“የእባብ ማሳደድ” ውጤት (The snake chasing effect)
እንዲህ የሚል አባባል አለ፡-
አንድ ሰው በሚያሳዝን ሁኔታ በመርዛማ እባብ ቢነደፍ ያለው አማራጭ ሁለት ነው፡፡ አንደኛው፣ የነደፈውን እባብ ተከታተሎ በመግደል ለመበቀል መሞከር ሲሆን፣ ሁለተኛው መርጫው ደግሞ በመጀመሪያ ለቁስሉ ትኩረት በመስጠት መርዙ እንዳይጎዳው ለራሱ አስፈላጊውን ክትትል ማድረግ ነው፡፡
እኛን የነደፈው እባብ ሌሎችን እንዳይነድፍ ከማድረግ አንጻርና ከመሳሰሉት አመለካከቶች (logic / አመክንዮ) አንጻር ብዙ የመወያያ ሃሳቦች ማምጣት የመቻላችን እውነታ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ሊቀድም የሚገባው ግን ምን እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡
በምንም ዓይነት ሁኔታም ሆነ በየትኛውም ሰው ስትጎዱ ለበቀልና አጸፋ ለመመለስ ከመንቀሳቀሳችሁ በፊት ለራሳችሁ የመጠንቀቃችሁን ጉዳይ ቅድሚያ ስጡ፡፡
ይህንን ስታደርጉ . . .
1. ለሆነባችሁ ነገር ሁሉ አጸፋ ለመመለስ ስትሯሯጡ ራሳችሁን ከማከም ችላ በማለታችሁ ምክንያት ከሚመጣ ጉዳት ትጠበቃላችሁ፡፡
2. ለሆነባችሁ ነገር ሁሉ አጸፋ ለመመለስ ስትታገሉ ከዋናው ዓላማችሁ መስመር ትወጣላችሁ፡፡
3. ይህ አይነቱ ምላሽ ሰጪነት መነሻው ስሜታዊነት በመሆኑ፣ ከዚያኛው ወገን ሌላ ስሜታዊ ምላሽን ሊወልድ ስለሚችልና የዑደቱ መጨረሻ ስለማይታወቅ ላልተጠበቁ ውጤቶች ራሳችሁን ታጋልጣላችሁ፡፡
በመጀመሪያ ራሳችሁን ጠብቁ፡፡ ሲቀጥል፣ በቅድሚያ ራሳችሁን አክሙ፡፡
መልካም ቀን!
https://hottg.com/Dreyob
https://m.youtube.com/user/naeleyob623
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
>>Click here to continue<<
