TG Telegram Group & Channel
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት | United States America (US)
Create: Update:

ውጤታማ የተልዕኮ አፈፃፀማችንን የሥነ ምግባር ጥሰትን ፣ ብልሹ አሠራር እና ሙስናን በመከላከል  ልንደግም ይገባል
     ሌተናል ጄኔራል አጫሉ ሸለመ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሰኔ 21 ቀን 2017 ዓ.ሞ

የመከላከያ ሥነ ምግባር መከታተያ ዳይሬክቶሬት ከሁሉም የተቋሙ ክፍሎች የሥነ ምግባር መከታተያ አመራሮች ጋር ዓመታዊ የሥራ አፈፃፀም  ውይይት አድርጓል።

በማጠቃለያው መርሀ ግብር በክብር እንግድነት የተገኙት የመከላከያ ሰው ሃብት አመራር ዋና መምሪያ ሀላፊ ሌተናል ጄኔራል አጫሉ ሸለመ ዳይሬክቶሬቱ ተቋሙና ሠራዊቱ የሥነ ምግባር ስህተትንና ብልሹ አሠራርን እየታገለ ተልዕኮውን በብቃት እንዲወጣ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው ብለዋል ።

ሠራዊቱ የሀገራዊ ተልዕኮው ውጤታማነትን በሥነ ምግባር ክፍተት ፣ ሙስናና ብልሹ አሠራርን በመታገል መድገም ይገባል ያሉት ጄኔራል መኮንኑ ቀጣይም በሥልጠና ፣ በሃብት ምዝገባና በሌሎችም የተገኘውን ውጤትና ዕውቀት በማካፈል በቅንነትና በታማኝነት ሀገርን ማገልገል እንደሚገባ አሳስበዋል።

ሁሉም የተቋሙ አባላት የሙስና ወንጀሎችን በማወቅ ሀገርንና ተቋሙን ከሙስና ስጋት መጠበቅ የሚችልና አምርሮ የሚጠላ በማድረግ ቀጣይም ተልዕኮውን
ለመፈፀም እንጥራለን ብለዋል የመከላከያ ሥነ ምግባር መከታተያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮሎኔል አዲሱ ሽፈራው ።

ኮሎኔል አዲሱ ዳይሬክቶሬቱ በሥልጠና ፣ በሃብት ምዝገባና በሌሎች ላገኘው ውጤት ድጋፍ ላደረጉ የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን እና ለተቋሙ ክፍሎች ምስጋና አቅርበው ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት የመስራቱን ሂደት እንደሚያጠናክሩም ተናግረዋል።

የመከላከያ ሥነ ምግባር መከታተያ ዳይሬክቶሬት በበጀት ዓመቱ ድጋፍ ላደረጉና የተሻለ የሥራ አፈፃፀም ለነበራቸው ክፍሎች እውቅናና ሰርተ-ፊኬት አበርክቷል።

ዘጋቢ ቃለእግዚአብሔር ፍቃዱ
ፎቶግራፍ ፉራ አብደላ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://hottg.com/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

>>Click here to continue<<

FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)