#ቅድስት_እናት
@Mgetem
ይቺ ቅድስት እናት _ ቃልን ወሰነችው
በከብቶቹ ግርግም_ ወልዳ ታቀፈችው
በመጠቅለያም_ጠቀለለችው።
ለደቱንም ዘር_ አልቀደመውም
የዳዊት ሥር ነው_መድኃኒአለም
በመወለዱም ድንግልናዋን_አልለወጠውም
የተዘጋች ደጃፍ_እናታችን ማርያም።
ቃል ከአብ _ ያለ ድካም ወጣ
የአዳም ልደቱ_ ደረሰለት ዕጣ
ከድንግልም ያለ _ሕማም ተወለደ
በእውነተኛው ብርሃን_ከሳሽ ተሰደደ።
ምጥ ሳያገኛት_ተሰማ እልልታ
ሰበአ ሰገል መጡ_ሊሰግዱ ለጌታ
እረኞች _ ዘመሩ ተሞልተው ደስታ።
ለአምላክነቱ አመጡለት _ዕጣን
ለንጉሥነቱ _ አቀረቡ ወርቁን
መድኃኒት ነውና _ ገለጡት ትንቢቱን
እነሆ አየነው_ ምስዋዕት ከርቤውን።
ግርማ ያለሽ_ድንግል የአሮን በትር
እናደንቅሻለን _ የሁላችን ክብር
ገናንነትሽን _ልንዘረዝር
በያሬድ ውብ ዜማ_ በዳዊት መዝሙር
ቆመናል ከደጅሽ_ ልንደረድር።
እንደ መልአኩ ገብርኤል_ ከላይ እንደመጣው
ልናመሰግንሽ _ ማርያም ግድ ነው
የባሕሪያችን መዳን_ካንቺ ተገኘልን
በማሕጸንሽ ፍሬ_ሞት ተቀበረልን።
እንደ ሠርግ _ቤት ጉድፍ የሌለብሽ
መንፈስ ቅዱስ _ ያደረብሽ
የልዑል ኃይልም ማርያም ጸለለበሽ ።
ዘለአለም ነዋሪ_የነገስታት ንጉስ
ከኃጢአት ያዳነን_ ይመስገን ኢየሱስ
የልባችን ሰላም_ፍቅርህ በኛ ይንገስ።
ከአብ የተወለደ _ከአለም በፊት የነበረ
አንዱ ቃል እራሱን ( ባሕሪዩን) ሰወረ
እንደምን ይረቃል_የሰማዩ ምስጢር
የሱ ያደረገን_ ይመስገን እግዚአብሔር።
የኪዳን ጽላት_ያለብሽ
የተሰወረ መና_የተሸከምሽ
የወርቅ መሶብ_ የምንልሽ
ደብተራ ድንኳን _አንቺ ነሽ
የጥበብን ወንጌል_ በክንድሽ የታቀፍሽ
አሳስቢ ድንግል ሆይ_ ለመሃሪው ልጅሽ
እናምናለንና _ ሁሉ እንደሚቻልሽ
https://hottg.com/Mgetem
https://hottg.com/Mgetem
https://hottg.com/Mgetem
>>Click here to continue<<
