዊያን ተጓዦቹ ግራ በመጋባት በመሆንና አባ ፓይሲየስ ለመልካሙ ዜናቸው በሰጠው ምላሽ ሲናደዱ፣ ቅዱስ ፓሲዮስ የሚከተለውን ነገራቸው፡-
ይህ መነኩሴ በታናሿ እስያ ነው ከእልቂቱ
"holocaust" በፊት ብዙም ሳይቆይ የተወለደው።  ወላጆቹ ልጃቸውን ብቻውን መተው ስላልፈለጉ አዝመራውን ለመሰብሰብ "harvest" ሲሄዱ ይወስዱት ነበር፤ በዚህም ልጃቸው እንዳያለቅስ እና እንዳይያዙ ወተቱ ላይ ጠንካራ የአልኮል መጠጥ ጨምረው እንቅልፍ እንዲተኛ በተደጋጋሚ ያደርጉት ነበር።  በዚህም ምክንያት ይህ መነኩሴ የአልኮል ሱሰኛ ሆነ...ሐኪሞችም ቤተሰብ እንዳይመሰርት  ስለመከሩት፣ ወደ አቶስ ተራራ "mount Athos" በመምጣት መነኩሴ ሆነ።  ሰካራም መሆኑንም ለአንድ ሽማግሌ ካህን ተናዘዘ።  ሽማግሌው ካህንም በየቀኑ እንዲሰግድ አዘዘው እና ወደ ቅድስተ ቅዱሳን የአምላክ እናት ድንግል ማርያም "theotokos" እንዲጸልይ እናም ቀስ በቀስ መጠጥ እንዲቀንስ እንድትረዳው እንዲጠይቃት እንዲለምናትም ነገሩት...ይህንንም በብዙ ጥረት ማድረጉን ቀጠለ። 
ከአንድ አመት ተከታታይ ተጋድሎ እና ንስሃ በኋላ በየቀኑ የሚጠጣውን 20 መጠጥ ወደ 19 ዝቅ ማድረግ ቻለ። ትግሉ ቀጠለ እና ከዛ ሁሉ መንፈሳዊ ጦርነት ዓመታት በኋላ መነኩሴው በቀን የሚጠጣው ከ2-3 ጊዜ ብቻ ነበር። ለዓመታት ሰዎች እንደ ሰካራም መነኩሴ እና ችግር ፈጣሪ ያውቁታል "ነገር ግን እግዚአብሔር እንደ አንድ ተዋጊ ስሜቱን ለማሸነፍ በታላቅ ቅንዓት ሲታገል ተመለከተ።" በዚህም በከበሩ መላእክት ነፍሱ ታጅባ ሄደች" አላቸው።
ይህንን የሰሙት መነኮሳቱ እና መንፈሳዊያን ተጓዦቹም ምን ያህል በሰው ድካም ሲፈርዱ እንደነበር አውቀው ተጸጸቱ...ለዚህም ነው ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስ "ኃጢአት ሲሠራ ባየኸው ወንድም ላይ አትፍረድ አንተ ግልጽ የወጣ ኃጢአቱን እንጅ በስውር ለካህን የሚነግረውን ንስሐ አታውቅምና ስለዚህ የራስህን ድካም ተመልከት።" ያለው🙂🙏🏾

እና ምን ልላቹ ነው በአንዳች ነገር ላለመፍረድ እንሞክር እንኳን ባላየነው ባየነውም ጭምር!!

>>Click here to continue<<

👉 ᴘʀᴏᴍɪsᴇ AIRDROP 👑

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)