የተከበራችሁ ወንድሞችና እህቶች ፣
ሃገራችን በቀብር አምልኮና በቢድዓ የተሞላ ነው ። ላኢላሃ ኢለሏህን ያልተገነዘበው ከተገነዘበው በሰፊ ልዩነት ይበልጣል ።
አንዳንድ ሰዎች በኛ ላይ የሚያደርጉት ንግግርና ወሰን ማለፍ ሊያሳስበንና ተመሳሳይ መልስ ውስጥ ሊያስገባን አይገባም ።
የኛ በአንዳንድ ርእሶች መጠመድ የተመቻቸው አሕባሾችና መሰሎቻቸው ስራዎቻቸውን ከመቼውም በደመቀ ሁኔታ በመስራት ላይ ናቸው ።
ታገሱ ፣ ፅኑ ። ተዘምቶብናልና እንዝመት ። ተብሎብናልና እንበል የሚል ሙግት ውስጥ አንግባ ።
ስድብ ን ፣ ፀያፍ ንግግርን እና በእልህ መንቀሳቀስን እንራቅ ።
ከራሳችንም ሆነ ከወንድሞች በመከላከል ብዙ ግዜን ከማባከን ከመጨቃጨቅ እንቆጠብ ።
ህዝባችንን እያስታወስን ብዙሃንን በሚጠቅመው ተውሒድ ላይ እንትጋ ።
“ቅድሚያ የተዉሒድ “ ተግባራዊ የሚደረግ የእውነት መፈክራችን ይሁን ።
አላህ ይምራን
https://hottg.com/Muhammedsirage
>>Click here to continue<<