ጀምሮ ማቆም! የብዙዎች ትግል!
ለምንድን ነው የጀመርነውን ነገር መቀጠል የሚያስቸግረን?
1. የትኩረት ችግር
አንድ ሰው የተበታተነ አሳብ ካለው አንድን ነገር ጀምሮ እንዲቀጥልና ወደፍጻሜ እንዲገሰግስ አይፈቅድለትም፡፡ በጀመረው ስራ ላይ ከማተኮር ይልቅ በየእለቱ እንደመጣው ጉዳይ ሃሳቡን ስለሚቀያይር በአንድ ነገር ላይ በመቆየት እስከጥጉ የማድረስ ብቃቱ አይኖረውም፡፡
2. እንቅፋቶችን አስቀድሞ አለማሰብ
ሊገጥሙን የሚችሉ እንቅፋቶችን እቅጩን መተንበይ ባንችልም ዋና ዋና ችግሮች አስቀድመን ማየት ግን እንችላለን፡፡ ጥንቃቄ-ተኮር ትንበያ ከጅማሬ ግለት የተነሳ አስተሳሰባችን ተጋርዶ ከመገስገስና፣ እንቅፋት ሲመጣ ከመደናገጥ ይጠብቀናል፡፡
3. በቁርጠኝነት አለመጀመር
አንድን ነገር በቁርጠኝነት መጀመር ማለት አንዴ ጀምሬዋለሁ በሚል እሳቤ በጭፍንነት ወደፊት ብቻ ማየት ማለት አይደለም፡፡ ከጀመርን በኋላ በየጊዜው ግምገማና ማስተካከያ ማድረግ አስፈላጊ ቢሆንም፣ መነሻው የቁርጠኝነት ጉድለት ሲሆን ግን ውጤቱ ክስረት ነው፡፡
4. ሰው አስደሳችነት
አንድን ነገር ከጀመርን በኋላ ለሰዎች አመለካከት፣ ስሜትና የሃሳብ ስንዘራ አላግባብ ትኩረት በመስጠት የስሜት ውጣ ውረድ ውስጥ መግባት አቅማ ያሳጣናል፡፡ አንድን ነገር ለመቀጠል ከሁሉም በፊት በጉዳዩ እኛ ማመን ይኖርብናል፡፡
ሳታስቡና ሳትዘጋጁ አትጀምሩ፣ አንዴ ከጀመራችሁ በኋላ አታቁሙ!
https://hottg.com/Dreyob
https://m.youtube.com/user/naeleyob623
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
>>Click here to continue<<
