በገንዘብ እንዳናድግ የሚያደርጉን አመለካከቶች
በገንዘብ አቅም የማደግ ሁኔታ ከምንም ነገር ጋር ከመነካካቱ በፊት ከአመለካከታችን ጋር ይነካካል፡፡ በምንም የኑሮ ደረጃ ላይ ብንሆን፣ አመለካከታችንን ጤናማና ሚዛናዊ አደርገን ከጀመርን ቀስ በቀስ ማደጋችን አይቀርም፡፡
ለዛሬ ሶስቱን ልጥቀስ . . .
1. የገንዘብ ጉዳይ ከእድል ጋር እንደሚገናኝ ማሰብ፡፡
ልክ ነው! ሰዎች በአጋጣሚም እንበለው በእድል ገንዘብን ሊያገኙ ይችላሉ፡፡ ያንን ያገኙትን ገንዘብ ግን እንዴት መጠቀም፣ ማባዛት፣ መቆጠብና ኢንቨስት ማድረግ ካላወቁበት ተመልሰው መከሰራቸው አይቀርም፡፡
2. ሰዎች ሃብታም የሆኑት ሌላውን በመጨቆ እንደሆነ ማሰብ፡፡
ልክ ነው! አንዳንድ ሰዎች በተዛባ መንገድም ሆነ ሌላው በመጨቆን ሃብታም ሆነው ሊሆን ይችላል፡፡ ሆኖም፣ ምንም እንኳን በሌብነትና በተንኮል የገንዘብ ሃብትን ቢያገኙም፣ ያላቸው የባህሪይ ድህነት ጊዜ ጠበቆ ወደታች እንደሚያወርዳቸው ግልጽ ነው፡፡
3. በገንዘብ የማደግ ፍጎት ትክክል እንዳልሆነ ማሰብ፡፡
ልክ ነው! ማሕባዊ እሴቶቻችን እና ኃይማኖታችን በገንዘብ ላይ ጥንቃቄ እንዲኖረን ያስተምሩናል፡፡ ሆኖም፣ ገንዘብን የማግኘት ሂደት በትክክለኛው መንገድ ከተያዘ ጥቅሙ እጅግ የላቀ እንደሆነ ማሰብ አለብን፡፡
“ታዲያ ትክክለኛው አመለካከት ምንድን ነው?” ለምትሉ መንገዱን የሚያመላክታችሁ ስልጠና ተዘጋጅቶላችኋል
የስልጠው ርእስ፡- “የገንዘብ አስተዳደር ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Money Management Skills and Discipline)
ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ
ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)
የስልጠናው ቀናት፡- ሰኔ 19, ሰኔ 26፣ ሐምሌ 3, ሐምሌ 10 እና ሐምሌ 17 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)
የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)
የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል
@DrEyobmamo
>>Click here to continue<<