🔸🔸🔸 #ሸህ_ኑር_ሁሴን(ባሌ)🔸🔸🔸
✍🏼አሚር ሰይድ
ሸህ ኑር ሁሴን የዘር ሀረጋቸዉ ከነብዩ አጎት ልጅ ከአቂል ኢብኑ አቡጧሊብ 12ኛ የዘር ሀረጋቸዉ ይመዘዛል፡፡አረባዊ ዜጋ ቁረይሽ ናቸዉ የተወለዱት በ690 ሂጅራ የዛሬ 746 አመት በፊት ገዳማ የነበሩ አሊም ነበሩ::
🔶 የሼህ ኑር ሁሴን አባት ሸህ ኢብራሂም አብደላ ወደ ማያቁት ህዝብ ሀበሻ መጥተዉ ባሌ ዉስጥ ኢስላምን አስፋፍተዋል፡፡ሸህ ኢብራሂም ማኪዳ የምትባለዉን የባሌ ተወላጅ አግብተዉ ሶስት ልጆች ወለዱ የልጆችም ስም
➊ ሙሀመድ
➋ ሱለይማንና
➌ሁሴን ይባላሉ::
የባሌዉ ሸህ ሁሴን ኢብኑ ኢብራሂም በደንብ የሚታወቁት ሼህ ኑር ሁሴን በሚለዉ አጠራር ነው ትርጉሙ ብርሀማዉ ሁሴን እንደማለት ነው፡፡ይህም ወደ ፊት ሀገሩን በእስልምና ብርሀን ያበረዋል በሚል መልካም ምኞት የወጣላቸዉ ቅጥል ስም ነዉ ይባላል፡፡ የተወለዱት አናጂር በምትባለዉ የገጠር ቀበሌ ነው፡፡
ታዳ ልጃቸዉ ሁሴን የአባታቸዉን የደአዋ ስራ በማስቀጠል በባሌና አርሲ ባሉ ማህበረሰቦችን የኢስላም የተዉሂድ እዉቀትን አሳፋፍተዋል፡፡
እናጂና የሚባል መስጂድ ነበራቸዉ መስጂዱም በወቅቱ በ10ሺ የሚገመት ህዝብ የጀመአ ሶላት ይሰግድበት ነበር፡ ሰዉን ለጀመአ ሶላት የዲን እዉቀት ቀን ማታ ሳይሉ ያስተምሩ ነበር ፡፡ ኑርሁሴን አመትን በሁለት በመክፈል 6 ወር ደረሶቻቸዉን ከቤትና ከቤተሰብ በማራቅ በሸለቆዋማ ቦታ ዉስጥ በመሰብሰብ ሲያስቀሯቸዉ፤ 6 ወር ደሞ ደረሶቻቸዉ ወደየ ትዉልድ ስፈራቸዉ እንዲሄዱና መስጂድ እንዲሰሩና ህብረተሰቡን ወደ ኢስላም እንዲጣሩ ያደርጓቸዉ ነበር፡፡
🔶 #አለመታደል_ሆኖ እሳቸዉ ወደ አኼራ ከሄዱ በኋላ ተግባራቸዉ ተዘንግቶ አላማቸዉ ተረስቶ ስለሳቸዉ ማንነትና ምንነት የሚያሳዉቅ ጠፍቶ የማያዉቋቸዉ ስብስቦች ወዳጆቻቸዉ ተብለው ተፈጠሩ፡፡የኑር ሁሴን ቀን ተብሎ በሳምንት ዉስጥ ይከበር ይዟል፡፡
ኑር ሁሴንን ላይከተሉዋቸዉ ተከታዮች የተባሉት ከሙስሊሙ ህብረተሰብ በአኗኗራቸዉ! በአለባበሳቸዉ! በባህሪያቸዉ ለየት ባለ ሁኔታ እንዲታወቁና ከየአገሪቱ ክፍል እንዲሰበሰቡ ተደረገ፡፡
ዛሬ ላይ መሰብሰቢያ የተደረገዉ ቦታ አናጂና በመባል ይታወቃል፡፡እናጂና ለኑር ሁሴን ባሌ የእውቀትና የደእዋ ስልጠና ማዕከላቸዉ ለስድስት ወራት ደረሶቻቸዉን የሚሰበስቡባትና ለተለያዩ እስላማዊ ስልጠና ሲገለገሉባት የነበረች ልዩ ስፍራ ነበረች፡፡
መስጂዱም በወቅቱ በ10ሺ የሚገመት ህዝብ የጀመአ ሶላት ይሰግድበት ነበር፡፡ ዛሬስ ላይ ምን ያህል ሰው ይሰግድበት ይሆን? ዛሬ ላይ በየአመቱ ወደዚያ ስፍራ የሚሰበሰበው በብዙ ሺህ የሚቆጠር ህዝብ ስለ ሽህ ኑር ሁሴን ማንነት ቢጠየቅ ምናልባት በአፈ ታሪክ የተነገረዉን፤ ስለወዳጅነቱ የሚያንጎራጉርና ከዚያም አልፎ ከተዉሂድ ጋር የሚጋጩ ቃላትን በግጥም ከማዜም የዘለለ አብዛኛውሰው ጨርሶም አያዉቃቸዉም ለማለት ያስደፍራል፡፡ምክንያቱም ወዳጆችነን የሚሉት የዋሆች የሚተገብሩት ከሸህ ኑር ሁሴን ህይወትና ተግባር ጋር የማይገናኝ እጅግም ተቃራኒ ሆኖ እናገኘዋለንና፡፡
የኑር ሁሴን አባት ከአረቦች ቁረይሾች መጥተዉ እስልምናን ሀባሻ ላይ አስፋፍተዋል እኛ ግን እዚሁ ተቀምጠን ኢስላም ላይ ምን ሰራን?? እስኪ አንተ አንቺ እኔም ለኢስላም ምን አበርክተናል??
መስራቱ ማስፋፋቱ ቀርቶብን ኢስላምን በላሰደብን ....
🟢 ሽህ ኑር ሁሴን ባሌ ከተናገረውቸው ጠቃሚ ንግግሮች በከፊል
✏️ ዝናብ ሲዘንብ በንፁህ መሬት እና ንፁህ ባልሆነም መሬት ላይ ነው፡፡በንፁህ መሬት ላይ የወረደ ዝናብ ለሰው ልጅ እንደሚጠቅም ሁሉ ቁርአንና እስላማዊ እውቀት በንፁህ ልቦና እና ንፁህ ባልሆነ ልቦና ውስጥ ከገባ ልዩነቱ የዚያኑ ያክል የተለያየ ነው፡፡ አላህን በሚፈራ ሰው ውስጥ ያለው ቁርአን ለዱኒያም ሆነ ለአኼራ ይጠቅማል፡፡
✏️ #ስለ_ነፍሲያ_አስቸጋሪነት_ሲያብራሩ
✔ነፍሲያ የመሬትና የአለም ስፋት እንጂ የቀብር ጥበት አይታያትም፡፡
✔ነፍሲያ ገንዘብ መሰብሰብ እንጂ እነማን ሰብስበው ጥለው እንደሄዱ አይታያትም፡፡
✔ ነፍሲያ ሰፊ ምኞት እንጂ ሞት በአቋራጭ ሊመጣ እንደሚችል አይታያትም፡፡
✔ ነፍሲያ የሰው ነውር እንጂ የራስዋ ነውር (ገበና) አይታያትም››
✔ የነፍሲያ ሽር (ተንኮል) ከሰባ ሺህ ሸይጧን ተንኮል (ሸር) ይበልጣል› እናም ሌባው ቤት ውስጥ ከሆነ በር መዝጋቱ ትርጉም የለውም፡፡ ሌባው ነፍስያ ስትሆን ቤቱ የሰው ልብ ማለት ነው፡፡ ብለዋል
✏️ #በኸይር_መሽቀዳደምን_ሲገልፁ
☞በአንዱ ቢቀድምህ አንተ በሌላው ቅደመው፡፡
☞በቁርኣን ቢቀድምህ አንተ በዒልም ቅደመው፡፡
☞ በዒልም ቢቀድምህ በስራ ቅደመው።
☞በመልካምሥራ ቢቀድምህ አንተ ለአላህ ታማኝ በመሆን (በኢኽላስ) ቅደመው፡፡
☞በኢኽላስ ቢቀድምህ በትዕግስት ቅደመው፡፡
☞በትዕግስት ቢቀድምህ በውዴታ ቅደመው።
☞በውዴታ ከቀደመህ አንተ በምንም ነገር መቅደም አትችልም፡ አንተ ከእሱ አብልጠህ ካልወደድከው በቀር...ብለዋል፡፡
✏️ አንዳንድ በእውቀት የተካኑ ሰዎችን
#የምላስን_አደገኛነት ሲናገሩ:-ለምላሴ በአፌ ውስጥ አንበሳ አለ እና አስሬ ከያዝኩት እድናለሁ ከለቀቅኩት ግን እበላለሁ በማለት ይናገራሉ፡፡ ከምላስ ወለምታ አላህ ይጠብቀን፡፡
ኑር ሁሴን ተብሎ ማክሰኞ ቀንን ለይቶ ማክበር አግባብ አይደለም ልናስተዉል ይገባል🚫
⚡️⚡️ #አሏህ ይዘንላቸዉ ቀብራቸዉን ኑር ያድርግላቸው... ጀነተል ፊርዶስ ይወፍቃቸዉ
◈━━━━━━━━◈━━━━━━━━ ◈
4 another channal👇
hottg.com/Islam_and_Science
💐<<<<<<>>>>>>⭐️<<<<<<>>>>>>💐
hottg.com/IslamisUniverstiy_public_group
hottg.com/IslamisUniverstiy_public_group
>>Click here to continue<<