TG Telegram Group & Channel
ኢትዮ GENIUS 👑 | United States America (US)
Create: Update:

«አስተናጋጅ!»

“ኧረ አይባልም! ”

«እናት... እናቱ! »

“ሆ ሆ... አንድ ፍሬ ልጅ ናት ! ብትወልድ ታደርሳታለህ። አታፍርም? ”

ግራ እጄን ሰቅዬ እንድታየኝ ማውለብለብ... ጀመርኩ።

“ ኧረ እጅህን አውርድ። ይሄ የትምህርት ቤት አመልህ አለቀቀህም? በስተርጅና እጅ ሰቅለህ ቲቸር ቲቸር ? ኧረ እንደ እድሜህ ሁን ... ”

ላጨበጭብ እጄን አዘጋጀሁ።

“ነውር ነው ! አይጨበጨብም! የሰለጠነው ዓለም ቢሆን በጋርድ ገፍትሮ ያስባርርሃል...”

«እንዴ? ታዲያ ምን ላድርግ? »

“እስክታይህ ጠብቃት...”

ጥብቅቅቅቅቅ።
እስከ ምናምን ጉዳይ ለምናምን ሰዓት ድረስ...

ሰለቸኝ።

«ልታየኝ አልቻለችም! ወይ ላጨብጭብ ... ወይ ሄጄ ልጥራት ወይ እንውጣ»

“ታገስ!”

ትግስስስስስስስ
እስከ ምናምን ሰዓት ከሩብ ድረስ...

ተውኳት...
ረሳኋት...
የት እንዳለሁ፣ ምን እንደምፈልግ፣ ለምን እንደምጠብቅ... ከማን ጋር እንደተቀመጥኩ ረሳሁ። ረሳሁና በሀሳብ ጠፋሁ። ድንገት ቀጭን ድምፅ ቀሰቀሰኝ...

«ምን ልታዘዝ? »

ቀና ብዬ አየኋት። አየሁና ከአፌ ይወጣል ብዬ ያልጠበኩት ቃል ወጣኝ

«ይቅርታ... ትንሽ መቆየት ፈልጌ ነበር!»

ፈገግ ብላ ዞራ ስትሄድ፣ ያመለጡኝን ቃላት ለማፈን በሚመስል የዘገየ ችኮላ እጆቼን አፌ ላይ ደፈንኳቸው። ዞር ዞር አልኩ። ብቻዬን ነኝ። ማን ነበር ታዲያ ቅድም ሲሞግተኝ የነበረው? ማንም አልነበረም። ብቻዬን ነበርኩ።

ዝም አልኩ... በዝምታ ግን አስተማረኝ።

የምፈልገውን አላውቅምና ... ኮተት ለመጠየቅ ስሙን በከንቱ አልጠራውም። እንዲታዘዘኝ ብዬ “አባ!” “አባቴ!” አልለውም። ሁሉን ማየቱን ክጄ፣ እንዲያየኝ ብዬ እጄን በከንቱ ወደላይ አልሰቅልም፣ ትኩረቱን ለማግኘት ብዬ እጆቼን አላውለበልብም። ጆሮውን ወደኔ እንዲያዘነብልልኝና ፍላጎቴን ሰምቶ እንዲያሟላልኝ ብዬ አላሸበሽብም አላጨበጭብም። በራሱ ጊዜ እስኪያየኝ ልታገስ በሚል የተጠናና የተሸመደደ ጥበቃ... ከልብ ባልሆነ ትዕግስት ባለሁበት ተቸክዬ.. ልብና ኩላሊት የሚመረምረውን አልፈታተነውም።

ስጠራው ቢመጣ ምን እንደማዝዘው አላውቅም። ምን እንደምጠይቀው አላውቅም። ነዝንዤው «አቤት? ምን ልታዘዝ?» ቢለኝ ይሄኔ መልሴ «ይቅርታ... ትንሽ መቆየት ፈልጌ ነበር!» ሊሆን ይችላል።... የማላውቀውን እንዴት ልምረጥ? ያልገባኝን እንዴት ልጠይቅ? ዝም እላለሁ።

በክብር ስሙ ብጠራውም ፣ በፍቅር ስሙ ብጠራውም፣ እጄን ብሰቅልም፣ ባውለበልብም፣ ባጨበጭብም ከእንግዲህ ለማዘዝ አይደለም.. በዝምታ ለማውጋት...

Forwarded from Red-8

>>Click here to continue<<

ኢትዮ GENIUS 👑

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)