TG Telegram Group & Channel
MuhammedSirage M/Nur TextPosts | United States America (US)
Create: Update:

እቃዎችን በመግዛት ላይ ተመስርቶ እጣ ለሚወጣላቸው ሰዎች የሚሰጡ “ ሽልማቶች”ን በተመለከተ ….

ዛሬ አንድ ማስታወቂያን ተመለከትኩ

“ እስከ ….. ድረስ ‘ ይህንን ይህንን ‘ ለሚገዙ ግለሰቦች ሽልማት አዘጋጅተናል “ የሚል

ማስታወቂያቸው በርእሱ ዙሪያ የተመለከትከኩትን የዑለማእ ንግግር እንዳስታወስ አደረገኝና ጥቂት ነገርን ማለት ፈለግኩ ….

ሸቀጥን በመግዛት ለባለ እጣዎች ብቻ የሚገኙ ሽልማቶችን በተመለከተ የተለያዩ ገፅታዎች አሉና የተለያዩ ብይኖች ይኖራሉ - ዑለማእ እንደሚሉት

ለዛሬ ሁለቱን ብቻ ላውሳ ፣

1ኛው ገፅታ ፣ ለባለ እጣዎች በታሰበው ሽልማት ምክንያት በሸቀጡ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደርጎ ከሆነ ( ለምሳሌ ሽልማቱ ከመዘጋጀቱ በፊት 100 ይሸጥ የነበረ እቃ ከሽልማቱ ወዲህ 110 ቢገባ ) ወደ እንዲህ አይነቱ ውል መግባት የተከለከለ ይሆናል ።

ምክንያቱም ተጨማሪ ገንዘብ እየተከፈለ ያለው የሽልማቱ ባለ እጣ ለመሆን ነውና ነገሩ ሎተሪ ብለው ከሚጠሩት ቁማር የተለየ እንዳልሆነ ዑለማእ ይገልፃሉ

2ኛው ገፅታ ባለ እጣ ለሚሏቸው የተዘጋጀን ሽልማት በማሰብ ብቻ የማይፈልጉትን እቃ መግዛት ሲሆን እንዲህ አይነቱ ቅርፅም እንደማይፈቀድ ዑለማእ ያስተምራሉ ።

ለምሳሌ “ የታሸጉ የልጆች ምግቦችን ለሚገዙ እስከ ጥቅምት የሚዘልቅ ሽልማት አለ - እጣው ለሚወጣላቸው “ ቢባል ፣ እነዚህን ሸቀጦች የመግዛት ልምድና ፍላጎት የሌላቸው ላጤዎች ሸቀጦቹን መግዛትና በሽልማቱ መጠቀም አይፈቀድላቸው - የቁማር ገፅታ አለበትና ።

ምክንያቱም ፣

እኒህ ግለሰቦች ገንዘቡን እየከፈሉ ያሉት ይኖራል የተባለውን ሽልማት በማሰብ እንጂ ለሸቀጡ እውነተኛ ፍላጎት ኖሯቸው አይደለም - ሸቀጡ ለነዚህ ሰዎች የመጀመሪ ግብ ሳይሆን ትርፍ ፍላጎት ነው - ሸልማቱ የመጀመሪያ ግብ ነው !

ለዚህማ ነው ሽልማት አለ ባይባል ኖሮ እቃውን ባልገዙት ነበር !

ሁለቱም የጠቀስኳቸው ገፅታዎች ከሎተሪ ቁማር እንደማይለዩ ዑለማእ ገልፀዋል ፣

አሏህ ያውቃል

እንጠንቀቅ

https://hottg.com/Muhammedsirage

Forwarded from MuhammedSirage M.NOOR (MuhammedSirage MuhammedNoor)

>>Click here to continue<<

MuhammedSirage M/Nur TextPosts

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)