TG Telegram Group & Channel
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር) | United States America (US)
Create: Update:

ይድረስ ለወይዘሪት አ - ሕ - ባ - ሽ
ይዘገያል እንጂ አህያ የጅብ ነው!!
~~ ~~~~
በናንተ ምክኒያት ስንት ኢስላማዊ ተቋም ተዘጋ? ስንቱ ተደበደበ? ስንቱ ታሰረ? ስንቱ ሀገሩን ጥሎ ተሰደደ? ስንት የደዕዋ እንቅስቃሴ ተገታ? ስንትስ ቤተሰብ ተናጋ? ከምንም በላይ ደግሞ በኢስላም ስም ስንት የተበላሸ ዐቂዳ ደካሞች ላይ አሰረፃችሁ? ኢስላምን ስንት አመት ወደ ኋላ ለመጎተት እየተውተረተራችሁ እንደሆነ ለማንም አይሰወርም - ለካ * ፊ & ር እንኳን፣ ለናንተ ሲቀር፡፡ እናንተማ ከሰል ጠቆረ ውሃ ቀጠነ ብላችሁ የምትከራከሩ ናችሁ፡፡ እናንተ'ኮ “የትኋንና የቅማል ደም ነጃሳ ነው፤ የነካውም ሰው አወቀም አላወቀም ሶላቱ ውድቅ ነው” የምትሉ ናችሁ፡፡ ሀሰት ካላችሁ ኪታባችሁ ይናገራል፡፡ (ቡግየቱ ጧሊብ፡ 87(ሁለተኛ እትም፡ 119)) እንዴት ያለች “ፅድት” ያለች እምነት ነችi የዝንብ ጡሃራ አይነት እንዳትሆን ብቻ። “የዝንብ ጡሃራ ከነጃሳ እኩል ነው” ትል ነበር እህቴ፡፡ አባባሉን ከየት እንዳመጣችው አላውቅም፡፡ ብቻ ሳስታውስ አጓጉል የሆነ ንፅህና ስታይ ነበር እንዲህ የምትለው፡፡ ግን አ - ሕ - ባ - ሽ “ጡሃሪት” በነጃሳ ያውም በውሻ ኩስ፣ ሽንትና ልጋግ ተጨማልቆ መስገድ ይቻላል ትላለች፡፡ (ቡግየቱ ጧሊብ፡ 99 - 100 (አዲሱ እትም፡ 131-132))፡፡
እኔን የገረመኝ “የትኋንና የቅማል ደም ነጃሳ ነው” ማለታቸው አይደለም፡፡ ምንም እንኳን የሚገርም ቢሆንም፡፡ እኔን የገረመኝ “በውሻ ኩስ፣ ሽንትና ልጋግ ተጨማልቆ መስገድ ይቻላል” ማለታቸውም አይደለም፡፡ ምንም እንኳን የሚገርም ቢሆንም፡፡ እኔን የገረመኝ የሚገርመኝም ሁለቱ የተራራቁ ሀሳቦች ከአንድ አካል መውጣታቸው ነው፡፡ እስኪ አስቡት “የውሻ ኩስ አይነጅስም” ያለ ሰው “የትኋን ደም ይነጅሳል” ይላል? ኧረ ተመስጌን በሉ። “ምራቋም ይነጅሳል” ብለው የካ * ፊ & ር መሳለቀያ ቢያደርጉን ምን ይባል ነበር? ሞኝ ባያፍር የሞኝ ዘመድ ያፍር፡፡
ለነገሩ እንዲያው ቢገርመኝ አነሳሁት እንጂ ከዚህ የከፋ ስንት የዐቂዳ ክፍተት አለባቸው አይደለም ወይ? ለምሳሌ “አላህ አለም ውስጥም የለም፣ ከአለም ውጭም የለም፣ ከአለም ጋር ተያይዞም የለም፣ ተነጣጥሎም የለም” የሚሉት፡፡ ሱብሐነላህ! ሰዎቹ ምን እየሆኑ ነው? ይሄ ምን ማለት ነው? ይሄ ብቻ አይደለም “አላህ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ አይደለም” ይላል ሸይኻቸው አብደላህ አልሀረሪ፡፡ ምነው ስትሉ “ለምሳሌ አላህ መበደል አይችልም” ሲል ይፈላሰፍባችኋል፡፡ እናስ አላህ ስላቃተው ነው እንዴ የማይበድለው? ፍትሃዊ ስለሆነ እንጂ፡፡ ይሄውና በሐዲሠል ቁድሲ ላይ፡- “ባሮቼ ሆይ! እኔ በራሴ ላይ በደልን ክልክል አድርጊያለሁ፤ በናንተም መካከል እንዲሁ ክልክል አድርጌዋለሁና አትበዳደሉ” ይላል ጌታችን፡፡ ስለዚህ ስለሚችል አይደለም እንዴ በራሱ ላይ ክልክል ያደረገው? ባይችል እንዲህ ይል ነበር? ኧረ እነኚህ ሰዎች በምንኛ ነው የሚያስቡት?
ይሄን ሁሉ እያደረጉ ከማንም በላይ ለኢስላም እየሰሩ እንደሆነ ይነግሩናል፡፡ ድንቄምi “ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል” ነውና ነገሩ ይሄው ለጊዜው የሚችሉትን ብቻ ሳይሆን ከጉልበተኛ ተጠግተው የማይችሉትንም ጭምር እያደረሱ ነው፡፡ “ውጭ ካለ መቶ ጠላት ቤት ውስጥ ያለ አንድ ጠላት የከፋ ነው” ይላሉ ዐረቦች፡፡ ጥፋታችሁ ምንኛ ከፋ?! ይሄ አቋማችሁ ድንገት አንድ ቀን ተሳስታችሁ ካሰባችሁ ያሳፍራችኋል፡፡ ምናልባት ካሰባችሁ።
ኧረ አላህን ፍሩ! ሞት አለ፣ የቀብር ጥያቄ አለ፣ ነገ አላህ ፊት መቆም አለ፣ ሲራጥ አለ፣….፡፡ ከውስጣችሁ አላህን የሚፈራ የለምንዴ? ለነገሩ ይሄ ቋንቋ መቼ ይገባችኋል? ጨው ቀምሳችኋላ! ምነው “አልገባንም” ብላችሁ ዝም ባላችሁ!!! ገልብጣችሁ መረዳታችሁ ከፋ እንጂ፡፡
ግን ቢገባችሁም ባይገባችሁም ወላሂ ወቢላሂ ወተላሂ ትሸነፋላችሁ! እርግጠኛ ሆኜ ነው የምናገረው! እየጠነቆልኩ አይደለም፡፡ በጥንቆላም በኹራፋትም አላምንም፡፡ ይቺ የናንተ ናት፡፡ እናም እላለሁ፡፡ አይወድቁ አወዳደቅ ነው የምትወድቁት፡፡ ሰማያዊ፣ መለኮታዊ መመሪያ አንብቤ ነው ይህን የምለው፡፡ ኢስላምን ሊያጠቃ የመጣ የውስጥም ይሁን የውጭ ጠላት መቼም ቢሆን ቋሚ ድል ሊቀናው አይችልም፡፡ ይሄው አብረን እናንብብ፡-
{ یُرِیدُونَ أَن یُطۡفِـُٔوا۟ نُورَ ٱللَّهِ بِأَفۡوَ ٰ⁠هِهِمۡ وَیَأۡبَى ٱللَّهُ إِلَّاۤ أَن یُتِمَّ نُورَهُۥ وَلَوۡ كَرِهَ ٱلۡكَـٰفِرُونَ (32) هُوَ ٱلَّذِیۤ أَرۡسَلَ رَسُولَهُۥ بِٱلۡهُدَىٰ وَدِینِ ٱلۡحَقِّ لِیُظۡهِرَهُۥ عَلَى ٱلدِّینِ كُلِّهِۦ وَلَوۡ كَرِهَ ٱلۡمُشۡرِكُونَ (33) }
((የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ለማጥፋት ይፈልጋሉ፡፡ አላህም ከሓዲዎች ቢጠሉም እንኳ ብርሃኑን መሙላትን እንጅ ሌላን አይሻም፡፡ እርሱ ያ አጋሪዎቹ ቢጠሉም መልክተኛውን (ሙሐመድን) በቅን መንገድና በእውነተኛ ሃይማኖት ላይ ከሃይማኖት ሁሉ በላይ ይፋ ያደርገው ዘንድ የላከው ነው፡፡
[አሶፍ፡ 32-33]

ታማኙና እውነተኛው ነብይም ዐለይሂ ሶላቱ ወሰላም እንዲህ “ውርደትና የበታችነት ትእዛዜን በጣሰ ላይ ይሁን” ብለዋል።
በርግጥ ብዙ መስዋእትነት ታስከፍሉ ይሆናል፡፡ ቢሆንም ዲኑ ብዙ ሊከፈልለት የሚገባ ዲን ነውና ወደ ኋላ አንልም፡፡ በአላህ ፈቃድ ትወድቃላችሁ፡፡ እንዲያውም የሮማን አወዳደቅ ነው የምትወድቁት፡፡ ታዲያ አትሰሙም እንጂ ወድቃችሁ መውደቃችሁ ላይቀር መፈራገጥ ባታበዙ መልካም ነበር፡፡ “የማይበስል ጭንቅላት መብሰሉ ላይቀር የሰው ማገዶ ያስጨርሳል።”
-
ማሳሰቢያ፦
ከላይ ምንጭ እያያዝኩ የጠቀስኳቸውና ሌሎችም የአ - ሕ - ባ - ሽ ጥፋቶች የኋላ እትሞች ላይ ከፊሎቹን ገፅ በመቀየር ከፊሎቹን ደግሞ ከነ ጭራሹ በማውጣት አስወግደዋል። ታዲያ ካጠፉ ለምን ይነሳል? እንዳይባል "ስህተት ነበር ታርሟል" በማለት ፋንታ ሽምጥጥ አድርገው "ተዋሽቶብን ነው" እያሉ ነው።
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ መስከረም 10 / 2005)
የቴሌግራም ቻናል፦
https://hottg.com/IbnuMunewor

>>Click here to continue<<

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)