TG Telegram Group & Channel
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት | United States America (US)
Create: Update:

በኢትዮጵያ የፈረንሳይ ወታደራዊ አታሼ የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲን ጎብኝቷል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጥር 24 ቀን 2017 ዓ.ም

በኢትዮጵያ የፈረንሣይ ወታደራዊ  አታሼ ኮሎኔል ፕሊሲየር በዛሬው እለት ከቡድናቸው ጋር በመሆን የሁለትዮሽ ወታደራዊ ትብብርን ማሳደግ በሚያስችል አግባብ የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ እየሰጠ የሚገኘውን የትምህርት ፣ የስልጠና እና የምርምር ፕሮግራሞች ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ኮማንዳንት ብርጋዲየረ ጀኔራል ከበደ ረጋሳ ከቡድኑ ጋር ጠንካራ ውይይት በነበራቸው ቆይታ ዩኒቨርሲቲው ከፈረንሳይ ጋር ያለውን ዘርፈ ብዙ አጋርነት በተለያዩ ትብብሮች ላይ በተግባር ለማጠናከር ሰፊ ፍላጎት እንዳለው በስፋት አስረድተዋል።

ሃገራቱ በረዥም ጊዜ እና በአጭር ጊዜ የአካዳሚክ ስልጠናዎች ላይ ትኩረት አድርገው በመስራት የትምህርት ተቋማቶችን፣ የተማሪዎችን እና የሰራተኞችን የልምድ ልውውጥ ማጎልበት የሚችሉ የትብብር ፕሮግራሞችን በጋራ ቢተገበሩ ውጤታቸው ጠቃሚ እንደሚሆንም ኮማንዳንቱ አስገንዝበዋል።

ሃገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን በትምህርት ዘርፍ ላይ አጠናክረው በመቀጠል በዩኒቨርሲቲው የተጀመረውን የፈረሳይኛ ቋንቋ ስልጠናን ማሳደግ የሚችሉ ደረጃቸውን የጠበቁ የመማሪያ ክፍሎችና ዘመናዊ ላብራቶሪዎች እንደሚያስፈልጉም አመላክተዋል።

የፈረንሳይ ወታደራዊ አታሼ ኮሎኔል ሴፓስቲን ፕሊሲየር በውይይቱ የፈረንሳይ መንግስት የኢትዮጵያን ወታደራዊ ሃይል በትምህርትና ስልጠና ለመደገፍ ያለውን ቁርጠኝነት በማረጋገጥ ሃገራቸው ከዩኒቨርሲቲው ጋር ያላትን ትብብር ለማስፋት የፈረንሳይኛ ቋንቋ ስልጠና ፕሮግራሞችን በዘመናዊ መሳሪያዎች ለማጎልበት እየሰራች መሆኗን ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ የፈረንሳይ ኤምባሲ የፈረንሳይኛ ቋንቋ አስተባባሪ የሆኑት ሜጀር አርናዉድ ሪምበርት በበኩላቸው በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ወታደራዊ ግንኙነት ለማሳደግ የቋንቋ ክህሎት ያለውን ጠቀሜታ በማጠናከር በዩኒቨርሲቲው ለፈረንሳይኛ ቋንቋ ማሰልጠኛ ፕሮጀክት የተለያዩ ድጋፎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አብራርተዋል ።

ቡድኑ ጠንካራ ውይይት ካደረገ በኋላ የፈረንሳይኛ ቋንቋ ማሰልጠኛ ኮምፒዩተሮች ፣ ላብራቶሪዎች እና የመማሪያ ክፍሎችን ተዘዋውሮ ተመልክቷል ።

ዘጋቢ በላይነህ ፈንቴ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https:///channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://hottg.com/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

👍2221🔥2

>>Click here to continue<<

FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)