TG Telegram Group & Channel
Dr. Eyob Mamo | United States America (US)
Create: Update:

ነጻ የሆነ ሕይወት !!!

ወደ እናንተ የሚሳቡትን ሰዎች የሚወስነው በራሳችሁ ላይ ያላችሁ አመለካከትና ከዚያ አመለካከታችሁ የተነሳ የምታንጸባርቁት ሁኔታ ነው፡፡

1. ራሳችሁን ከሆናችሁት በላይ ማሰብና ያንን ማንጸባረቅ

ይህ ሁኔታ የሌላችሁን ማንነትና ስኬት እንዳላችሁ በማሳየታችሁ ምክንያት ያንን የሌለ ነገር ለማግኘትና ለመጠቅም የሚፈልጉ ሰዎች ወደ እናንተ እንዲቀርቡ ያደርጋቸዋል፡፡ የዚህ ሁኔታ መጨረሻው ያልሆናችሁትንና የሌላችሁን ነገር ፈልገው ከመጡ ሰዎች ጋር ወራትና ዓመታት ካሳለፋችሁ በኋላ እንደገና ከዜሮ መጀመር ነው፡፡ ይህ ደግሞ የክስረት ሁሉ ክስረት ነው፡፡

2. ራሳችሁን ከሆናችሁት በታች ማሰብና ያንን ማንጸባረቅ

ይህ ሁኔታ ከማንታችሁ፣ ካላችሁና ከምትችሉት በታች ሆናችሁ ራሳችሁን በማቅረባችሁ ምክንያት ሕይወታችሁን እንደፈለጉ ለማድረግ እንደሚችሉ የሚያስቡና ያንን የሚፈልጉ ሰዎች ወደ እናንተ እንዲሳቡ ያደርጋቸዋል፡፡ የዚህ ሁኔታ መጨረሻው ብዙ ነገር ማከናወን የሚችለው ማንነታች በሰዎች ቁጥጥር ስር ሆኖ በከንቱ የማለፉና ከአቅሙ በታች የመኖሩ ሁኔታ ነው፡፡

3. ራሳችሁን በሆናችሁት መጠን ማሰብና ያንን ማንጸባረቅ

ይህ ሁኔታ ትክክለኛውን ማንነታችሁን፣ ያላችሁበትን ደረጃና የተሳካውንም ሆነ ያልተሳካውን በትክክል አይተው ከነማንነታችሁ የሚቀበሏችሁን ትክክለኛ ሰዎች ወደ እናንተ እንዲሳቡ ያደርቸዋል፡፡ የዚህ ሁኔታ መጨረሻው ከሩቅ ሲያዩዋችሁና በቅርብ ሲያገኟችሁ አንድ አይነት ሁኔታን በማግኘታቸው ምክንያት በእናንተ ላይ ትልቅ አመኔታን ይዘው የሚነሱ ሰዎችን መሳብ ነው፡፡ ይህ ግንኙት ዘላቂና ስኬታ ግንኙነቶች የሚጀመሩበትና ወደፊት የሚዘልቁበት አይነት ግንኙነት ነው፡፡

የራስ በራስ ጥያቄ!

• በማሕበራዊ ሚዲያ ራሴን አቅርቤ የምታወቅበትና ሰዎቹ በአካል ቢያገኙኝ ሊያዩት የሚችሉት ሁኔታ ክፍተት አለው?

• ስለማንነቴም ሆነ ስላለኝ ነገር የምናገረውና በእርግጥም የሆንኩትና ያለኝ ነገር ልዩነት አለው?

• ሰዎች በቀረቡኝና ባወቁኝ መጠን ይንቁኛል ብዬ በማሰብ የምሸማቀቅበት ሁኔታ አለኝ?

ሰዎች ላልሆናችሁት ማንነት ከሚወዷችሁና ለሌላችሁ ነገር ከሚቀርቧችሁ፣ በእውነተኛው ማንነታችሁ ቢጠሏችሁና ባላችሁበት የሕይወት ደረጃችሁ ምክንያት ቢርቋችሁ ይሻላችኋል፡፡

እንዴት ያለ ነጻ የሆነ ሕይወት !!!

https://hottg.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

>>Click here to continue<<

Dr. Eyob Mamo

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)