TG Telegram Group & Channel
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት | United States America (US)
Create: Update:

ኢትዮጵያና አሜሪካ በሠላምና በፀጥታ ጉዳይ በጋራ የመስራት ልምዳቸውን አጠናክረው ይቀጥላሉ።
   ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሰኔ 13 ቀን 2017 ዓ.ም

የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ የአሜሪካ በአፍሪካ ዕዝ አዛዥ  (አፍሪኮም)  ጀነራል ሚካሄል ላንግሌይ የተመራ ልዑክን ተቀብለው አነጋግረዋል።

አሜሪካና ኢትዮጵያ ከመቶ ዓመት በላይ ግንኙነት እንዳላቸው የገለፁት ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ  ጁላ ሁለቱ ወዳጅ ሀገራት በመከላከያ ዘርፉ በቀጣይም በጋራ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መግባባት መድረሳቸውን ገልፀዋል።

በውይይቱ በቀጠናው ባለው ሁኔታ የጋራ መግባባት የተያዘበትና በተለይም በቀይ ባህር ፣ በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ በሚታዩ የፀጥታ ጉዳዮች ላይ  ለጋራ ተጠቃሚነት በጋራ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ  መስማማታቸውን ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ተናግረዋል።

የአፍሪኮም አዛዥ ጀነራል ሚካኤል ላንግለይ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድና በቀጠናው ከፍተኛ ሚና ያላት ሀገር መሆኗን  ጠቅሰው፣ በተለይም በሶማሊያ ሰላምን ለማስፈንና ሽብርተኝነትን ለመዋጋት  እያደረገች ላለው ጥረት ያላቸውን አድናቆት ገልፀዋል።

በውይይታቸው በቀጠናው ያለውን ሁኔታ በግልፅ  መረዳታቸውን የገለፁት ጀነራል ሚካኤል ላንግሌይ በቀጣይም በወታደራዊና በፀጥታ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን ተናግረዋል።

በውይይቱ ላይ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋን ጨምሮ ከፍተኛ የኢትዮጵያና የአሜሪካ ወታደራዊ አመራሮች ተገኝተዋል።

ዘጋቢ ብዙአየሁ ተሾመ
ፎቶግራፍ ገነት  አወቀ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://hottg.com/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

>>Click here to continue<<

FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)