TG Telegram Group & Channel
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር) | United States America (US)
Create: Update:

ኢማምነትና ኸጢብነት ሸሪዐዊ ሃላፊነቶች ናቸው። በሸሪዐዊ ሃላፊነት ላይ በአግባቡ አማናን መወጣት ይገባል። የራስን ፍላጎት ብቻ ከመከተል ይልቅ ሰፊውን ተገልጋይ ማሰብ ይገባል። ስላሰኘህ ብቻ ማስረዘም፣ ስለ ታከተህ ብቻ ማሳጠር ተገቢ አይደለም። ኢማም ወይም ኸጢብ የሆነ ሰው አቅመ ደካሞችን፣ ባለ ጉዳዮችን፣ ህመምተኞችን፣ አዛውንቶችን፣ ፀሐይ ወይም ዝናብ ላይ ያሉ ሰጋጆችን ወይም አድማጮችን ታሳቢ ማድረግ አለበት። ነብያችንኮ ﷺ የሚያለቅስ ልጅ ድምፅ ሰምተው እናቱ እንዳትረበሽ በሚል ሶላት ያሳጥሩ ነበር።
ልክ እንዲሁ በኸጢቦች የሚነሱ ርእሶችም ማህበረሰቡ ያለበትን ሁኔታ ወይም ወቅታዊ ጉዳዮችን የዘነጉ መሆን የለባቸውም። ረመዷን ላይ አብዛኛው ደዕዋ ስለ ረመዷን ነበር። ይሄ ጥሩ ነው። ነገር ግን በዘረኝነት ስንታመስ፣ በሱስ ስንወረር፣ ነጋዴው መሀል ማጭበርበርና መካካድ ሲንሰራፋ፣ መጨካከን ሲበዛ፣ ሺርክና ቢድዐ ሲስፋፋ፣ ... ዱዓቶችና ኸጢቦች ጭልጥ ብለው ሌላ አለም ውስጥ ሊሆኑ አይገባም። አስተማሪ ማለት ልክ እንደ ሃኪም ነው። ሃኪም የውስጥ ደዌ ለማከም የቆዳ መድሃኒት አይሰጥም። ልክ እንዲሁ ለወገኑ ተቆርቋሪ የሆነ ዳዒያህ ማለት ህዝቡ ያለበትን ነባራዊ ሁኔታ እያየ ተገቢውን ህክምና የሚሰጥ ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://hottg.com/IbnuMunewor

>>Click here to continue<<

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)