TG Telegram Group & Channel
MuhammedSirage M/Nur TextPosts | United States America (US)
Create: Update:

በድሩ ሑሴን ሆይ! ምን እያልክ ነው?
~ ~ ~ ~ ~ ~ ~
በቅርቡ አንዱ “የአይነላህ ተቆርቋሪዎች” እያለ በነብዩ ﷺ ሐዲሥ እና በትልቅ የሙስሊሞች ዐቂዳ ላይ ሲሳለቅ አይተናል። ለዚህ አደገኛ ንግግር እርምት እንደመስጠት አንዳንዶች “ጣሊያን ነው የተማረው”፣ “የታሪክ መፅሐፍ ፅፏል”፣ “አንባቢ ነው”፣ “የሸይኽ ልጅ ነው” የሚሉ አስቂኝ መከላከያዎችን ሲያቀርቡለት ነበር። በጎን ትክክለኛውን ዐቂዳ የሚያስተምሩ ሰዎች ላይ በዚህ መልኩ የማሸማቀቅ ስራ ይሰራሉ። በዚህም ከቡድናዊ ሽኩቻ ውጭ የሆኑ በመምሰል የዋሃንን ይሸውዳሉ። በሌላ በኩል ደግሞ ከስር ተያይዞ እንደምታዩት አሕባሾች የአላህን ከዐርሹ በላይ መሆን ለማስተባበል በሚሰብኩበት መልኩ ይሰብካሉ። ይሄ ሰውዬ ከዚህ በፊት “መውሊድ አይለያየንም” ሲል እንደነበር ይታወሳል። ያኔም ከ0ቂዳቸው ይልቅ ለግለሰቦች ይበልጥ የሚሟገቱ ሰዎች ሲከራከሩለት ነበር። ዛሬም ተመሳሳይ ጫጫታ እንደሚኖር እገምታለሁ። ቢሆንስ? መቼም “ህልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም።” ልክ እንዲሁ የነሱን ጫጫታ ፈርተን ከ0ቂዳችን ለመከላከል የምናፍርበት ምክንያት ሊኖር አይችልም። ይህንን ቪዲዮ ዉስጥ ላይ እንደምታዩት አሕባሾች እያራገቡት ነው። በድሩ ሑሴን የአላህን ከዐርሹ በላይ መሆን ከአሕባሾች በተለየ የሚያፀድቅ ከሆነ አሻሚነት የሌለው፣ የሌሎች መጠቀሚያ ያልሆነ ግልፅ ምላሽ ሊሰጥ ይገባዋል። ያለበለዚያ "በቦታም፣ በጊዜም የተገደበ አይደለም ማለት ነው የፈለገው" የሚለው በቂ ማመሀኛ አይደለም። ምክንያቱም አሕባሾችም እንዲህ እያሉ ነውና ከዐርሹ በላይ መሆኑን የሚያስተባብሉት። እየተጠቀመበትም በገሃድ እያየን ነው።
በነገራችን ላይ “አላህ ከቦታም፣ ከጊዜም ወሰን ውጭ ነው” በሚል ሸዋጅ ቃል ጀርባ እያደፈጡ ከዐርሹ በላይ መሆኑን ማስተባበል የጥንቶቹ ጀህሚያዎች አካሄድ ነው። ጀሪር ብኑ ዐብዲል ሐሚድ (188 ሂ.) እንዲህ ብለዋል፡-
كَلَامُ الْجَهْمِيَّةِ أَوَّلُهُ عَسَلٌ وَآخِرُهُ سُمٌّ وَإِنَّمَا يُحَاوِلُونَ أَنْ يَقُولُوا لَيْسَ فِي السَّمَاءِ إِلَهٌ
“የጀህሚያ ንግግር መጀመሪያው ማር ነው። መጨረሻው ግን መርዝ ነው። የሚጥሩት በሰማይ አምላክ የለም ለማለት ነው።” [ደርእ፡ 6/265] [አልዑሉው፡ ቁ. 111] [አልጁዩሽ፡ 2/220]
“መጀመሪያው ማር ነው” ያሉበት ምክንያት ልክ ዛሬ አሕባሾች እንደሚያደርጉት በተውሒድና አላህን በማጥራት ስም ያቀርቡት ስለነበሩ ነው።
ለማንኛውም “አላህ ከዐርሹ በላይ ነው” የሚለው ዐቂዳ የቀደምት ታላላቅ ዑለማዎች ኢጅማዕ ያለበት እምነት ነው። ለናሙና ያክል የጥቂቶቹን ንግግር እንደሚከተለው አቀርባለሁ፦
1. ኢብኑል ሙባረክ (181 ሂ.) እንዲህ ብለዋል፡-
فَإِنَّ أَهْلَ الْإِثْبَاتِ مِنْ أَهْلِ السُّنَّةِ يُجْمِعُونَ ... وَأَنَّ اللَّهَ عَلَى عَرْشِهِ بَائِنٌ مِنْ خَلْقِهِ
“የአላህን መገለጫዎች የሚያፀድቁት የሱና ሰዎች … አላህ ከፍጡሩ ተለይቶ ከዐርሹ በላይ እንደሆነ ኢጅማዕ አድርገዋል።” [አልኢባና፣ ኢብኑ በጧህ፡ ቁ. 694]
2. ሰዒድ ብኑ ዓሚር አዱበዒ (208 ሂ.) እንዲህ ብለዋል፡-
الْجَهْمِيَّةُ أَشَرُّ قَوْلًا مِنَ الْيَهُودِ وَالنَّصَارَى، قَدِ اجْتَمَعَتِ الْيَهُودُ وَالنَّصَارَى، وَأَهْلُ الْأَدْيَانِ أَنَّ اللَّهَ تَبَارَكَ وَتَعَالَى عَلَى الْعَرْشِ، وَقَالُوا هُمْ: لَيْسَ عَلَى الْعَرْشِ شَيْءٌ
“ጀህሚያዎች ከአይሁድና ከክርስቲያን ንግግራቸው የከፋ ነው። አይሁድ፣ ክርስቲያንና የሌሎችም ሃይማኖት ተከታዮች አላህ - ተባረከ ወተዓላ - ከዐርሹ በላይ እንደሆነ ከሙስሊሞች ጋር ተስማምተዋል። ጀህሚያዎች ግን ‘ከዐርሽ ላይ ምንም የለም’ አሉ።” [ኸልቁ አፍዓሊል ዒባድ፡ 31]
3. ሐማድ ብኑ ሀናድ አልቡሸንጂይ (230 ሂ.) እንዲህ ብለዋል፡-
“ይሄ የተለያዩ ሃገራት ነዋሪዎችን ያገኘንበት፣ መዝሀቦቻቸውም በሱ ላይ ያመላከቱት፣ የዑለማዎች ጎዳና ግልፅ የሆነበት፣ የሱናና የባለቤቶቿ መታወቂያ የሆነው አላህ ከፍጡሩ ተለይቶ ከሰባቱ ሰማይ በላይ ከዐርሹ ላይ እንደሆነ ነው። እውቀቱ፣ ስልጣኑና ችሎታው ግን ከሁሉም ቦታ ነው።” [አልዑሉው፡ 527] [ጁዩሽ፡ 2/242]
4. ዐሊይ ብኑል መዲኒይ (234 ሂ.) የአህሉ ሱና ወልጀማዐ አቋም ምን እንደሆነ ሲጠየቁ እንዲህ ሲሉ መልሰዋል፡-
أَهْلُ الْجَمَاعَةِ يُؤْمِنُونَ ... وَأَنَّ اللَّهَ فَوْقَ السَّمَاوَاتِ عَلَى الْعَرْشِ اسْتَوَى
“የጀማዐ ሰዎች ... አላህ ከሰማያቱ በላይ በዐርሹ ላይ እንደሆነ ያምናሉ።” [መጅሙዑል ፈታዋ፡ 5/49] [አልዑሉው፡ ቁ. 473]
5. ኢስሓቅ ብኑ ራሀወይህ (238 ሂ.) እንዲህ ብለዋል፡-
إِجْمَاعُ أَهْلِ الْعِلْمِ أَنَّهُ فَوْقَ الْعَرْشِ اسْتَوَى وَيَعْلَمُ كُلَّ شَيْءٍ فِي أَسْفَلِ الْأَرْضِ السَّابِعَةِ
“እርሱ ከዐርሹ በላይ ከፍ እንዳለና ከሰባተኛው ምድር ጀምሮ... ሁሉን ነገር እንደሚያውቅ የዑለማዎች ስምምነት አለ።” [ደርእ፡ 2/35] [አልዑሉው፡ ቁ. 487]
6. ቁተይባ ብኑ ሰዒድ (240 ሂ.) እንዲህ ብለዋል፡-
هَذَا قَوْلُ الْأَئِمَّةِ فِي الْإِسْلَامِ وَالسُّنَّةِ وَالْجَمَاعَةِ نَعْرِفُ رَبَّنَا سُبْحَانَهُ بِأَنَّهُ فِي السَّمَاءِ السَّابِعَةِ عَلَى عَرْشِهِ كَمَا قَالَ تَعَالَى: {ٱلرَّحۡمَٰنُ عَلَى ٱلۡعَرۡشِ ٱسۡتَوَىٰ}
“ይሄ በኢስላም የሱናና የጀማዐ ኢማሞች አቋም ነው። ጌታችንን ጥራት ይገባውና {አረሕማን በዐርሹ ላይ ከፍ አለ} እንዳለው ከሰባተኛው ሰማይ በላይ ዐርሹ ላይ እንደሆነ እናውቃለን።” [ሺዓሩ አስሓቢል ሐዲሥ፣ አቢ አሕመድ አልሓኪም፡ 34]
7. ኢማሙል ሙዘኒ (264 ሂ) የአህለ ሱናን አቋም ሲዘረዝሩ ቁጥር አንድ ያስቀመጡት የአላህን ከዐርሹ በላይ መሆን ነው። ከዚያም ሌሎችም መሰረታዊ ነጥቦችን ከዘረዘሩ በኋላ እንዲህ ብለዋል፦
هَذِه مقالات وأفعال اجْتمع عَلَيْهَا الماضون الْأَولونَ من أَئِمَّة الْهدى
“እነዚህ የመጀመሪያዎቹ ቀደምት የቅኑ ጎዳና ኢማሞች የተስማሙባቸው ንግግሮችና ተግባራት ናቸው።” [ሸርሑ ሱና፣ ሙዘኒ፡ 75፣ 89]
8. አቡ ዙርዐ አራዚይ (264 ሂ.) እና ሓቲም አራዚ (277 ሂ.) የአህሉ ሱናን ዐቂዳ ሲተነትኑ እንዲህ ብለዋል፡-
أَدْرَكْنَا الْعُلَمَاءَ فِي جَمِيعِ الْأَمْصَارِ حِجَازًا وَعِرَاقًا وَشَامًا وَيَمَنًا فَكَانَ مِنْ مَذْهَبِهِمُ: … وَأَنَّ اللَّهَ عَزَّ وَجَلَّ عَلَى عَرْشِهِ بَائِنٌ مِنْ خَلْقِهِ كَمَا وَصَفَ نَفْسَهُ فِي كِتَابِهِ , وَعَلَى لِسَانِ رَسُولِهِ ﷺ بِلَا كَيْفٍ

>>Click here to continue<<

MuhammedSirage M/Nur TextPosts

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)