የስኬታማ አጋርነት ምስጢር!
በማንኛውም መስክ ውስጥ ከአንድ ሰው ጋርም ሆነ ከአንድ ሕብረተሰብ ጋር ስኬታማ፣ የጠለቀና ዘላቂ የሆነን አጋርነት ከፈለጋችሁ ምስጢሩ ሁለት ነው፡-
1) በጋራ የምተወዷቸውና አጥብቃችሁ የምትከታተሏቸው ነገሮች ሲኖሩ፣
2) በጋራ የምትጸየፏቸውና አጥብቃችሁ የምትርቋቸው ነገሮች ሲኖሩ፡፡
እንደ ንግድ አጋሮች አብረን የምንበለጽገው፣ እንደ ባለትዳሮች አብረን ውብ የሆነን ቤተሰብ የምንመሰርተው፣ እንደ አንድ ሃገር ዜጎች አብረን የምንቀጥለውና የምናድገው፣ በጋራ የምወዳቸውና በጋራ የምንጠላቸው ሁኔታዎች ሲበዙልን ነው፡፡
አስቡት እስቲ፡- መሪዎቻችን በሙሉ በጋራ ለሰለጠነ ሕብረተሰብ መስራትን ቢወዱና ያንንም ቢከታተሉ! መሪዎቻችን በሙሉ በጋራ አንድነትንና እኩልነትን ቢወዱና ያንን ቢከታተሉ . . . አስቡት!
አስቡት እስቲ፡- መሪዎችን በሙሉ በጉቦ (ሙስና) ላይ የጋራ ጥላቻ ቢኖራቸውና ያንንም ቢሸሹ! መሪዎቻችን በሙሉ በዘረኝነት ላይ የጋራ ጥላቻ ቢኖራቸውና ያንንም ቢርቁ . . . አስቡት!
የዚህ እውነት ተግባራዊነት በትዳር፣ በንግድና በራእይ አጋርነት ውስጥም ቢሆን ያው ነው፣ አይለወጥም!
አብረን በጋራ የምንወዳቸውና የምንከታተላቸው፣ እንዲሁም አብረን በጋራ የምንጸየፋቸውና የምንሸሻቸው ነገሮች በበዙ ቁጥር እድገታችን ፈጣን ይሆናል፡፡ እነዚህ ሁለት ነገሮች ሲዥጎረጎሩና ሲዛቡ፣ የሕብረተሰቡ እድገትም ከዚያው ጋር አብሮ ይዛባል፣ ይጎተታል፡፡
https://hottg.com/Dreyob
https://m.youtube.com/user/naeleyob623
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
>>Click here to continue<<
