TG Telegram Group & Channel
Dr. Eyob Mamo | United States America (US)
Create: Update:

ሌሎች ሰዎች በእናንተ ውስጥ ሲኖሩ!

ሌሎች ሰዎች በእናንተ ውስጥ እየኖሩ እንደሆነ ለማወቅ . . .

• የእናንተና የእነሱ ግንኙነት አልቆለት እንኳን፣ ትምህርትና ስራ ላይ ማተኮር እስከማትችሉ ድረስ በፍጹም መርሳት የማትችሏቸው ሰዎች ካሉ፤ ሰዎቹ በእናንተ ውስጥ እየኖሩ ነው፡፡

• ጥቃቅን ውሳኔዎችን እንኳን ሳይቀር ከእነሱ ውጪ ምንም አይነት ውሳኔ ማድረግ የማትችሏቸው ሰዎች ካሉ፤ ሰዎቹ በእናንተ ውስጥ እየኖሩ ነው፡፡

• እነሱ ለሚሰማቸው ስሜትና ከዚያ ስሜታቸው ጋር በየቀኑ ለሚለዋወጠው በህሪያቸው የጥፋተኝነትን ስሜት የምትሸከሙት እናንተ ከሆናችሁ፤ ሰዎቹ በእናንተ ውስጥ እየኖሩ ነው፡፡

• እነሱና እናንተ ብቻ የምታውቁትን “አሳፋሪ” ወይም “አስፈሪ” ምስጢራችሁን እንዳያወጡባችሁ ስትሉ መንቀሳቀስ እስከማትችሉ ድረስ በእነሱ ቁጥጥር ስር ያደረጓችሁ ሰዎች ካሉ፤ ሰዎቹ በእናንተ ውስጥ እየኖሩ ነው፡፡

• ላጠፉት ጥፋት ተገቢውን ይቅርታ አድርጋችሁ ወደፊት ከመሄድ ይልቅ ቂም የያዛችሁባቸው ሰዎች ካሉ፤ ሰዎቹ በእናንተ ውስጥ እየኖሩ ነው፡፡

• በሰራችሁት ጥፋት ምክንያት ሰዎች ይቅርታ ነፍገዋችሁ ቂም ስለያዙባችሁ ብቻ ካለማቋረጥ በጭንቀት ውስጥ የምትኖሩ ከሆነ፤ ሰዎቹ በእናንተ ውስጥ እየኖሩ ነው፡፡

ፈጣሪ የራሳችሁን ሕይወት የሰጣችሁ እናንተው እንድትኖሩት እንጂ ሌላው ሰው በውስታችሁ ሆኖ እንዲኖር አይደለምና የሚከፈለውን ዋጋ ከፍላችሁ ተገቢውን ማስተካከያ አድርጉ፡፡ አለዚያ የእድሜ ልክ ዋጋ ትከፍላላችሁ፡፡

https://hottg.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

>>Click here to continue<<

Dr. Eyob Mamo

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)