አንዳንድ በነገሩ በሚገባ ያሰቡና ያጠኑ አዋቂዎች እንዲህ ይሉናል . . .
ከ20 ዓመት በታች የለጋነትና “የሞኝነት” ጊዜ ነው፡፡ ከዚሁ ጋር በገንዘብ ላይ ያለንም ግንዛቤ አናሳ ሊሆን ይችላል፡፡ ምናልባት ገንዘብን ብናገኝ ያገኘነውን ገንዘብ የምናውለው ዘለቄታ ለሌለው ነገር ሊሆን ይችላል፡፡
ከ20 ዓመት እስከ 35 ዓመት ቤተሰብን የመመስረትን ፍላጎት የምናዳብርበት ጊዜ ነው፡፡ ከዚሁም ጋር የገንዘብ ፍላጎታችንና ትኩረታችን አብሮ ይለወጣል፣ ስለወደፊትም ስለሚኖረን ኑሮ ማቀድ ወይም ደግሞ መጨነቅ እንጀምራን፡፡
ከ35 ዓመት እስከ 55 ዓመት የገንዘብ አቅማችንን የምንመሰርትበትና የምንገነባበት ጊዜ ነው፡፡ ማለትም፣ ቀድሞ ባስቀመጥነው እቅድና መሰረት ላይ በመገንባት ጠንክረን የምንሰራበትና የገንዘብ አቅማችንን የምናሳድግበት ጊዜ ነው፡፡
ከ55 ዓመት በላይ ደግሞ ቀድሞ ለፍተን በገነባነው የገንዘብ አቅምና መሰረት ላይ በመረጋጋት የምንኖርበት ጊዜ ነው፡፡ በዚህ እድሜያችን በገንዘብ ተደላድለን ካልተረጋጋን ሁኔታው ምንም እንኳን አሳሳቢ ቢሆንም ተስፋ ግን አይቆረጥም
ይህ እይታ ገንዘብን ከወቅቱ እድሜአችን ጋር በማዛመድ ማየት እንደሚገባን ይጠቁመናል፡፡
ጥያቄው ግን፣ “የገንዘብ አቅምና አቋማችንን እንዴት እንገንባ?” የሚለው ነው፡፡
በዚህ ጉዳይ ላይ በርካታ መርሆችንና መመሪያዎችን የሚሰጣችሁ ስልጠና አያምልጣችሁ፡፡
የስልጠው ርእስ፡- “የገንዘብ አስተዳደር ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Money Management Skills and Discipline)
ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ
ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)
የስልጠናው ቀናት፡- ሰኔ 19, ሰኔ 26፣ ሐምሌ 3, ሐምሌ 10 እና ሐምሌ 17 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)
የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)
የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል
@DrEyobmamo
>>Click here to continue<<