የሙዳችሁ ጉዳይ
በሕይወታችሁ ለስኬታችሁ ወሳኝ ከሆኑ ነገሮች አንዱ የየእለት “ሙዳችሁ” ጉዳይ ነው፡፡
የየእለት “ሙዳችን” በመጠኑ ሊለዋወጥ የመቻሉ እውነታ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ቶሎ ቶሎ የሚለዋወጥ ከሆነ ሁለት ነገሮችን ይነካብናል፡-
1. ለአንድ ተግባር ያለንን መነሳሳት
2. ከሰዎች ጋር የሚኖረንን ግንኙነት
በሕይወታችን የምንሰራቸው ነገሮች “በሙዳችሁ” ምክንያት ካልተሳኩ፡፡ እንዲሁም ያለን ማሕበራዊ ግንኙነት በዚሁ “የሙድ” መዛባት ምክንያት ከተበላሸ - ምን ቀረን?
የሙዳችሁ ሁኔታ በየእቱ ሊለዋወጥ የመቻሉ እውነታ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ልኩን ጠብቆ እንዲቆይ ከፈለጋችሁ . . .
1. ከሰዎች የምትጠብቁትን (Expect የምታደርጉትን) ነገር ሚዛናዊ አደርጉ፡፡
ሰዎች ሁል ጊዜ ሰዎች ናቸው፡፡ እኛ የምንጠባበቀውን ቀርቶ ቃል የገቡትን ነገር እንኳን ላይፈጽሙት ይችላሉ፡፡ ልባችንን ሙሉ ለሙሉ ከሰዎቹ በምንጠባበቀው ነገር ላይ ከጣልን የስሜት ቀውስ የማይቀር ነው፡፡ ያለፈው ታሪካችሁን መለስ ብላች ካስታወሳችሁ፣ የብዙ የስሜት ቀውስና የተስፋ መቁረጥ መንስኤዎች ከሰዎች የምንጠብቀውን ነገር ያለማግኘታችን ጉዳይ እንደሆነ እንደርስበታለን፡፡
2. መለወጥ ወይም መቆጣጠር ከማትችሉት ነገር ላይ ትኩረታችሁን አንሱ፡፡
አንድ ነገር እንደሚሆን ካሰባችሁ ወይም ከሆነባችሁ የመጀመሪያው ሊመለስ የሚገባው ጥያቄ ያንን ነገር መቆጣጠር ወይም መለወጥ የመቻላችሁ ጉዳይ ነው፡፡ ምንም ብታደርጉ የማትለውጡት ነገር ከሆነ፣ አንደኛችሁን ትኩረታችሁን ከዚያ ነገር ላይ በማንሳት ወደ አስፈላጊው ነገር ላይ እንድታደርጉ ትመከራላቸሁ፡፡ መለወጥ የማትችሉትን ነገር ሲያብሰለስሉ መዋል መለወጥ በምትችሉት ነገር ላይ እዳትሰሩ ጉልበታችሁን ይወስደዋል፡፡
https://hottg.com/Dreyob
https://m.youtube.com/user/naeleyob623
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
>>Click here to continue<<
