TG Telegram Group & Channel
🙏አሜን💞 ማስታወሻዬ📝📨💌 | United States America (US)
Create: Update:

📚ከብዕረኛው.....

            ጠበኛ እውነቶች
                      ~ በሜሪ ፈለቀ

✏️ ሰዎች ሊያወድሱህ ከፈለጉ ከፈጣሪ ታናሽ፥ ሊዘልፉህ ከፈለጉ ደግሞ ሳጥናኤል የሚቀናበት ክፉ ያደርጉሀል፤ ከሰማሃቸው ራስህን የመሆን እድል አይሠጡህም፥ ሁሉም በፈለጉት መንገድ ሊቀርፁህ መጥረቢያ ይስላሉ። ልብህን ከከፈትክላቸው የየድርሻቸውን ጠርበውህ ቅርፅ አልባ ያደርጉሀል………
✏️ ስህተት በስህተት ቢባዛ ቢደመርም ውጤቱ የትየለሌ ጥፋት ነው………
✏️ ሁሉም በልቡ ለማንም የማያሳየው ቆሻሻ ይኖረዋል፥ ጥላቻ ክፋት ግልፍተኝነት ራስን መውደድ… አንዱ ይኖርበታል፤ ልዩነቱ ብዙዎቻችን ያ ባህሪያችን በአስገዳጅ ሁኔታ ፈንቅሎ ካልተገለጠ በቀር ንፁህ ቅን እና ፍፁም እንደሆንን እናስመስላለን………
✏️ ሲገባኝ ሁሉም ሰው የሆነች "የለውጥ ኩርባ" አለችው፥ አስተሳሰቡ ስሜቱ ወይ ድርጊቱ የሚቀየርባት፥ ወደ አዲስ ምዕራፍ የሚታጠፍባት፥ ከወደቀበት መቀመቅ የሚስፈነጠርባት ወይም ለዛለው ጉልበቱ አቅም የሚያገኝበት………
✏️ ለህይወት መጨረሻ ብሎ ነገር የለም፥ የአንዱ ቀን መጨረሻ የሌላው ቀን መጀመሪያ ነውና፤ የሰኞ ማለቅ የማክሰኞ መጀመር እንደሆነው፥ የምድር መጠቅለል ለሰማያዊ ህይወት መጀምር እንደሚሆነው………
✏️ ከእያንዳንዱ ክፋት ጀርባ መሪር የሆነ በደል አለ፥ ጥያቄው በደልን ይቅር ያለ በጎነት አለ? ካለም በደልን ይቅር ለማለት የሚያስችል ትልቅ በጎነት የሚፈጥር 'ፍቅር'ን የሚጠይቅ ይመስለኛል………
✏️ ሁሌም ዛሬ ላይ ቆመህ ሁለት ምርጫ አለህ፥ ትናንት ወይም ነገ፤ ትዝታ ወይም ተስፋ!………
✏️ ብሩህ ነገ የሚባል ቀን የለም፥ ማንም ቢሆን ነገን ኖሮ የሚያውቅ የለም፤ ምክንያቱም ነገን መኖር ስንጀምር ዛሬ ተብሏል………
✏️ እኔና አንተ አንድ ቦታ ላይ በተለያየ አቅጣጫ ፊታችንን አዙረን ብንቆም የእኔ ቀኝ ላንተ ግራ ነው፥ ያንተ ግራ የኔ ቀኝ ነው፤ ቀኝ ይሄ ነው ግራ ይሄ ነው ብዬ ብከራከርህ ቂል ነኝ። እንዳንተ አቋቋም ያንተ እውነት ይሆናል.. ባንተ እውነት ለማመን ያንተን ጫማ መዋስ አለብኝ………

         ...❤️ #ዮቶራዊት ❤️...

            @ItsMeMadi👩‍💻
       @Mahder_Kasahun🦋

>>Click here to continue<<

🙏አሜን💞 ማስታወሻዬ📝📨💌

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)