የፀጋው ግምጃ ቤት
@mgetem
ከፀጋ ቀንሶ ፤ ልጇ መድሀኒአለም
ከድንግል ማርያም ፤ ያስቀረባት የለም።
ለሚካኤል ምህረት ፤ ለገብርኤል ብሥራት
ሰፍሮ እንደሰጣቸው ፤ አላጎደለባት
የሰማይ ሀብት ሁሉ ፤ ለማርያም ተሰጣት።
አላት ልዩ ግርማ ፤ የሚወደድ ጠባይ
ከኪሩቤል እና ፤ ከሱራፌል በላይ።
የቅዱሳን ሁሉ ፤ የሐዋርያትም
ፀጋ ቢሰበሰብ ፤ ከማርያም አይበልጥም ።
ክብር የምታሰጥ ፤ የፀጋው ግምጃ ቤት
ለሰው ልጆች ሁሉ ፤ አርጓታል ተምሳሌት።
ለደናግል ቢሉ ፤ በአላማ ፅኑነት
ከእርሷ የተሻለ ፤ ማን አለ አብነት ።
ለወላጅም ቢሉ ፤ ከእርሷ ማነው በልጦስ
እናት ቢሉ እናት ፤ ያውም የክርስቶስ ።
ለጠቢባን ቢሉ ፤ እንደ እርሷ አዋቂ
ማን አለ መላእክን ፤ መርማሪ ጠያቂ።
እንደ አባ ጊዮርጊስ ፤ እንደ ቅዱስ ኤፍሬም
የለመናት ዛሬም ፤
ከእርሷ የተጠጋ ፤
ፈልጎ አያጣም ፤ የእግዚአብሔርን ጸጋ።
✍ አቤል ታደለ
https://hottg.com/Mgetem
https://hottg.com/Mgetem
https://hottg.com/Mgetem
ለአስተያየት : @abeltadele
>>Click here to continue<<
