TG Telegram Group & Channel
ግጥም ለሚጠማዉ | United States America (US)
Create: Update:

የፍቅር ሰላምታ
ጠጉርሽን ዳብሶ በጆሮሽ ያለፈው
ነፋሱ ምን አለሽ? በመስኮት ላይ ሆነሽ፡፡
የፍቅሬን ሰላምታ ሲያስተጋቡ ይዘው ተራሮች የላኩት፤
በሩቅ የሚታዩት።
የሚወዛወዙት ቆመው በመስኮትሽ
ዛፎቹ ምን አሉ? ይንሾካሾካሉ፡፡
አይተዋል ደብዳቤ ማታ ስጽፍልሽ ፤
ይግለጹ ምሥጢሩን ልቤ መሸበሩን።
ልብስሽን ስትለብሽ ወፎች የሚዘፍኑት
የሚሉት ምንድነው? ጡቶችሽን አይተው
በፍቅርሽ ሰላምታ ልቤን እንዲያክሙት ላኪያቸው ያምጡልኝ፤
መድኃኒቱን ይስጡኝ፡፡ ኮከቦች ከሰማይ ይጠቃቀሳሉ
ውበትሽን አይተው፤
በቅርጽሽ ተደንቀው።
በሰማዩ ባሕር ጠልቀው ይዋኛሉ
ፍቅርሽን ሊይዙ
ወደኔ ሊጓዙ፡፡
ምን አለች ጨረቃ በመስኮትሽ ገብታ
ስትነካ ፊትሽን፤ ተደግፋ አልጋሽን፡፡
ልኬልሽ ነበረ የፍቅር ሰላምታ ጠይቂአት ውሰጂ፤
መልሱንም ስደጂ፡፡
የቤተ ክርስቲያን ደወሉ ዘመረ ምን ሆኖ ይጮኻል?
ሰው ይሰበሰባል።
ጉዳችንን አይቶ ገልጦ ተናገረ
እባክሽ ለፍቅር ሞተን እንቀበሮ፣
ምነው ምን ፈለገ ሲጨፍር ከበሮ?
ተነሣ የሚለኝ? የሚቀሰቅሰኝ፡፡
ፍቅርሽና ፍቅሬን በመሐረም አስሮ እንሒድ ተቃቅፈን፤
ደብቆ ይውሰደን፤
የበረረው ልቤ ካጠገቤ ጠፍቶ ምን ምሥጢር አወራ?
ደንግጦ እየፈራ፡፡
ስታንጎራጉሪ መኝታሽ ቤት ገብቶ የፍቅሬን ሰላምታ
ይስጥሽ በቀስታ፡፡ከታሪኩ ረጋሳ❤️❤️

የፍቅር ሰላምታ
ጠጉርሽን ዳብሶ በጆሮሽ ያለፈው
ነፋሱ ምን አለሽ? በመስኮት ላይ ሆነሽ፡፡
የፍቅሬን ሰላምታ ሲያስተጋቡ ይዘው ተራሮች የላኩት፤
በሩቅ የሚታዩት።
የሚወዛወዙት ቆመው በመስኮትሽ
ዛፎቹ ምን አሉ? ይንሾካሾካሉ፡፡
አይተዋል ደብዳቤ ማታ ስጽፍልሽ ፤
ይግለጹ ምሥጢሩን ልቤ መሸበሩን።
ልብስሽን ስትለብሽ ወፎች የሚዘፍኑት
የሚሉት ምንድነው? ጡቶችሽን አይተው
በፍቅርሽ ሰላምታ ልቤን እንዲያክሙት ላኪያቸው ያምጡልኝ፤
መድኃኒቱን ይስጡኝ፡፡ ኮከቦች ከሰማይ ይጠቃቀሳሉ
ውበትሽን አይተው፤
በቅርጽሽ ተደንቀው።
በሰማዩ ባሕር ጠልቀው ይዋኛሉ
ፍቅርሽን ሊይዙ
ወደኔ ሊጓዙ፡፡
ምን አለች ጨረቃ በመስኮትሽ ገብታ
ስትነካ ፊትሽን፤ ተደግፋ አልጋሽን፡፡
ልኬልሽ ነበረ የፍቅር ሰላምታ ጠይቂአት ውሰጂ፤
መልሱንም ስደጂ፡፡
የቤተ ክርስቲያን ደወሉ ዘመረ ምን ሆኖ ይጮኻል?
ሰው ይሰበሰባል።
ጉዳችንን አይቶ ገልጦ ተናገረ
እባክሽ ለፍቅር ሞተን እንቀበሮ፣
ምነው ምን ፈለገ ሲጨፍር ከበሮ?
ተነሣ የሚለኝ? የሚቀሰቅሰኝ፡፡
ፍቅርሽና ፍቅሬን በመሐረም አስሮ እንሒድ ተቃቅፈን፤
ደብቆ ይውሰደን፤
የበረረው ልቤ ካጠገቤ ጠፍቶ ምን ምሥጢር አወራ?
ደንግጦ እየፈራ፡፡
ስታንጎራጉሪ መኝታሽ ቤት ገብቶ የፍቅሬን ሰላምታ
ይስጥሽ በቀስታ፡፡ከታሪኩ ረጋሳ❤️❤️


>>Click here to continue<<

ግጥም ለሚጠማዉ




Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)