TG Telegram Group & Channel
وبيجوت Tube | United States America (US)
Create: Update:

▫️የቆስጠንጢንያ ድል ከመሰረቱ

▪️ክፍል~8

ዑስማኒዮች በነቢያቸው (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ንግግር የቂን ብለዋል፡፡ ተፈፃሚ እንደሚኾን አምነው ጥረት አድርገዋል፡፡ በጥረታቸው ላይ ሶብረዋል፡፡ በመጨረሻም ድሉን አረጋግጠዋል፡፡ ቁስጠንጢኒያን ከፍተዋል፡፡ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እውነት ተናገሩ “….ምን ያምር አሚር ነው አሚሯ፣ ምን ያምር ጦር ነው ያም ጦሯ” ከዚህ ከዑስማኒዮች የጂሃዳዊ ተጋድሎ ታሪክ የሚወሰደው ትምህርት በዱሩሥ ወ ኢበር የቂን ማለት፣ ጥረት ማድረግ፣ በጥረቱ ላይ መሶበር ይኾናል ስኬት ነው፡፡

ሡልጣን ሙሐመድ አል-ፋቲሕ የቁስጠንጢኒያን መከፈት አረጋግጦ፣ ድሉን አጠናከረ፡፡ ቀሪ መሰናክሎችን አስወገደ፡፡ ከዚያ በኋላ ወደ ቀጣይ ፉቱሐቱ አመራ፡፡ ን
ሰርቢያ የዑስማኒያ መንግሥት አካል መሆን

እንደሚታወሰው ቀደምቱ የዑስማኒያ ሡልጣኖች በዓመታዊ የጂዝያ ክፍያ ለሰርብ ነፃነቷን ሲያውቁላት ቆይተዋል፡፡ ሰርቦች ግን በሁሉም አጋጣሚ የዑስማኒዮችን በሌላ ግንባሮች መጠመድ ባዩ ቁጥር የገቡትን ቃል በማጠፍ (ነቅዱል ዓህድ) በመፈፀም ጂዚያ አልከፍል ይላሉ፡፡ ስለዚህ ሡልጣን ሙሐመድ አልፋቲህ ሰርቢያን ከእንግዲህ ወዲያ ሙሉ ለሙሉ የዑስማኒያ መንግሥት አካልና ኣንድ ክፍለ-ሀገር ለማድረግ ቆርጦ ተነሳ፡፡ ወደዚያው በመዝመት በ858 ሂጅሪያ ሰርቢያ ገባ፡፡ ዙሪያ መሬቷን ቢቆጣጠርም ታዲያ ርዕሰከተማዋን ቤልግሬድን የሀንጋሪ ንጉሥ ባደረገው መከላከል ሳቢያ ሊከፍታት አልቻለም፡፡ ይሁንና በዚህ ድል ሰርቢያ ነፃነቷን አጥታ የዑስማኒያ መንግሥት አንድ ክፍለ-ሀገር (ዊላያ) ሆናለች፡፡

በመጨረሻም ከቤልግሬድ ውጪ አንዲትም ጋት መሬት ከዑስማኒያ ቁጥጥር ውጪ ሳትሆን ከተማዋን እንዳለች ትተው ወደ ሌላ ግንባር በ885 ሂጅሪያ በጣሊያን የባህር ጠረፍ ላይ የ‹ኦውትራኑት ከተማን ቢከፍትም የሱ መሞት የሠራዊቱን ግስጋሴ ሊገታው ችሏል፡፡ እነሆ ሡልጣን ሙሐመድ ዳግማዊ በአላህ መንገድ ስላደረገው ታላቅ ጂሃድና ብዙ ሀገራትንም ስለ መክፈቱ አል-ፋቲሕ መባልን የተቀፀለው ጀግና ሰው - በረቢዑል አወል 4ኛ ቀን 886 ሂጅሪያ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡ ኢጣሊያን ለመክፈት ታላቅ ጦር አስከትቶ በንቅናቄ ላይ ነበረ ፈጀዛሁላህ ኸይረን ዓኒል ሙስሊሚን ጀሚዓን

📕ማጠቃለያ

ዑስማኒያ ቱርኮች የኢስላም ጠላቶችን በመዋጋትና በነሱ ላይ ጂሃድ በማድረግ ከስድስት ክፍለ-ዘመናት በላይ ኢስላማዊውን ደዕዋ ተሸክመዋል፡፡ ከነሱ በፊት ማናቸውም ያላሳኩትን የቆስጠንጢኒያን መከፈት በጂሃዳዊ ተጋድሎ አሳክተዋል፡፡ ከነሱ በፊት ሌሎች ሙስሊሞች ችለው ያልከፈቷቸውን ሀገራትም እነሱ ከፍተዋል፡፡ የፉቱሐት ንቅናቄያቸውን አድማስ በማስፋት እስከ አውሮጳ እምብርት ድረስ ዘልቀው- ግሪክን ሰርብና ጀበል አስወድን፣ ሩማኒያን፣ ሀንጋሪያን፣ ስሎቫኪያን፣ ኢጣሊያን፣ ከትንሹ አስያ የተቀረውን ግዛት ሙሉ ቱርክን ፣ አርሜኒያን፣ ጆርጂያን፣ በተለይም ደሞ ቀውቃዝን፣...እያሉ ቀጥለው ግሥጋሴያቸው የተገታው ኦስትሪያ ርዕሰ ከተማ ቪየና በር ላይ ነው፡፡ እስከ ዛሬም አሻራቸው ለተመልካች እዚያ ይገኛል፡፡

ደውላ ዑስማኒያ ወይም የዑስማኒያ መንግሥት በታሪክ ብቅ ያለችበት ጊዜ 699 ሂጅሪያ ሲኾን መንበረ-ኸሊፋውን ግን እስከ 923 ሂጅሪያ አልጨበጠችም፡፡ የዑስማኒያ መንግሥት በዘመኑ እጅግ ገናና መንግሥት ነበረ፡፡ በዓለም ላይ በባህል በሥልጣኔና በወታደራዊ ክህሎት ወደር አልነበረውም፡፡ በአንድ ጊዜ በአራት ግዙፍ የውጊያ ግንባሮች የኢስላምን ጠላቶች ገጥሞ በኢስላማዊ መንገድ እየተዋጋ የተፅዕኖ አድማሱን በፉቱሐት እያሰፋ ኖሯል፡፡

📕አራቱ ግንባሮች የሚከተሉት ናቸው

1. በምዕራብ ግንባር - በዘመኑ ሰፊ ሀገረ-ግዛት የነበረውን የነምሳን ኢምፓየር - በዛው ግንባር - በመግሪበል ዐረቢያ ስፓኝን

2. በደቡብ ግንባር - ወደ ዐረብ ጀዚራ መስፋፋት የሚሹትን ፖርቱጋሎችን

3. በሰሜን ግንባር - ሩሲያን

4. በምሥራቅ ግንባር ከመስቀላዊያን ጋር በቃል ኪዳን ተሳስረው ባጠቃላይ አህሉ ሱንና ወልጀማዓን በተለይም ደሞ የዑስማኒያ መንግሥት የሚዋጉትን ራፊዳ ሺዓዎችን ይዋጋሉ፡፡

ነሣራ አውሮጳ የዑስማኒያን ኺላፈት በሙስሊም ሀገራት ላይ ዐረብ በሆኑትና ባልሆኑት ላይ ሁሉ - በኃይል እንደተጫነባቸው ቅኝ ገዢ ኃይል አስመስለው በመሳል በኡምማው መሀል ክፍፍል ለመፍጠር ሲዶልቱ ኖረው ወደ መጨረሻ ተሳክቶላቸዋል፡፡ እውነታው ግን እነሱ የዑስማኒያን ኺላፈት ከሳሉበት በተቃራኒ ነው፡፡ በዚህ የአውሮጳ ወጥመድ ውስጥ የወደቁና ኢስላማዊውን የዑስማኒያ ኺላፈት በኃይል እንደተጫነባቸው ቅኝ ገዢ ኃይል የተመለከቱ ዐረቦች በመሰረቱ የረሱልን (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ሐዲስ የዘነጉ ናቸው “ዐረቡ በአዕጀሚዩ ላይ ብልጫ አይኖረውም-በተቅዋ ቢኾን እንጂ ... ይሁንና ለዑስማኒያ ቱርኮች የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ምስክርነት ከምንም በላይ በቂያቸው ነው፡፡

“ወኒዕመል አሚር አሚሩሃ ፣ ወኒዕመል ጀይሽ ዛሊከል ጀይሽ”

🍁#ተ__ፈ__ፀ__መ🍁
--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot

>>Click here to continue<<

وبيجوت Tube

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)