TG Telegram Group & Channel
የ ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የስነምግባር እና ፀረ ሙስና ክበብ | Hawassa University Ethics and Anti corruption Club | United States America (US)
Create: Update:

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ Main Campus '‘ሙስናን መታገል በተግባር’' በሚል መሪ ቃል ዓለም ዓቀፍ የፀረ ሙስና ቀን በዛሬው ዕለት ተከብሯል፡፡

የምርምርና ቴ/ሽ/ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ታፈሰ ማቲዎስ ሙስናና የስነ ምግባር ችግር ለአለምችን እና ለሰው ልጆች ፈተና ሆኖ የቆየ ሲሆን በተለይ በአፍሪካ በሚገኙ ሀገራት እጅግ በጣም ብዙ ሀብቶች እንደሚመዘበሩና በዚህ ችግር ውስጥም እየዳከሩ እንደሚገኙ በርካታ ጥናቶች እንደሚያሳዩ ጠቅሰው አለማችን ለመሰረታዊ ፍላጎት የሚሆን በቂ ሃብት ቢኖራትም ጥቂቶች በስግብግብነታቸው የተነሳ የብዙሃኖችን ሃብት በመመዝበር ያለቅጥ በማከማቸታቸው ምክንያት ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል እንዳይኖር፣ የሰዎች የእርስ በርስ ግንኙነት እንዲደፈርስና በየቦታው ግጭት እየነገሰ እንዲመጣ ሆኗዋል ብለዋል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የስነ-ምግባርና ፀረሙስና ክበብ አስተማሪና ትምህርታዊ የሆነ ጭውውት እንዲሁም ሙስናን በተመለከተ ድንቅ የሆነ መነባነብ ለታዳሚው አቅርበዋል።

በተጨማሪም በፕሮግራሙ ላይ አቶ አባይነህ ገናሌ የስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት ተወካይ ዳይሬክተር ሙስናን መታገል በተግባር እንዴት ይቻላል በሚል ሃሳብ ላይ የመወያያ ሃሳብ ያቀረቡ ሲሆን ተሳታፊዎችም የተለያዩ ነጥቦችን አንስተው ተወያይተዋል፡፡

በመጨረሻም የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አያኖ በራሶ እንደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ከከፍተኛ አመራር ጀምሮ መምህራኖችና የአስተዳደር ሰራተኞች ለስራ የተመደበላቸውን ጊዜና ሰዓት እንዲሁም መገልገያ ቁሳቁሶችን በአግባቡ ከመጠቀም አንስቶ ሙስናን እና የስነ ምግባር ብልሽቶችን በመጋፈጥ እና ተማሪዎችም በስነ ምግባር የታነፁ ብቁ ዜጋ እንዲሆኑ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ አሳስበው ፕሮግራሙ ተጠናቋል።

https://hottg.com/HUethics

>>Click here to continue<<

የ ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የስነምግባር እና ፀረ ሙስና ክበብ | Hawassa University Ethics and Anti corruption Club

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)