TG Telegram Group & Channel
🙏አሜን💞 ማስታወሻዬ📝📨💌 | United States America (US)
Create: Update:

ክፍል ፬

        በ #ሄኖክ_በቀለ

    ታላቁ ልጄ እንደምታውቁት የቀኝ እጁ አራት ጣቶች ቆራጣ ናቸው። የእርሱ ታናሽ ደግሞ እጁም እግሩም ላይ ስድስት ስድስት ጣት አለው። ይህ እንዴት ሆነ? ሲቀለድብኝ መሆኑ ነዋ! .....አንድ ቀን ጠዋት የጀመርሁ ሥራ ፍለጋ ስንከራተት ውዬ ሰውነቴ ዝሎ አመሻሽ ላይ ቤት ደረስኩ። ምንም ምንም ሳልል፤ እህልም ሳልቀምስ፤ ልብሴንም ሳላወልቅ መጥረቢያዬን ቆጥ ላይ ሳልሰቅል ተኛሁ። ብዙም አልቆየ ታላቅ ልጄና ነፍሰጡር ሚስቴ በጩኸት ቤቱን ሲያናጉት ብትት ብዬ ተነሣሁ። ሳይ ከልጄ መዳፍ ላይ ደም እንደወራጅ ውኃ ይንዠቀዠቃል። ዘልዬ አፈፍ ሳደርገው አራት ጣቶቹ ተራ በተራ ጠብ፣ ጠብ ብለው እንደጉድፍ መሬት ላይ ወደቁ። ያ መጥረቢያ ከንፈሩ ደም ጠግቦ ተጋድሟል። የሆነው ወዲያው ገባኝ። ታዲያ ምን ዋጋ አለው? ከረፈደ ዕውቀት የቀደመ ጠርጣራነት እንደሚበልጥ ማን አስተምሮኝ  ያኔ? ደንቆሮ፣ የደንቆሮ ዘር አይደለሁ። አንድ ቀን መጥረቢያዬን ማራቅ ብረሳ... ። ዛሬም ድረስ አውራ ጣቱ በመዳፉ ላይ ብቻዋን ፍርፍር ስትል ሳያት እንባዬ ይመጣል። ጠማማ ዕድሌን መግራት ተስኖኝ እንዳጎደልሁት ይሰማኛል!”

    "ይበቃል ተብለሀል።"

     “አይበቃኝም ገና መች ጀመርኩትና?! ኋላ ስንቀዠቀዠ ቤቱ ሄድኳ። ምነው ፈጣሪ ምነው ሳምንህ ጉድ ሠራኸኝ? ስል አለቀስሁ። ስለትህን አጉድዬ አውቃለሁ? የምበላው ባጣ እንኳ አሥራትና መባህን ነክቼ አውቃለሁ? ውለታ አታውቅም? አምላክ አይደለህም ተንደርድረህ ከሰው ልታንስ ነው? ምነው እኔን እንዳሻህ ብታደርገኝ? ምነው ልጆቼን ብትተውልኝ?” አልኩት። ሞኝ፣ የሞኝ ዘር አይደለሁ? ...የሰማኝ መሰለኝ። “አይዞህ ያለኝ መሰለኝ። “ይቅርታህን! የዛሬን ብቻ እለፈኝ ትቼሃለሁ” ያለኝ መሰለኝ። “ታርቀናል” ብዬ እንባዬን ጠርጌ ተነሣሁ። ቤት ስደርስ ያቺ ወረግቡ ሚስቴ ስታምጥ ደረስኩ። ቀበቶዬን አላልቼ የምትሰጥም አንተ፤ የምትነሣም አንተ ተመስገን!” አልሁት። ክፋቱን ረሳሁለት። ሚስቴ ምጥዋ ሳይጠና ተገላገለች። ቆንጅዬ ወንድ ልጅ በጨርቅ ጠቅልለው አሳቀፉኝ። ሳይደግስ አይጣላም!” ይሉ የለ የእኛ ሀገር ሰዎች? ...ደጋጎቹ። “መከራዬን አይተሃልና ኀዘኔን በሳቅ፣ ለቅሶዬን በደስታ ቀይረሃልና” ስል ስሙን ካሣ አልኩት። የካሠኝ መስሎኝ! አይ ደንቆሮ፣ የደንቆሮ ዘር ...ቶሎ አይነቃም እኮ።

     ያዋለደችው ሴት በደስታ የምሆነውን ሲያሳጣኝ ፊቷን ጨምታ ስታየኝ ጠረጠርኩና ጨርቁን ገለጥሁት። በእጆቹ በእግሮቹም ላይ ስድስት ስድስት ጣቶች አሉ። ስድስተኛ ሆነው የበቀሉት እንደሌሎቹ ጠንካራ ስላልሆኑ ወዲያና ወዲህ ተንከርፍፈዋል። ደነገጥሁ። ከማዘን ማበድ ቀረበኝ። ጣቱ ስድስት መሆኑ አይደለም፤ ነገረ-ሥራው ገርሞኝ እንጂ። የታላቁን አራት ጣት ነሳኸኝ ብዬ “ምነው?” ስላልኩት ካሣ ላይ መመለሱ ነው? ይሄ ቀልድ እንጂ ሌላ ምን ይሆናል? ድርቅ በጎርፍ ይካሣል? ሥርጉዳት በእባጭ ይሣሳል? ኧረ እንዲህም አድርጎ ቀልድ የትም የለ!

     ሽማግሌው የግራ ጆሯቸውን፤ ከፊቶች አንዱን እያከኩ ተነሡ።

     “እንግዲህ ሰማንህ 'ዕድሉ'። ለሰሚ የቸገረ ነገር ነውና የሸንጎውን ሐሳብ አድምጠን ፍርዱን ለዋናው ዳኛ እንሰጣለን። 
ወደ ሸንጎው ዞረው  ፈጣሪና መጥረቢያ አጥፍተዋል። ፍርድ ይገባቸዋል? የምትል እጅህን አውጣ ተብለሃል!”

           ይቀጥላል.........
    @Mahder_Kasahun🦋

>>Click here to continue<<

🙏አሜን💞 ማስታወሻዬ📝📨💌

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)