🔸🔸🔸 #ሸህ_አብደልቃድር_ጄይላኒ🔸🔸🔸
✍ አሚር ሰይድ
የሙሀመድ ዲን አጥሩ እየፈራረሰ፣ መሰረቱ እየተናጋ ነው፡፡የምድርላይ ነዋሪዎች ሆይ፣ ኑ የፈረሰውን እንገንባ፡፡ የወደቀውን እናቅና፡፡ይህ ሊፈፀም የሚችለው በተግባር ስንቀሳቀስ ነው፡፡ ጨረቃ ሆይ፣ፀሐይ ሆይ፣ ቀን ሆይ፣ ኑ ተባብረን ይህን ዲን እንታደግ(ሸህ አብደል ቃድር ጄይላኒ)
🔷 ሸህ አብደልቃድር ጄይላኒ ማን ናቸዉ?የኛ ሀገር በተለይ በገጠሩ ያሉ ወይም ከተማ እየኖሩ ያልነቁ ሰዎች ስለ እሳቸዉ ትክክለኛ መረጃ ሳያቅ እሮብን ቀን እየመረጡ ዛሬ አብደልቃድር ናቸዉ እያሉ በአቅማቸዉ በቡናዉ በቡና ቁርሱ ቤት ባፈራዉ ነገር አብደል ቃድር ድረሱልን አማልዱን የሚሉ ጫት የሚቅሙ ወገኖች አሉ?አብደል ቃድር ግን ማን ናቸዉ??እንደ አሁን ዘመን ሰዎች የሽርካ ሽርክ አሊም ሳይሆኑ የተዉሂድ ጠንካራ አሊም ነበሩ፡፡
🟢 ሽህ አብዱልቃድር ጄይላኒ የተወለዱት እንደ ሂጅሪያ አቆጣጠር በ470 ወይም እ.ኤ. አበ1075 ጂላኒ በተባለች ከተማ ውስጥ ነው፡፡ የዘር ሀረጋቸው በአባት በኩል ከሀሰን ኢብኑ አሊ ኢብን አቡ ጣሊብ በእናት ደግሞ ከሁሴን ኢብን አሊ ኢብኑ አቡ ጧሊብ ጋር ይገናኛሉ፡፡ እናታቸው ሴቶች መውለድ በማይችሉበት የእድሜ ክልል በ60 አመታቸው ነበር የወለዱዋቸው፡፡ወንድም እህት የላቸዉም ብቸኛ ልጅ ነበሩ፡፡
#የመጀመሪያ_ደረጃ_ትምህርታቸውን ጀይላኒ ከተማ ውስጥ ተከታተሉ፡፡የአብደል ቃድር ጀይላኒ እናት ለዲናቸዉ ጠንካራ እንዲሆኑ ፍላጎት ነበራት፡፡ ያላትን ብር ሰጥታ ዲናቸዉን እንዲማሩ በ488 ሂጅሪያ በ18 እድሚያቸው የበለጠ ትምህርት ለማግኘት ወደ ባግዳድ አመሩ፡፡ ወደ ባግዳድ ማምራታቸው በወቅቱ በሁሉም መስኮች ባግዳድ ውስጥ የነበረውን ማእበል ተከትሎ በእርሳቸው ህይወት ውስጥ ከፍተኛ ለውጥ አስከተለ፡፡
🟢 የመጀመሪያ የዲን ትምህርታቸውን በኢራቅ ባግዳድ ካጠናቀቁ በኋላ ወደ ትውልድ ሀገራቸው ሄደው ከእናታቸው ጋር እያሉ በአካባቢያቸው እየተንቀሳቀሱ ሳሉ በአንድ በሬ ኋላ ኋላ ሲሄዱ በሬው ዞረና በሰውኛ ቋንቋ አንተ ለዚህ አልተፈጠርክም እዚህም እንድትሰራ አልመክርህም ብሎ ሲላቸው.... በፍጥነት ወደቤታቸው ሄደው እናታቸውን ፈቃድ ጠይቀው ለሁለተኛ ጊዜ የዲን ትምህርታቸውን ለመማር ወደ ባግዳድ ተመለሱ
እናታቸውም በእርጅና ጊዜያቸው ማንም ወላጅ የልጁን የሞራል እና የገንዘብ ድጋፍን በሚፈልግበት ወቅት አንድ ልጃቸውን ያለምንም ማቅማማት ፈቀዱላቸው፡፡
አብዱልቃድር ጄይላኒ #ቁድስ(እየሩስአሌምን) የከፈተዉ ጀግናዉ #ሰልሀዲን_አልአዩብ ዘመን የነበሩ አሊም ናቸዉ፡፡ ሰልሀዲን አልአዩብ ጋር ጦር እንዲዘምቱ በደአዋ ያግዙት ነበር፡፡
አብደል ቀድር ጂላኔ የኢስላም መደፈሩ ሁሌ ይቆጫቸዋል፡፡ፍጡራን በአጠቃላይ ኢስላምን ለመርዳት ቢሰማሩ ይመኛሉ፡፡በአንድ ንግግራቸው እንዲህ ብለው ነበር፡፡
የሙሀመድ ዲን አጥሩ እየፈራረሰ፣ መሰረቱ እየተናጋ ነው፡፡የምድር ላይ ነዋሪዎች ሆይ፣ ኑ የፈረሰውን እንገንባ፡፡ የወደቀውን እናቅና፡፡ይህ ሊፈፀም የሚችለው በተግባር ስንቀሳቀስ ነው፡፡ ጨረቃ ሆይ፣ፀሐይ ሆይ፣ ቀን ሆይ፣ ኑ ተባብረን ይህን ዲን እንታደግ ይሉ ነበር
🔺🔻 በሰልሀዲን አልአዩብ ዘመን የነበሩ ሙስሊሞች በፊርቃ ሆድና ጀርባ ነበሩ አብደል ቃድር ጄይላን በቁርአንና በሀዲስ እየታገዙ የሚያጨቃጭቁ ነገሮችን ፈትዋ እየሰጡ ብዙዎችን አንድ አድርገዋል፡፡
አብዱልቃድር ጄይላኒ 84 ያላነሱ ኪታቦች በእጃቸዉ ፅፈዋል፡፡ትዳር አላሰቡም ነበር ግን ሰዎች የነብዩን ሱናን አትቃረን አግባ ብለዉ በ51 አመታቸዉ አገቡ፡፡ በተለያዩ ጊዜ ካገቧቸዉ አራት ሚስቶቻቸዉ...መዲና/ሳድቃ/ሙእሚናህ/መህቡባህ ከተባሉ ሚስቶቻተዉ
የ27 ወንዶች የ22ሴቶች በአጠቃላይ የ49 ልጆች አባት ናቸዉ፡፡
🟡 በአብዱልቃድር በጀይላኒ እይታ ግለሰቦችና ህብረተሰቡ ኢስላምን መርዳትን ከተው በፍራንክ ከተመኩ፣ ጥቅም አሳዳጅነት ከተጠናወታቸው ስለ ጀነት እና እሳት ቢያወሩም በአላህ አጋርተዋል፡- «እናንተ የፍጡራን ባሮች ናችሁ፡፡ይሉ ነበር
ተማሪዎቻቸውን ደካማ አሊሞችን እንዳይቀርቡ : አስጠንቅቀዋል እንዲህም ይሏቸዉ ነበር፡- አላህን የማያውቁ አሊሞች አያታሏችሁ እውቀታቸው ሁሉ በነርሱ ላይ የተቆለለ እዳ ነው፡፡ቅንጣት አይጠቅማቸውም።የአላህን ሁክም ያውቃሉ፡፡ አላህን ግን አያውቁትም ከእርሱ ይሸሻሉ፡፡ በወንጀልና በእኩይ አድራጎት ይዳፈሩታል፡ (አልፈትሁልረባኒ 43)
ሕብረተሰቡም እንዲህ አይነት አሊሞችን እንዳይሰማ ጥሪ አድርገዋል። (የአላህ ባሮችሆይ፣ እነዚያን በቃላቸው ነፍሳችሁን የሚያስደስቱትን እኩያን አሊሞች አትስሙ፡፡ ከሹማምንት ፊት ተዋርደው ቅንጣት ታክል ይሆናሉ፡፡ አላህ ያዘዘውን አያዟቸውም፤ ከከለከለውም አይከለክሏቸውም ይህን ቢያደርጉም ለማስመሰል ነው፡፡ አላህሆይ፣ እባክህ ምድርህን ከእንዲህ አይነት እኩያን አፅዳ፡፡ ወይም ወደ መቀናት ምራቸው፡፡በልባቸው ሌላን አካል ቋጥረው በምላሳቸው የአላህን ስም ሲያወሱ ውስጤ በንዴት ይቃጠላል፡፡ ብለዉ ያስተምሩ ነበር አልፈትሁልረባኒ 245)
☑️☑️ የሸይህ ዐብዱል ቃድር ጂላኒ
#ወርቃማ_አባባሎች በጥቂቱ
☞አስቀያሚ ጠላትህ ክፉም ግባር ያለው ጎደኛህ ነው
☞ንግግርህ አላህን የማያረካ ከሆነ ዝምታህ ይበልጣል።
☞ ሕይወትህ በቀጥተኛ መንገድ ላይ ካልሆነ ሞትህ ላንተ በላጭ ነው፡፡
☞አላህን ለሚገዛ ሰው አላህ ሌሎች እንዲታዘዙለት ያደርጋል፡፡
☞ቅርቡ ዓለም ከቀጣዩ ዓለም ጋር በፍፁም በአንድ አይቀላቀሉም፡፡
☞ነፍስህን በአእምሮህ ጋልባት ካልሆነ እርሷ ትጋልብሃለች
☞ የሰውነት ፅዳት በነፍስ መፅዳት ካልታገዘ ጥቅም የለውም።
☞ለሰዎች በጎ በጎውን አስብ፣እንዲያ ስታደርግ ራስህንም ሌሎችንም ትጠቅማለህ፡፡
☞በጎ ምግባርና እዝነት ያልታከለበት ተግባር ውጤታማ አይደለም፡፡
☞አማኝ ሰው እድሜው በጨመረ ቁጥር ኢማኑም የሚጨምር ነው፡፡
☞አላህን እንድትዘነጋ የሚያደርግህ ሁሉ ለአንተ ክፉነው።
ብለዋል፡፡
➡️ አብደል ቃድር ጀይላኒ አሊም ናቸዉ ወልይም ባለከራማም ናቸዉ...አንዳንድ ሰዎች ድንበር ረገጥ ጥላቻ ያላቸዉ አሉ ..ጥላቻዉ ስህተት ነዉ ለምን
የነብዩ ﷺቤተሰብ (አህለል በይት) ናቸዉ፡፡ወሰን ያለፈ ዉዴታ እሮብ ቀን መርጦ እስከ ማክበር የደረሰም ስህተት ነዉ ....የኛ ማህበረሰብ የገጠሩ ወይም ትላልቅ ሰዎች አብደል ቃድር እንዲህ ብለዉ...እንዲህ ሂደዉ...እንዲህ አርገዉ እየተባለ ብዙ ወሬ ይወራል ፡፡ ይሄን ማወራት አግባባም አይደለም ለምን የእሳቸዉን ታሪክ እንዲህ አድርገዉ እንዲህ ብለዉ ከራማቸዉ ምናምን ተብሎ የተፃፈዉ የተዘጋጀዉ በሸአዎች ስለሆነ እዉነቱን ዉሸቱን ለመለየት አዳጋች ነዉ፡፡ብቻ አላህን ፈሪ የዲን ጠበቃ ከራማ እንዳላቸዉ ግን እርግጥ ነዉ ...ለምሳሌ ከላይ እንደጠቀስኩት በሬዉ ዙሮ በሰዉኛ ቋንቋ ተናግሯቸዋልና ..
ኑር ሁሴን ማክሰኞ አብደልቃድርን እሮብ ቀን ለይቶ ማክበሩ ስህተት መሆኑን ልናስተምር ይገባል፡፡
አብደል ቃድር ጀይላኒ በ91 አመታቸዉ ነበር ከዚች አለም በሞት የተለዩት....አላህ ይዘንላቸዉ ቀብራቸዉን ኑር ያድርግላቸዉ
◈━━━━━━━━◈━━━━━━━━ ◈
4 another channal👇
hottg.com/Islam_and_Science
💐<<<<<<>>>>>>⭐️<<<<<<>>>>>>💐
hottg.com/IslamisUniverstiy_public_group
hottg.com/IslamisUniverstiy_public_group
>>Click here to continue<<