🎖 #ስላስደነገጥከዉ_ሶስት_ቁና_ጨምርለት 🎖
✍ አሚር ሰይድ
ከአይሁድ ታላላቅ መሪዎች የነበረው ዘይድ ኢብኑ ሰዕነህ ወደ ነቢያችን ﷺ ዘንድ መጣ። ይህ ሰው ከሳቸው ላይ እዳ ነበረው። ድንገትም ከኋላቸው ሆኖ ኩታቸውን ሰብስቦ አንገታቸውን በኃይል አነቃቸው። ከዚያም እናንተ የዐብዱልሙጠሊብ ልጆች የሰውን እዳ ታቆያላችሁ??በማለት በኃይለ ቃል ተናገራቸው። ዑመር ከአጠገባቸው ነበሩ ሰውየውንም ገፍትረዉ ጣሉት። በጣምም ተናገሩት።
ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ የዑመርን ድርጊት አልወደዱለትም። ፈገግ አሉና 'አይ አንተ ዑመር! እኔና ይህ ሰው እኮ ካንተ የምንፈልገው ከዚህ የተሻለውን ነገር ነበር። አሁን ያደረግከው ነገር ለኛ ምንም አይጠቅመንም። እኔን በአግባቡ ያለብኝን እዳ እንድመልስለት እሱ ደግሞ የሰጠኝን ነገር በሥርዓት እንዲጠይቀኝ ማመላከት ትችል ነበር' አሉት። .....አስከትለውም እንዲህ አሉት “ለነገሩ ከተስማማንበት የጊዜ ቀጠሮ ሶስት ቀን ቀርቶታል። ቢሆንም ግን በል ሒድና የዚህን ሰውዬ እዳ ክፈለው። አንተ ደግሞ ስላስደነገጥከው ሦስት ቁና ጨምርለት!።'አሉት
ነቢይ ካልሆነ በስተቀር ማንም ከዚህ ዓይነቱ የሥነ-ምግባር ምጥቀት ላይ ሊደርስ አይችልም። አይገርምም! 'ስላስደነገጥከው ሶስት ቁና ጨምርለት። ሰውየው ባላሰበው መልኩ ካበደረው በላይ ጭማሪ ትርፍ አገኘ። በዚህ ባየው ክስተት አይሁዱ ሰውዬ ተገርሞ ብቻ አላበቃም።የአላህ ፈቀድም ሆነና እስልምናን ተቀበለ።
⚡️⚡️⚡️ይህ ሰው በሚያምንበት መፅሐፉ ተውራት ውስጥ ስለተነገሩት የነቢዩ ﷺ ባህሪዎች መረጃ ነበረው። የሰለመበትንም ምክንያት ሲናገር በዚህ ሰው ላይ ሁሉንም ነገሮች ሞከርኩኝ። ሁለት ነገሮች ብቻ ሲቀሩኝ ሁሉንም አየሁኝ። እነሱንም ዛሬ ለማረጋገጥ ቻልኩ “መቻሉ ታጋሽነቱ መሀይምነቱን ይቀድማል። ድንበር ከታለፈበትም የመቻል ሁኔታው እየጨመረ ይሄዳል ብሏል።
#ሀቢቡና_ሙሀመድ_ﷺ 😍😍
👌ሰይዲና ሙሀመድ ﷺ የእናንተ ባህሪ የሌላ ሀይማኖት አማኞችን ወደ ኢስላም ካልተጣራ ኢማናችሁ ላይ ደካማ ናችሁ ብለዋል...የእኛ ባህሪ ሌሎችን ወደ ኢስላም ይጣራል ወይ❔❔ወይስ እንኳን ሌሎችን ሊጣራ ለሙስሊም አማኙን የሚጎረብጥ እኔ ብቻ ነኝ ትክክለኛ አቂዳ የያዝኩት እያለ የሚያስቸግር ...ወይም በሚያሳየዉ ባህሪ አንተ ብሎ ሙስሊም እየተባልን ኢስላምን እያሰደብን ነዉ ወይ❓❓
ሁሉም ራሱን ይፈትሽ
█
┻┻
╚▩PubLished by ▩╗
ISLAMIC UNIVERSITY
◈━━━━━━━━◈━━━━━━━━
4 another channal👇
hottg.com/Islam_and_Science
💐<<<<<<>>>>>>⭐️<<<<<<>>>>>>💐
hottg.com/IslamisUniverstiy_public_group
hottg.com/IslamisUniverstiy_public_group
>>Click here to continue<<