🎖#ሀቢቢ_ናፍቀዉኛል_ከሞትኩ_እንዳታሳድሩኝ🎖
✍🏼አሚር ሰይድ
አቡበከር ሲዲቅ በሀቢቡና ሙሀመድ በነቢዩ ﷺ ህልፈተ-ቀን ጠዋት ላይ ነቢዩ ﷺ በመልካም ጤንነት ላይ በማግኘታቸው፤ ኸርጃ ቢንት ዙሀይር የተባለች ባለቤታቸውን ለመጐብኘት ከመዲና ጥቂት ማይሎች ወጣ ብለው ተጓዙ:: ብዙም ሳይቆዩ የነቢዩን ሕልፈተ-ሕይወት በመስማታቸው ከሄዱበት ተመለሱ:: እንደ ደረሱም በመስጂዱ አካባቢ ከፍተኛ የሆነ ግርግር አስተዋሉ፡፡ ማንንም ሳያናግሩ የነቢዩ ﷺ አካል ወዳረፈበት ወደ ልጃቸው ዓኢሻ ቤት በመሄድ ፈቃድ ጠይቀው ገቡ፡፡ ከዚያም እንባ ባይናቸው እየወረደ የነቢዩን ፊት ከሳሙ በኋላ፡- “ቤተሰቦቼ መስዋዕት ይሁኑልህ! የተወሰነልህን አንዲት ሞት ቀምሰሀታል😢፡፡ ዳግም ሞት ግን አይነካህም!” እያሉ እያለቀሱ ያንን የተከበረ ገላ በጨርቅ በመሸፈን ወደ መስጂድ አቀኑ፡፡
በመስጂዱ ውስጥ በርካታ ሰዎች ተሰባስበው ያነባሉ፡፡ ዑመር ኢብን ኸጧብም በከፍተኛ የሀዘን ስሜት ተውጠው:- “ነቢዩ አልሞቱም!” በማለት ይፎክራሉ፡፡ አቡበከር ዑመርን ሊያቀዘቅዟቸው ሞክረው ነበር፡፡ ሆኖም ዑመር ቁብም አላሏቸውም፡፡አቡበከር (ረ.ዐ) የነገሩን አሳሳቢነት በማጤን ዑመርን ተወት አድርገው ወደ አንድ የመስጂዱ ጠርዝ በመጠጋት ጠቃሚና ታሪካዊ የሆነ ንግግር ማድረግ ጀመሩ፡፡ አብዛኛው ሰው ወደሳቸው ጠጋ ብሎ ያደምጥ ጀመር፡፡
⚠️ #ሰዎች_ሆይ!" አሉ አቡበከር። “ከእናንተ ውስጥ ሙሀመድን የሚገዛ ካለ ሙሀመድ : ማረፉን ይገንዘብ፤ አላህን የምትገዙ ከሆነ ግን አላህ ሕያውና የማይሞት መሆኑን እወቁ፡፡" በማለት የሚከተለውን የቁርኣን አንቀፅ አነበቡላቸው፡-
ሙሐመድም ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ ታዲያ ቢሞት ወይም ቢገደል ወደ ኋላችሁ ትገለበጣላችሁን??ወደኋላው የሚገለበጥም ሰው አላህን ምንም አይጎዳም፡፡ አላህም አመስጋኞቹን በእርግጥ ይመነዳል፡፡(አል ኢምራን 144)
ይህ የአቡበከር (ረ.ዐ) ንግግር የአብዛኛዎቹን ልብ መለስ አደረገ፡፡ በዚህም ዑመር (ረ.ዐ) ከነበሩበት ሁኔታ ቀዝቀዝ አሉ፡፡
ይህንን ጉዳይ አስመልከተው ዐብዱላህ ኢብን ዐባስ “ምንም እንኳ ይህን አቡበከር የጠቀሱትን የቁርአን አንቀፅ በተደጋጋሚ ያነበብነው ቢሆንም ገና በዚያ ወቅት የወረደ ነበር የመሰለን፡፡” በማለት አድናቆታቸውን ገልፀዋል፡፡
🔰🔰 በዚህም አቡበከር (ረ.ዐ) በቀዳማዊ ኸሊፋነት
የነቢዩን ቦታ ተረከቡ፡፡ ከቃለ መሐላው ፍፃሜ በኋላ ኸሊፋው አቡበከር (ረ.ዐ) የሚከተለውን የመግቢያ ንግግር አደረጉ፡-
⚠️ #ሰዎች_ሆይ! ምንም እንኳን እኔ ከማንኛችሁም ባልሻልም፤ ባለ አደራችሁ አድርጋችሁ መርጣችሁኛል፥ ትክክለኛ ከሆንኩኝ ታዘዙኝ፥ ከተሳሳትኩም አርሙኝ፡፡ አዎ እውነት ማለት ታማኝነት ነው፥ ሐሰት ማለትም እምነት አጉዳይነት ነው፡፡ ከእናንተ መሐከል ደካማው ድርሻውን እስከሰጠው ድረስ በኔ ዘንድ ኃያል ነው፥ የአላህ ፈቃድ ከሆነ ኃያሉም የሌሎችን ድርሻ እስኪሰጥ ድረስ በኔ ዘንድ ደካማ ነው፡፡ ንቁ! በአላህ መንገድ ላይ መታገል ለሚያቆሙ ሕዝቦች አላህ የሐፍረት ካባ ያከናንባቸዋል፡፡ በርካሽ ተግባራት የሚዘፈቁ ሕዝቦችንም መቅሰፍት ያወርድባቸዋል፡፡
አላህንና ነቢዩን ﷺእስከታዘዝኩ ድረስ እንድትታዘዙኝ እጠይቃለሁ፡፡ አላህንና ነቢዩን ﷺካልታዘዝኩ ግን ባትታዘዙኝ መብታችሁ ነው::አሏቸዉ
📕📕አቡበክር ሲዲቅ ነቢዩ ﷺበተሳተፉባቸው የጦር ፍልሚያዎች በሙሉ ተገኝተዋል፡፡ በመጀመሪያውና በታሪካዊው የበድር ጦርነት ወቅትም እንደ ጥላ
ከነቢዩ ﷺ ጎን ባለመለየት ተፋልመዋል፡፡ በዚህ ጦርነት ወቅት የገዛ ልጃቸው በቁረይሾች ወገን ተሰልፎ ተዋግቷቸው ነበር፡፡ ይኸው ልጃቸው ኢስላምን ከተቀበለ በኋላ በአንድ ወቅት፡- “አባቴ ሆይ! በበድር ጦርነት ወቅት ከአንዴም ሁለቴ ልገድልህ የምችልበት አጋጣሚ አግኝቼ ነበር፡፡ ሆኖም ለአንተ ባለኝ ጥልቅ ፍቅር ምክንያት ሰይፉን ባንተ ላይ ማንሳት ተሳነኝ” በማለት ገለፀላቸው:: አቡበከር ግን (ከሁሉም በፊት ኢስላም ብለው የተነሱ በመሆናቸው) "እኔ ይህንን አጋጣሚ አግኝቼ ቢሆን ኖሮ አንተን ከመግደል ወደኋላ አልልም ነበር” በማለት መልሰውለታል፡፡
⚡️⚡️ አንድ ዕለት አቡበከር (ረ.ዐ) ሚንበር ላይ ወጥተው እንዲህ አሉ፡፡ "ሁላችሁም እንደምታውቁት ባለፈው ዓመት የአላህ መልዕክተኛ ﷺአሁን እኔ ከቆምኩበት ቦታ ላይ በመካከላችሁ ይገኙ ነበር፡፡ ... ይህን ካሉ በኋላ ማልቀስ😢 ጀመሩ፡፡ ከዚያም ንግግራቸውን ደገሙት፡፡ እንደገናም ማልቀስ ጀመሩ፡፡ አሁንም ለሶስተኛ ጊዜ ለመናገር ሞከሩ፡፡ ሆኖም ግን ራሳቸውን መቆጣጠር ባለመቻላቸው እንደገና ማልቀሳቸውን ተያያዙት…” (ቲርሚዚ)
✏️✏️ አዒሻ (ረ.ዐ) አባቷ አቡበከር (ረ.ዐ) ሊሞቱ በተቃረቡበት ጊዜ የሆነውን ሁሉ ታስታውሳለች፡፡ በአባቷ ላይ ይታይ የነበረው ደስታ ምንጩ ከወዳጃቸውና ከውድ ጓደኛቸው ጋር የሚቀላቀሉበት ጊዜ መቃረቡን በማወቃቸው እንጂ ከቶም በሌላ ምክንያት አልነበረም፡፡ ነብዩ ﷺ ከሞቱ ቡሀላ ሀዘኑ ናፍቆቱ ከአቅም በላይ ሁኖባቸዉ ሙተዉ ነብዩ ﷺ ጋር ለመገናኘት ነበር ናፍቆታቸዉ፡፡
አዒሻ (ረ.ዐ) እንዲህ ትላለች፡- “አንድ ዕለት አባቴ በፅኑ ታመው የመሞቻ ፍራሻቸው ላይ ሳሉ እንዲህ በማለት ጠየቁ፡- ‹ዛሬ ቀኑ ምንድን ነው?›
.....እኛም ‹ቀኑ ሰኞ ነው አልናቸው፡፡ እርሳቸውም እንዲህ አሉ፡-
...... ዛሬ ምሽት ከሞትኩኝ እስከ ነገ ድረስ ሳትቀብሩኝ እንዳታቆዩኝ፡፡ ምክንያቱም ለእኔ ተወዳጅ የሆኑት ቀናትና ሌሊቶች ከአላህ መልዕክተኛ ﷺ ጋር የምገናኝባቸው ናቸውና፡፡' አሉ (አህመድ)
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከሞቱ በኋላ አቡበከር (ረ.ዐ) ይኸ ነው የሚባል ትርጉም ያለው ሕይወት አልኖሩም፡፡ የወዳጃቸውና ጓደኛቸው ሞት ያስከተለባቸው ሀዘን በዚህች ዓለም ላይ በሰዎች መካከል እየኖሩ የባይተዋር ዓይነት ስሜት እንዲሰማቸው አድርጓቸው ነበር፡፡
🌹🌹 እንዲህ ይወዱህ ነበር ሀቢቡና ዛሬ ግን ከምላሳችን ሳያልፍ ልባችን ሳይገባ እንወዳለን እንላለን፡፡
አላህ ሆይ ትክክለኛ የሀቢቡና ሙሀመድ ﷺፍቅር እደለንና የፍቅራቸዉን ድካ አሳየን ያረብ
❤️ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ ሰይዱና ሙሀመድ ﷺ❤️
◈━━━━━━━━◈━━━━━━━━
4 another channal👇
hottg.com/Islam_and_Science
💐<<<<<<>>>>>>⭐️<<<<<<>>>>>>💐
hottg.com/IslamisUniverstiy_public_group
hottg.com/IslamisUniverstiy_public_group
>>Click here to continue<<