TG Telegram Group & Channel
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር) | United States America (US)
Create: Update:

የመጨረሻ የውይይት ጥሪ
~ ~~~~
بسم الله الرحمن الرحيم
ከሆነ ጊዜ ወዲህ ያለውን ንትርክ ውል ለማስያዝ ብለን የውይይት ጥሪ ያደረግንላቸው አካላት እስካሁን ድረስ ሰበብ እየደረደሩ ማሰናከሉን ተያይዘውታል። አሁን ደግሞ "ህዝብ ምን ያውቃልና ነው ዳኛ የሚሆነው?" በማለት ለህዝብ ክፍት መሆኑን እየነቀፉ ነው። በጉዳዩ ላይ ግር ያለው ሁሉ ከአሉባልታ ባለፈ በቀጥታ በመከታተል የጠራ አቋም ይይዝ ዘንድ ለህዝብ ክፍት ይሁን አልን እንጂ ህዝብ ዳኛ ሆኖ ነጥብ ይስጠን አላልንም። በዚያ ላይ ካልተግባባን የደረስንባቸውን ነጥቦች በጋራ ፅፈን በጋራ ለምናምንባቸው ዓሊሞች እናቀርባለን ብለናል። አንድ ጫፍ ላይ ሳንደርስ "ዓሊም እናስመጣለን" ወይም "ወደ ውጭ እንሄዳለን" ማለት መሸሻ ሰበብ እንጂ መፍትሄ መሻት አይደለም። ይህን ያክል ጉዳዩ ለታላላቅ ዓሊሞች እንዲቀርብ ብትፈልጉ ኖሮማ ተብዲዕ ውስጥ ከመዋኘታችሁ በፊት ተረጋግታችሁ ትጠብቁ ነበር።
ደግሞስ ከዚህ በፊት ለተለያዩ ወገኖች በግልፅ የውይይት ጥሪ ስናደርግ እንደነበር ይታወቃል። ለምን ያኔ አትነቅፉም ነበር? ጉዳዩ ወደናንተ ሲመጣ ነው ሰበብ የምትደረድሩት?
ለማንኛውም "ውይይቱ በአካል ቢሆን" ስትሉ ለነበራችሁ አካላት ሁሉ! ይሄው ጥያቄያችሁን በበጎ በማየት አንድ እርምጃ ለመቅረብ ወስነናል። ስለዚህ ሁለት ወይም ሶስት ሆነን ወደ ባህርዳር እንሄዳለን፣ ኢንሻአላህ። ይሁን እንጂ በር ዘግተን ከጥቂት ሰዎች ጋር ብቻ የምናወራበት ሁኔታ አይኖርም። በእንዲህ አይነት አካሄድ በተደጋጋሚ ተነድፈናል። ስለዚህ ባህዳር ውስጥ ካሉ መስጂዶች ውስጥ በአንዱ ይመቻች። የፈለገ ይታደምበት ዘንድ በሩ ክፍት ይሁን። ውይይቱን መቅዳትም፣ ቀጥታ ማስተላለፍም ለፈለገ አካል እንዲሁ ክፍት እንዲሆን እንፈልጋለን። ውይይቱን ለመምራትም የውጭ ሰው እንዲሆን አንጠይቅም። እዚያው ባህርዳር ያሉ መሻይኾች (ሸይኽ ዐብደላህ፣ ሸይኽ አሕመድ፣ ሸይኽ ሙሐመድ አወል፣ ኡስታዝ ዩሱፍን ጨምሮ) ይምሩት።
ለመረጃ ያክል ከውስጣችሁ ከኢኽዋን ጋር በግልፅ ውይይት ያደረገ ሰው አውቃለሁ። ይህንን የማነሳው ጥሪያችንን በሆነ ማመሀኛ እንዳትገፉት ነው።

NB፦
~~
በነገራችን ላይ ሰሞኑን በሕሩ የለቀቀውን ድምፅ አልሰማሁትም። የሰሙ ሰዎች ሲነግሩኝ ግን በዚህ መጠን መድረሱ ገርሞኛል። እንዲህ አይነቱን የዙልም አካሄድ ለህዝብ መበተኑ "ለአኺራዬ ያዋጣኛል" ካለ ምርጫው የራሱ ነው። ለጊዜው ግን ለራሴ እየተከላከልኩ ምላሽ በመስጠት ዋናውን የውይይት አጀንዳ ማደብዘዝ አልፈልግም። እቅጩን ስናገር ከውይይቱ ጥሪ ሰበብ እየደረደሩ የሚሸሹት የያዙት አቋም ሆድ የሚያስነፋ እንዳልሆነ ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ነው። ስለዚህ የሚፈልጉት ወይ በተዘጋ ክፍል ውስጥ ወይ ደግሞ ጭፍን ደጋፊ ብቻ ባለበት ቦታ ያለ ጠያቂ፣ ያለ ሞጋች እንደፈለጉ መወንጀል ነው። በዚሁ መልኩ ብቻ ነው የምንቀጥለው ካሉ፣ ለህሊናቸው ካልጎረበጣቸው መንገዱን ጨርቅ ያድርግላቸው። "እናንተ ዘንድ የሌለ እውነት አለን" ካሉ ይሄው ለመታረም ዝግጁ ነን እያልን ነው። እኛ እጅ ለመስጠት ፈቃደኞች ካልሆንም "እውነታቸውን" ገልጠው እንደሚያስቡት በኛ የተሸወዱትን አካላት የሚያተርፉበትን እድል ይጠቀሙበት። የቀደመ አቋሙን የቀየረው ማን እንደሆነ ይለይ። እዚያም እዚህም የምንሰማው የተምይዕ ውንጀላም ተፍረጥርጦ ይውጣ። ይሄ ወደ ሱና በመጣራትና ቢድዐን በመዋጋት ጭንብል የተንሰራፋው ውሸትም ይጋለጥ። ባጭሩ እንገናኝና ወይ አጥፊው ይታረም፤ ወይ ውሸታሙ ይፈር።
~ ሰላም ~

>>Click here to continue<<

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)