TG Telegram Group & Channel
ISLAMIC SCHOOL | United States America (US)
Create: Update:

#ብር_ይብልጦብኛል_ብሎ_አንገቱ_ተሰበረና_ሞተ😔
                   ✍🏼 አሚር ሰይድ

  አል-አዕሻ ኢብኑ ቀይስ ይባላል፡፡ ገጣሚ የሆነ ትልቅ ሽማግሌ ነበር፡፡ ረሱልን ﷺ ፈልጎ ከነጅድ የማማ ይነሳል፡፡ ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ መገናኘትን በመናፈቅ በእሳቸዉ እጅ እስልምናን ለመቀበል ጉዞውን ቀጠለ፡፡ እንዲያውም በጉዞው ላይ ነብዩን እያወደሰ ነበር የሚጓዘዉ

የረሱል ﷺ ፍቅርና ናፍቆት ሜዳውና በርሀውን በቀላሉ እንዲያቋርጥ አድርጎታል፡፡ ጉዞውን ኢስላምን በመሻትና የጣኦት አምልኮን በመጣል ወደ ረሱል ﷺ ጉዞ አድርጓል፡፡ ወደ መዲና የቀረበ ጊዜ የተወሰኑ ሙሽሪኮች አገኙትና ስለ ጉዳዩ ጠየቁት፡፡ እርሱም ከሀገሩ የወጣው ረሱል ﷺ ለመገናኘትና ኢስላምን ለመቀበል እንደሆነ ነገራቸው፡፡ ይህ ገጣሚ እንዳይሰልምና የረሱል ﷺ ዲን እንዳይጠነክር ፈሩ፡፡ ሀሳን ኢብኑ ሳቢት እንኳን በግጥሙ ብቻውን በእነሱ ላይብዙ ድንቅ ነገሮችን ሰርቷል፡፡ ይህ በአረቡ ዓለም ላይ ዕውቅ የሆነ ገጣሚ አዕሻ ኢስላምን ቢቀበል ደግሞ እንዴት ሊሆን ነው?ብለዉ አሰቡና ክፋት ተመካክረዉ ለአዕሻ የክፋት ሀሳብ አቀረቡለት እንዲህም አሉት፡-
..... “አዕሻ ሆይ! ሀይማኖትህና የአባቶችህ ሀይማኖት ላንተ የተሻለ ነው፡፡'' አሉት
..... እሱም “አይደለም! የእሱ ሀይማኖት የተሻለና ቀጥተኛ ነው አላቸው፡፡" እርስ በእርሳቸው ተያዩ፡፡ ወደ ሀይማኖቱ እንዳይገባ እንዴት አድርገው መከላከል እንዳለባቸው ተመካከሩ:: ከዚያም “አቡ አዕሻ ሆይ! እሱ እኮ ዝሙትን ሀራም ያደርጋል'' አሉት፡፡
......“እኔ እኮ ትልቅ ሽማግሌ ነኝ ከሴት ፍላጎት የለኝም'' አላቸው፡፡
......እነሱም "መጠጥንም ይከለከላል" አሉት፡፡
.........”እሷ መጠጥ አዕምሮን የምታበላሽ፣ ወንድን ልጅ የምታዋርድ ናት፡፡ ከመጠጥ ጉዳይ የለኝም አላቸዉ

ኢስላምን ለመቀበል  ቁርጠኛ አቋም መያዙን ባዩ ጊዜ እንዲህ አሉት::፡ ኢስላምን ትተህ ወደ አገርህ ከተመለስከ 100 ግመል እንሰጥሀለን አሉት፡፡ በገንዘቡ ጉዳይ ማሰብ ጀመረ፡፡ ግዙፍ ሀብት ሆኖ አገኘው፡፡ ከአዕምሮው ይልቅ ሸይጧን አሸነፈው… ወደ እነርሱ ዞረና በገንዘብ ከሆነማ ተስማማቻለሁ አላቸው:: ለእሱ 100 ግመሎችን ሰበሰቡለት፡፡ ግመሎቹን ይዞ ወደ መጣበት ተመለሰ፡፡ በከህደቱ ላይ እንዳለ ወደ ህዝቦቹ ገሰገሰ፡፡ ግመሎቹን በደስታና ፈንጠዝያ ከፊት ለፊቱ እየነዳ ሄደ፡፡ ሀገሩ ሊገባ ትንሽ እንደቀረው ከግመሉ ላይ ወደቀ፡፡ አንገቱ ተሰበረና ሞተ፡፡

🎖🎖🎖አንዳንድ ጊዜ ሰውየው እውነታውን ያውቅና ሀቁን ከመከተል ግን ያፈነግጣል፡፡ በዱንያ ጥቅማ ጥቅሞች ይታለላል፡፡ በወንጀሉም ላይ ይቀጥላል....

ዛሬ ላይ ስንት እህቶታችን ለዱንያ ጥቅም ብለዉ ዚና ላይ የወደቁ በሀገር ዉስጥም በሀገር ዉጭም ቤት ይቁጠረዉ....ዛሬ ለገንዘብ ተብሎ ሀራም የሚነግድ ሀራም የሚበላ ሀራም የሚጠጣ ሁነናል ትዉልዱ፡፡ የሚታመን አላህን የሚፈራ ማግኘት ከባድ ሁናል...ብቻ ሞት አማክሮ አይመጣምና ኑራችን አኗኗራችን የምንበላዉ የምንጠጣዉ ከሀራም ነዉ ከሀላል የሚለዉን ብንፈትሽ መልካም ነዉ

አሏህ በሀዲሰል ቁድስ ወደ እሱ የሚመለሱ ባርያዎችን እንዲህ ብሏል፡-
አንተ ዳዉድ ሆይ! ከእኔ ጀርባቸውን የሰጡኝ ባሪያዎቼ እንዴት ሆኜ እንደምጠብቃቸው ቢያውቁ ኖሮ ከወንጀላቸው ወጥተው እኔን በመናፈቅ ይሞቱ ነበር። #ዳዉድ_ሆይ! ይሄ እዝነቴ ወይም ውዴታዬ እኔን ሁሌ ለሚወነጅሉኝ ከሆነ፣ ለእነዛ እኔን ለሚፈሩኝማ እዝነቴና ናፍቆቴ እንዴት ሊሆን እንደሚችል ገምት።" ብሏል

ዱንያ ሞላ ሲሏት የምጎድል የልፋት ሀገር ናትና ...ለዘላለማዊዉ ሀገር ሞት ሳይቀድን ለተዉበት ብንቀድም አትራፊዎች ነን!!!

◈━━━━━━━━◈━━━━━━━━ ◈
4 another channal👇
             hottg.com/Islam_and_Science
💐<<<<<<>>>>>>⭐️<<<<<<>>>>>>💐
hottg.com/IslamisUniverstiy_public_group

>>Click here to continue<<

ISLAMIC SCHOOL

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)