TG Telegram Group & Channel
Campus love ❤ Stories | United States America (US)
Create: Update:

......የሀዘኔ መጨረሻ .........

ክፍል 19

.....አይሆንም አሉ፡፡ ከዛን ወደ መኝታ ክፍላቸው ገቡ፡፡ ወ/ሮ ኤልሳም ተከትላቸው ገባች፡፡ እኔና ብሩኬ ብቻ ቀረን፡፡ "ሰላሜ ካንቺ መለየት አልፈልግም " አለኝ፡፡ እንባዬ ፈሰሰ ፊቴ ላይ የውሸት ፈገግታ ጣል እያደረኩበት "ብሩኬ የአባትህን ትዛዝ ማክበር አለብህ እኔ ሁሌም እጠብቅሀለው " ብዬው እየሮጥኩኝ ወደ ክፍሌ ገብቼ ማልቀሴን ቀጠልኩኝ፡፡

ያው ጊዜያቶች ሄዱ፡፡ ብሩኬ ወደ ሌላ ዮንቨርስቲ እንዲሄድ ሆነ፡፡ በጣም ነበር የከፋኝ፡፡ ብሩኬም እንደዛው፡፡ ብሩኬ እቃዎቹን ማዘገጃጀት ጀመረ፡፡ የመሄጃው ቀን አይኑን አፍጥጦ ወጣ፡፡ የደረሰው ባህር ዳር ዮንቨርስቲ ነበር፡፡

አመሻሽ ላይ ብሩኬን የሚወስደው መኪና መጣ፡፡ በፍጥነት ከክፍሌ ወጥቼ ወደ ሳሎን ሄድኩኝ፡፡ ወ/ሮ ኤልሳ ብሩኬን አቅፋ ታለቅሳለች፡፡ አቤል ሶፋው ጥግ ላይ ተቀምጦ ለንቦጩን ጥሎታል፡፡ አቶ ሄኖክ ወ/ሮ ኤልሳን ማባበል ይዘዋል፡፡ ደርቄ ቀረሁኝ፡፡ ብሩኬ ዞር ብሎ አየኝ ከማልቀሴ ብዛት አይኖቼ ቲማቲም መስለው ነበር፡፡ ወደኔ ቀረብ አለኝ አንገቴን አቀረቀርኩኝ "ሰሊ ቻው አትይኝም እንዴ " አለኝ ፡፡ ከአይኔ እንባ እየፈሰሰ ተጠመጠምኩበት፡፡ አቶ ሄኖክ በድካም ስሜት ሶፋው ላይ ቁጭ አሉ፡፡

ከብሩኬ እቅፍ መውጣት አልፈለኩም ነበር፡፡ ግን ወድያው ሹፌሩ መጣና "ዝግጁ ነኝ ጌታዮ መሄድ እንችላለን " አለ፡፡ አቶ ሄኖክም " በል ልጄ እንዳይረፍድብህ ሂድ " አሉት፡፡ እሱም ወደ መኪናው አመራ፡፡ ከአይኖቹ እንባ ጠብ ጠብ ሲል ታየኝ፡፡ ፈጣሪዬ ለምንድን ነው የምወዳቸውን ሰዎች የሚወስድብኝ ብዬ ተማረርኩኝ፡፡ ሁላችንም አቅፎን መኪናው ውስጥ ገባ፡፡ ሁላችንም እያለቀስን ነው፡፡ መኪናው መንቀሳቀስ ጀመረ፡፡ ገና ከግቢ ሳይወጣ ቆመ፡፡ ብሩኬ ከመኪናው ውስጥ ወጥቶ አቶ ሄኖክ እግር ስር ወድቆ " አባቴ እባክህ እንድሄድ አታስገድደኝ እኔ እዚሁ መማር ነው የምፈልገው፡፡ ያንተን ትዕዛዝ ላለመሻር ብዬ የማልፈልገውን ነገር እንዳደርግ አትፍረድብኝ እባክህ አባት! " አለው፡፡ አቶ ሄኖክ ራሳቸውን ያዝ አደረጉ፡፡ ወ/ሮ ኤልሳ ብሩኬን ከአቶ ሄኖክ እግር ስር እያነሳች " ሄኖክ አሁንስ አበዛኀው ልጄ ጥሩ ልጅ ነው እንደማንኛውም ሌባ አይደለም ለሁሉምለሚፈልገው ነገር ዋጋ መክፈል ያውቃል ልጄን እንደዚ ነው ያሳደግኩት ስለዚህ እዚሁ እንዲማር አድርግ እባክህ አታስገድደው " አለችው፡፡

አቶ ሄኖክም ብሩኬን አቀፍ እያደረጉ " ልጄ ታውቃለህ ላንተ የሚበጀውን ነው የምፈልገው ግን እንደማንኛውም የሀብታም ልጅ በቤተሰብህ ብር የምትመካ እንዳትሆን ብዮ ነው " አሉት ፡፡ ብሩኬም "አይዞህ አባቴ እንደዚያ አይነት ሰው አልሆንም ብቻ አንተ አታስገድደኝ" አለው፡፡ አቶ ሄኖክም "እሺ ልጄ አምንሀለው እዚሁ ትማራለህ "አሉት፡፡ ሁላችንም ፊት ላይ ፈገግታ አበራ፡፡ ተቃቀፍን፡፡ ወደ ቤታችንም ገባን፡፡ የዛን ቀን ከምታስቡት በላይ ነበር ደስያለኝ፡፡የኔና የብሩኬ ፍቅርም ጦፈ፡፡

ብሩኬም ኮሌጅ ገባ እኔም 12ኛ ክፍል ገባሁ፡፡ ብሩኬ በትምህርቱ በጣም ጎበዝ ስለሆነ ያስጠናኛል፡፡ የምር አፍቃሪ ነው፡፡ አንድ ቀን ክፍሌ ውስጥ እያስጠናኝ " ሰላሜ " አለኝ፡፡ "ወዬ " አልኩት፡፡ ትኩር ብሎ እያየኝ "በጣም እኮነው የማፈቅርሽ " አለኝ፡፡እኔም በስስት እያየሁት " እኔም በጣም አፈቅርሀለው " አልኩት፡፡ አይን ለአይን ተፋጠጥን......

ክፍል 20 እንዲቀጥል like ማድረግ አትርሱ

>>Click here to continue<<

Campus love ❤ Stories

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)