TG Telegram Group & Channel
وبيجوت Tube | United States America (US)
Create: Update:

📕ብቻህን ትኖራለህ ብቻህን ትሞታለህ

ባል በበረሓ መሀል የሞት ጣር ያጣድፈዋል፤ ሚስት ትይዝ ትጨብጠው ጠፍቷት ግራ ቀኟን እያማተረች ታለቅሳለች።
‹‹ለምን ታለቅሻለሽ?›› ሲል ከሞት አፋፍ ላይ የሆነው ባሏ ጠየቃት።
‹‹መከፈኛ ልብስ እና ቀብር ቆፋሪም ሆነ ቀባሪ በሌለበት በዚህ በረሀ ማን ነው ሰግዶብህ ሚቀብርህ?›› ብላ ለቅሶዋን ቀጠለች።
‹‹አብሽሪ! ይህ እኮ ድሮ ረሱል ያበሰሩኝ ብስራት ማረጋገጫ ነው። እየውልሽ አንድ ግዜ ምን ሆንን መሰለሽ! ረሱልለአንድ ዘመቻ ሰሀቦቻቸውን አስከትለው ከከተማ ቀድመውኝ ወጡ፤ እኔም ተከታትያቸው የበረሀውን ጉዞ ለብቻዬ ጀመርኩት።
ነገር ግን በቅሎዬ እግሩ መጓዝ ሲሳነው እሱን ትቼ በእግሬ የበረሀውን አሸዋ ማቋረጥ ጀመርኩ። አንዴ ስሮጥ አንዴ ስራመድ ብዙ ከተጓዝኩ በኋላ ከረሱል እና ከሰሀቦቻቸው ጋር ተገጣጠምን።
ረሱል እኔን ሲመለከቱ ፊታቸው መፍካት ጀመረ። በሁኔታዬ ተደስተው የምርጠትን ዘውድ ከራሴ ላይ ደፉልኝ። እንዲህም አሉ አባ ዘር ሆይ! አላህ ይዘንልህ። ብቻህን ትጓዛለህ። ብቻህን ትሞታለህ። ብቻህንም ትቀሰቀሳለህ።
ብቻህን በሞትክ ግዜም የሙስሊሞች ቆንጮ የሆኑ ቡድኖችም በበድንህ ላይ ይሰግዱብሀል›› ሲል ከህይወት ማህደሩ ወደ ኋላ በትዝታ ተመልሶ ተረከላት።
ንግግሩንም ቀጠለ፦ ‹‹ነፍሴ ስትወጣ ጎዳናው አፋፍ ላይ አስጠግተሽ አስቀምጪኝ። ከዝያ ጎዳና በኩል እነዝያ የሙስሊሙ ቁንጮዎች ይመጡ ይሆናል›› ብሎ ተናዘዘላት።
ነፍስ ወጣች። ሚስትም የባሏን በድን ተሸክማ ከጎዳናው አፋፍ አጋድማ ያለአፅናኝ ታለቅስ ጀመር። ብዙም ሳይቆይ አብዱላህ ኢብኑ መስዑድን ያቀፈ የሰሀባዎች ጀመዓ ከዝያ ጎዳና ብቅ አለ።
‹‹ለምን ታለቅሻለሽ?›› ብለው ጠየቋት።
‹‹ይህ ባሌ አባ ዘር በበረሀ ሞተብኝ ምከፍንበትም ልብስ አጣሁ ቀባሪም የለም›› አለቻቸው።
ሰሀባዎቹም ልብሶቻቸውን እያወላለቁ በመሽቀዳደም ከፈኑት። ዱዓም እያደረጉ የሰሐቢዩን ገላ ከማረፍያ ላህዱ ውስጥም አስገቡት።
ያኔ በደጉ ዘመን በእግሩ በረሀውን አቋርጦ ወደ ነቢዩ የመጣ ጊዜ የረሱልን ደስታ እያወሱ ቀብረውት ጉዟአቸውን ቀጠሉ።

ሰላም በአቡ ዘር ላይ ይሁን!
የአላህ ውዴታም በሱ ላይ ይሁን!

--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot

>>Click here to continue<<

وبيجوت Tube

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)