እርምጃ ውሰዱ እንጂ !!!
አንድ ሰው አጠገቡ ለነበሩ ሰዎች በጨዋታ መልክ እንዲህ ሲል ጥያቄን አቀረበ፡-
“በአንድ መሬት ላይ በተጋደመ ትልቅ ግንድ ላይ ሶስት እንቁራሪቶች በመደዳ ቆመው ነበር፡፡ አንደኛዋ እንቁራሪት ቆመው ከነበረበት ግንድ ላይ ወደ መሬቱ ለመዝለል ወሰነች፡፡ ስንት እንቁራሪቶች ግንዱ ላይ ቀሩ?”
ይህንን ጥያቄ የሰሙት በሙሉ መልሳቸው፣ “ሁለት” የሚል ነበር፡፡ ሰውየውም መልሳቸው ትክክል እንዳልሆነ ገለጸላቸው፡፡ “አንዷ እንቁራሪት የመዝለል ውሳኔ አደረገች እንጂ አልዘለለችም፡፡ ስለዚህ አሁንም የቀሩት ሶስት እንቁራሪቶች ናቸው” ነበር ማብራሪያው፡፡
“አያችሁ”፣ አለ በመቀጠልም፣ “ይህ የሚያመለክተው ውሳኔን ከተግባር ጋር የማምታታት ዝንባሌያችንን ነው፡፡ አንድ ውሳኔ ወደተግባር እስኪለወጥ ድረስ ከውሳኔው በፊት ከነበርንበት ሁኔታና ደረጃ ትንሽም እልፍ አያደርገንም”፡፡ አብዛኛውን ጊዜ አንድን ነገር ለማድረግ ብዙ ካወጣን፣ ካወረድንና ከወሰንን በኋላ ልክ እንዳደረገ ሰው ኑሯችንን እንቀጥላለን፡፡ ውሳኔ ግን ያው ውሳኔ እንጂ ተግባር ማለት አይደለም፡፡
ለዚህ አይነቱ አደገኛ ልምምድ አጋልጠው ከሚሰጡ ሁኔታዎች መካከል . . .
1. ፍርሃት
አንድን ነገር ገና ሳንጀምረው፣ “ባይሳካስ” የሚል ፍርሃት የሚያጠቃን ከሆነ፣ ሁኔታው ቢሳካ የምናገኘውን ጥቅም ሳይሆን ባይሳካ የሚደርስብንን ጉዳት፣ ሃፍረትና የመሳሰሉት ነገሮች ነው የምናሰላስለው፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ ያሰብነውን ነገር ከመጀመር ይገታናል፡፡
መፍትሄው፡- ጥንቃቄ በተሞላው እና ትርፍና ኪሳራን ባመዛዘነ መልኩ ፍርሃትን መጋፈጥ ነው፡፡
2. ለነገ አስተላላፊነት
ለነገ የማስላለፍ ልማድ አንዳንድ ጊዜ ከፍርሃት ጋር ቢገናኝም ሌሎች ምክንያቶች ግን አሉት፡፡ ለምሳሌ፣ ለመጀመር ባሰብነው ነገር ላይ በቂ ክህሎት እንደሌለን ማሰብና በራስ አለመተማመን፣ የዲሲፕሊን ችግር፣ የሰዎችን ሃሳብ እየሰሙ ሃሳብን መለዋወጥ፣ በወቅቱ ስሜትና “ሙድ” ተጽእኖ ስር መውደቅ እና የመሳሰሉት፡፡
መፍትሄው፡- አንድን ነገር እንድናስተላለፍ የሚያደርግን ችግራችን ምን እንደሆነ መለየትና በማንበብ፣ በመሰልጠንና በመሳሰሉት መንገዶች መቅረፍ፡፡
3. ዓላማ ቢስነት
አንድ ለመጀመር ወይም ለማድረግ የምንፈልገው ነገር በመጨረሻ ከአንድ ማከናወን ከምንፈልገው ዋና ዓላማ ጋር የተነካካ ካልሆነ በውስጣችን ግለትና ጉጉት ስለሚጎድለን እርምጃን የመውሰድ አቅም አይኖረንም፡፡ ይህ የሚሆንበት ምክንያት ዋነኛው የመነቃቃት (Motivation) ምንጭ የሕይወት ዓላማ ማወቅ ስለሆነ ነው፡፡
መፍትሄው፡- የምናደርጋቸውን ነገሮች በሙሉ ከዋናው የሕይወታችን ዓላማ ጋር ወይም ከአንድ ወሳኝ ግብ ጋር መያያዙን እርግጠኛ መሆን፡፡
https://hottg.com/Dreyob
https://m.youtube.com/user/naeleyob623
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
>>Click here to continue<<
