TG Telegram Group & Channel
وبيجوت Tube | United States America (US)
Create: Update:

▫️የተባረከው የፍልስጤም ምድር

▪️ክፍል~3

ፍልስጥኤሞች ከ20ኛው ክፍለ-ዘመን ጀምሮ ህልውናቸውን ሊያስክድ የመጣባቸውን ባዕድ ኃይል በከፍተኛ አልበገር ባይነት የህይወት መስዋዕትነት እየከፈሉ በመከላከል ላይ ናቸው፡፡ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በመምለካና በቃሂራ የሚገኙ አንቱ የተሰኙ ሙፍቲ ዑለሞች ሳይቀሩ ለምን ምድሩን እንዳለ ጥላችሁላቸው አትሰደዱም የሚል ወኔ ሰላቢ ምክር እየለገሷቸውም እንኳ እጅ አልሰጡም፡፡ የመከላከሉ ጦርነት አጀማመርና ሂደት እንደ አንድ ተጨቋኝ ህዝብ ትግል የተለያዩ መርሐላዎችን (ስቴጆችን) ማለፍም ነበረበትና የሚከተለውን ይመስላል፡-
በ1918 አንድ የአርበኞች ኮሚቴ የፍልስጥኤም ሹርጣ አባላትን በማካተት በሕቡዕ ተቋቋመ፡፡ ይህ ኮሚቴ ለዐረብ አብዮት መሠረት በመጣልና በምሥራቅ ኦርዶን በሚኖሩት በረኸኛ ዐረቦች (አዕራብ) ዘንድ የጽዮናዊያንን ሤራ በማጋለጥና ንቃተ-ኅሊና በመፍጠር የላቀ ሚና ተጫውቷል፡፡ ኮሚቴው በመሪዎቹና በአስተባባሪዎቹ ላይ በደረሰው እስራትና ማሳደድ የተነሣ ሊዳከም ቢችልም ብሶት እያባባሰው የመጣው የፍልስጥኤሞች መነሳሳት ግን እየቀጠለ በመሄድ በ1920 ከኤፕሪል 4 እስከ 10 የዘለቀ አመፅ ተካሂዷል፡፡ ቀጥሎም በ1921 የጃፋ አብዮት ተቀጣጥሏል፡፡ እንደገናም የቡራቅ አብዮት በ1929 ቀጥሏል፡፡ እነዚህ አመጾች ምንም እንኳ ባደረጃጀት ያልተሟሉና ግብታዊ የነበሩ ቢሆንም ትግሉን በማቀጣጠልና የጽዮናዊያን መሠሪ እቅድ ባንዴ ፍጻሜ እንዳያገኝ በማጓተት የጎላ ድርሻ ነበራቸው፡፡
የፍልስጥኤም ታጋዮች ተጨማሪ ኃይል ማደራጀት ቀጠሉ፡፡ ከነዚህ መሀል በኢዘዲን አልቀሳም የተደራጀው በዋናነት ይጠቀሳል፡፡ ኢዘዲን አልቀሳም ማነው? እሱ ከሶሪያ ወደ ፍልስጥኤም በመምጣት የዲን ኡስታዝ ሆኖ የራሱን የትግል እንቅስቃሴ የጀመረ ሰው ነው፡፡ በ1926 አንድ የንቅናቄ ኮሚቴ ውስጥ በአባልነት ይመዘገባል፡፡ በ1928 የንቅናቄውን የሐይፋ ቅርንጫፍ ይመሰርታል፡፡ ቀጥሎም የዚሁ ቅርንጫፍ መሪ ይሆናል፡፡ በ1930 የንቅናቄው የአስተዳደር ኮሚቴ አባል በመሆን የመሪነቱን ቦታ ይጨብጣል፡፡
ከዚህ በኋላ አልቀሳም የመንግሥት ሠራተኛ በመምሰል በብዙ የፍልስጥኤም ክልሎች እየተዘዋወረ በአምስት አምስት አባላት የተደራጁ ህዋሳትን በስፋት አዋቀረ፡፡ ኢስላማዊ ህግጋት የትግሉ መመሪያ መሆን እንዳለባቸው አስተማረ፡፡ ብቸኛው የነፃነት መንገድም ጂሃድ ፊ ሠቢሊላህ መሆኑን አሠመረበት፡፡ አፅንዖት አደረገበት፡፡
ይህ በኢዘዲን አልቀሳም የተደረጃ የህቡዕ ንቅናቄ በዐይነቱ ለየት ያለና በዐረብ ፍልስጥኤሞች የትግል ታሪክ ውስጥ ትልቁ የፊዳዒይን (የመስዋዕትነት) ንቅናቄ እንደሆነም ይታመናል፡፡ ማዘዣ ቢሮዎቹ ደሃው ህዝብ በሚበዛበት የኢያሪኮ ከተማ ነበር፡፡ በአካባቢው ላይ ሰፊ ተቀባይነት እያገኘ ሲመጣ አደረጃጀቱን አሰፋው፡፡ የደዕዋና የአህዝቦት፣ የወታደራዊ ሥልጠና፣ የአቅርቦት፣ የኤሌክትሮኒክስና የውጭ ግንኙነት አካላትን በመፍጠር አቋሙን ይበልጥ አጠናከረ፡፡
በ1935 ኢዘዲን አልቀሳም የአብዮቱን መጀመር ይፋ አደረገ፡፡ ይህም የሆነው ሠላማዊ መፍትሄ የማፈላለጉ ጥረት ለተደጋጋሚ ጊዜ ተሞክሮ ያለውጤት መቅረቱ እውን ከሆነ በኋላ ነው፡፡ የአብዮቱን መጀመር ተከትሎ በቀሳም ታጣቂዎችና በእንግሊዝ ጦር መካከል ተከታታይ ግጭቶች ተካሄዱ፡፡ ብዙ ፍልሚያዎች ተደረጉ፡፡ ኋላ አልቀሳም ማፈግፈግ ግድ ሆነበት፡፡ ከተወሰኑ የጦር ጓዶቹ ጋር አንድ ቦታ ላይ ከበባ ተደረገበት፡፡ እጁን በሰላም እንዲሰጥ ተጠየቀ፡፡ አልፈቀደም፡፡ በተከተለው የተኩስ ልውውጥ ዐቅጣጫዋ በውል ያልተለየ ጥይት አገኘችው፡፡ ተገደለ፡፡ በተቀሩት ጓዶቹና በእንግሊዝ ጦር መካከል የከረረ ውጊያ ተካሂዶ የሞቱት ሞተው የተቀሩት ጠላት እጅ ወደቁ፡፡
አልቀሳም የመሰዋቱ ዜና ሲሰማ መላው ፍልስጥኤም ተላወሰ፡፡ የቀብር ሥነ-ሥርዓቱ ለፍልስጥኤም ሌላ የትግል ቃል ኪዳን ማሰሪያ ቀን ሁኖ ዋለ፡፡ የቀሳም ንቅናቄ በዓላማውና በተነሳሽነቱ ረገድ በዐይነቱ የመጀመሪያው ነው፡፡ በአይሁዶችና በእንግሊዞች ላይ በቀጥታ ያነጣጠረ ወታደራዊ ንቅናቄ ነበር፡፡
ኢዘዲን አልቀሳም ለፍልስጥኤም ነፃነት መዋጋትን ሊልላሂ ብሎ ኒይያው አድርጎ ከሶሪያ ወደ ፍልስጥኤም በመምጣት ኑሮውን እዚያው ያደረገ አላህን ፈሪ ሰው መሆኑ ይታወቃል፡፡ እሱ ባቀጣጠለው ሰውራና በከፈለው መስዋዕትነት በፍልስጥኤሞች ዘንድ የላቀ ተነሳሽነት ተፈጠረ፡፡ ህዝቡ ተቀሰቀሰ፡፡ በርግጥም እሱ ያመላከተው የትግል መንገድ፣ የውጊያ ስልትና የተጋፋጭነት አቋም ትምህርት ሰጪ ነበር፡፡ የአይሁድ/ እንግሊዝን ጣምራ ኃይል ጂሃድን መርሁ ባደረገ ስልት መዋጋት እንደሚያስፈልግ በሁሉም ፍልስጥኤማዊ ዘንድ እየታመነበት መጣ፡፡
በቀሳም መሞት የፍልስጥኤም አብዮት አብሮ አልሞተም፡፡ ነገሮች ቤንዚን እንደተርከፈከፈበት እሣት ይበልጥ ተቀጣጠሉ፡፡ የ1936ቱ የተራዘመ አብዮት ፈነዳ፡፡ የሥራ ማቆም አድማ፣ ተገዳዳሪ ሠልፍ፣ ለቅኝ አገዛዝ ህጎች አልታዘዝ ባይነት፣ የዚህ አብዮት ዐይነተኛ መለያዎች ነበሩ፡፡ ህዝባዊ አመጹ ብረታዊ ድጋፍም እየታከለበት በ1930ዎችና በ1940ዎች ቀጥሏል፡፡
ሁኔታው በፍልስጥኤሞች ወገን ባጭሩ ከላይ የተወሳውን ዐይነት ገጽታ ሲኖረው በአይሁዶች በኩል ደሞ የተጀመረው አፍራሽ ድርጊት በእንግሊዝ ጦር ሽፋን ሰጪነት እንደቀጠለ ነበር፡፡ በ1930ዎቹና በ1940ዎቹ ይበልጥ እየተጠናከረና ዐይን እያወጣ የመጣው የጽዮናዊያን እንቅስቃሴ ጭፍን ደረጃ በመድረስ የ1948ቱን የአይሁድ መንግሥት (Jewish state) ምሥረታ እውን አደረገ፡፡
ፍልስጥኤሞች ይህን ፈጣጣ ድርጊት በይሁንታ አላለፉትም፡፡ በቁጥርና በትጥቅ ከፍ ብሎ ተጠናክሮ ከተጋረደባቸው የእንግሊዝ ጦርና የአይሁድ ሠፋሪ ታጣቂ ኃይል ጋር እጃቸው ላይ ባለ ነገር ሁሉ ተፋልመዋል፡፡ የተቀሰቀሰው የህዝብ ፍልስጥኤም ቁጣ በዋዛ እንደማይበገር የተረዱት እንግሊዞችና አይሁድ ሠፋሪዎች የተነሱበትን ግዛት የማስፋት እቅድ ዳር ለማድረስ ሲሉ እስከዛሬ ድረስ ጠባሳው ያልሻረውንና በሙስሊሙ ዓለም በተለይም ዐረብ ፍልስጥኤም ዘንድ መሪር ትውስታ ያስከተለውን የሜይ 15/1948 አስከፊ ድርጊት በፍልስጥኤም ሠላማዊ ህዝብ ላይ ፈፀሙ፡፡

🍁#ይ__ቀ__ጥ__ላ__ል🍁
--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot

>>Click here to continue<<

وبيجوت Tube

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)