#ሰኔ_30 #ልደቱ_ለዮሐንስ መጥምቅ
ወብዙኃን ይትፌሥሑ በልደቱ ( በመወለዱ ብዙዎች ደስ ይላቸዋል) ሉቃ 1 ፥14
የኤልሳቤጥም የመውለጃዋ ጊዜ ደረሰ ወንድ ልጅም ወለደች። ወንድ ልጅም ወለደች ። ጎረቤቶቿም ዘመዶቿም ጌታ ምህረቱን እንዳገነነላት ሰምተው ከእርሷ ጋር ደስ አላቸው
በስምንተኛውም ቀን ሕጻኑን ሊገርዙት መጡ ፤ በአባቱም ስም ዘካርያስ ሊሉት ወደዱ ፤ እናቱ ግን መልሳ አይሆንም #ዮሐንስ ይባል እንጂ አለች ። እነርሱም ከወገንሽ ማንም በዚህ ስም የተጠራ የለም አሏት ፤ አባቱንም ማን ሊባል እንደሚወድ ጠቀሱት ፤ ብራናም ለምኖ ስሙ #ዮሐንስ ነው ብሎ ጻፈ። ሁሉም አደነቁ ፤ ያን ጊዜም አፉ ተከፈተ አንደበቱም ተፈታ
#ዮሐንስ_ማለት ፦ ጸጋ እግዚአብሔር ማለት ነው። ከእግዚአብሔር የተሰጠ ምሕረት ፣ ጸጋ ፣ ደግነት ፣ ባለሟልነት ፣ ውበት እንደ ማለት ነው።
" እስመ መካን ወለደት ሰብዐ ( መካኒቱ ሰባት ወለደች )
1ኛ ሳሙ. 2 ፥ 5 / በማለት የነቢዩ ሳሙኤል እናት መዘመሯ ለጊዜው ስለ ልጇ የተናገረቸው ሲሆን ፍጻሜው ግን መካኒቱ ኤልሳቤጥ ባለ ሰባት ፍሬ መልካም ዛፍ ቅዱስ ዮሐንስን አበቀለች ስትል ነው። አንድ ሰው አጣሁ ብላ ያዘነችውን ኤሌሳቤጥን የሰባት ክብር ባለቤት ፣ ሰባት ልጅ የመውለድ ያህል ደስታ ያለው ዮሐንስን ሰጣት ጥቂት ሲለምኑት ብዙ መስጠት ለእግዚአብሔር ልማዱ ነው ማለት ይህ ነው
#ሰባቱ_ክብር የተባሉትም
ነቢይ ፣ ሐዋርያ ፣ ባሕታዊ ፣ ሰማዕት ፣ ጻድቅ ፣ መምሕር ፣መልአክ
በጣፋጭ አንደበቱ ወንጌልን የሚሰብክ ፣ ቀኙ የሚያቃጥል መለኮትን የዳሰሰች ፣ ጀርባው በግመል ጠጉር የተሸፈነ ፣ የዮሐንስን ደግነት ፈጽመን እንናገራለን
/ ድጓ ዘዮሐንስ /
ለመቀላቀል👇👇👇
@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
>>Click here to continue<<
