ዐረገ በእልልታ
@Mgetem
የተዋሐደውን ሥጋ ፤
የከፈለበትን ዋጋ ፤
አልተወውም በመቃብር ፤
ከፍ አደረገው በክብር ፤
የአዳምም ፀጋ ፤ ከቀድሞ በለጠ
በዘባነ ኪሩብ ፤ ሰው ልጅ ተቀመጠ ።
ዛሬ በደመና ፤ ሰማይ ተቀበለው
ትላንትና ዮሴፍ ፤ እንደ ጠቀለለው ።
ዛሬ በአባቱ ቀኝ ፤ ከበረ ክርስቶስ
ትላንት እንደ ቆመ ፤ በቅጥረ ጲላጦስ።
ዛሬ በመለከት ፤ ዐረገ በእልልታ
ትላንትና ህማም ፤ የዋለበት ጌታ።
ዛሬ ዘመሩለት ፤ መላእክት አጅበው
ትላንትና ጭፍሮች ፤ ያፌዙበት ከበው።
ዛሬም ቢሆን ፥ ወደ ሰማይ ፤ ነገም ቢሆን ትላንትና
እንደ ኢየሱስ ፥ ከፍ አይልም ፤ ዝቅ ያላለ በትህትና ።
https://hottg.com/Mgetem
https://hottg.com/Mgetem
https://hottg.com/Mgetem
✍ አቤል ታደለ
ለአስተያየት : @abeltadele
>>Click here to continue<<
