TG Telegram Group & Channel
Campus love ❤ Stories | United States America (US)
Create: Update:

........የሀዘኔ መጨረሻ .........

ክፍል 18

.......እንድገባ ነገሩኝ.......እኔም በፍርሀት ገብቼ አልጋዬ ላይ ቁጭ አልኩኝ፡፡ ኮስተር ብለው ይልማ ምንድን ነው ያደረገሽ አሉኝ፡፡ በጣም ደነገጥኩኝ "አይ ምንም" አልኳቸው፡፡ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው "አትዋሺኝ ..... እኔን እኮ እንደ አባትሽ ልታይኝ ትችያለሽ እውነቱን ንገሪኝ " አሉኝ፡፡ አንገቴን አቀረቀርኩኝ፡፡ ወድያው ብሩኬ መጣ....

"ሰላም አትፍሪ ሁሉንም ነገር ለዳድ መናገር ትችያለሽ " አለኝ፡፡ ሳስበው ይልማ ሊያደርገኝ ለነበረው ነገር ቅጣት ማግኘት እንዳለበት ተሰማኝና ሁሉንም ነገር ነገርኳቸው፡፡

አቶ ሄኖክም እቅፍ አድርገውኝ "አይዞሽ ልጄ ሁሉም ነገር ያልፋል ሊያደርስብሽ ለነበረው ጥቃት ዋጋውን ያገኛል፡፡" አሉኝ፡፡ እኔም እንባዮን መጠራረግ ያዝኩኝ፡፡

አቶ ሄኖክ " በይ ሰላም ተነሺ ወደ ፖሊስ ጣቢያ እንሂድ አሉኝ፡፡" ብሩኬም "አው ልክ ነው ተነሺ እኔም አብሬያቹ እሄዳለው " አለን፡፡ ምንም አላንገራገርኩም በፍጥነት ለባብሼ አብረን ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሄድን፡፡

እንደደረስን አቶ ሄኖክ መርማሪው ክፍል ገባ፡፡ እኔና ብሩኬም ውጪ ቆየን፡፡ ከትንሽ ደቂቃዎቾ በኀላ ወደ መርማሪው ክፍል ገባን፡፡ ተቀመጥን ከመርማሪው ጋር ከተዋወቅን በኀላ "ሰላም አቶ ሄኖክ አንዳንድ ነገሮችን ነግረውኛል አሁን አንቺ በዝርዝር ትነግሪኛለሽ" አለኝ፡፡ እኔም "እሺ" አልኩት፡፡ እስኪብርቶውን ከጠረቤዛው ላይ እያነሳ ከፊት ለፊቱ ባለው ደብተር ለመፃፍ እየቃጣ በይ አሁን ጀምሪ አለኝ፡፡ አቶ ሄኖክም "በይ ሰላም እንዳትፈሪ ሁሉንም ነገር ተናገሪ" አሉኝ፡፡ ብሩኬንም ሳየው በፈገግታ አንገቱን ነቀነቀልኝ፡፡ እኔም የሆነውን ነገር በሙሉ ለመርማሪው ተናገርኩኝ፡፡ መርማሪውም ሁሉን ነገር ከሰማ በኀላ "በሉ አሁን ወደቤታችሁ መሄድ ትችላላቹ የተቀረውን እኛ እንጨርሰዋለን" አለን፡፡ እኛም ወደ ቤት ተመልሰን ሄድን፡በሙ
እቤት እንደደረስን ወ/ሮ ኤልሳ "ይቅር በይኝ ሰላም ምንም ነገር አላወኩም ነበር እባክሽ ይቅር በይኝ " አለችኝ፡፡ እኔም "ምንም ችግር የለውም " አልኳት፡፡ አቀፈችኝ እኔም አቀፍኳት፡፡ ብሩኬና አቶ ሄኖክ ፊታቸው በፈገግታ አበራ፡፡ አቤልም መጥቶ እቅፍ አደረገኝ በጣም ተደሰትኩኝ፡፡ይልማም ተይዞ ታሰረ፡፡ መታሰሩን ሳይ በጣም ጠነከርኩኝ፡፡ ከትንሽ ቀን በኀላ ፍርድ ቤት ቀርቦ የ5 አመት እስራት ተፈረደበት፡፡

ወ/ሮ ኤልሳ ስለታሰረ ከፍቷቷል ግን ቅጣቱ እንደሚገባው አውቃለች፡፡ ከዛች ቀን ጀምሮ ሰላማዊና የተረጋጋ ህይወት ኖረኝ፡፡

በድንገት አንድ ቀን ጠዋት አቶ ሄኖክ ተነስተው ብሩክ ወደ ዮንቨርስቲ መሄድ እንዳለበት ተናገሩ ፡፡ ሁላችንም ደነገጥን፡፡ ወ/ሮ ኤልሳ ለምን ብላ ጥያቄ አቀረበች፡፡ የሳቸው መልስ የሆነውም ሳስብበት ቆይቼ እዛ ሄዶ እንዲማር ወስኛለው ምክንያቱም የህይወትን ውጣ ውረድ ማሳለፍ አለበት ሰው እንዴት ተምሮ በራሱ እንደሚቆም ማወቅ አለበት፡፡ እዚህ ከተማረ የሚጎልበት ነገር አይኖርም እሱ ደግሞ ለቀጣይ ህይወቱ ጥሩ አይሆንም አሉ፡፡

ክፍል 19 እንዲቀጥል like ማድረግ አትርሱ

CONTACT US @Juliiian

>>Click here to continue<<

Campus love ❤ Stories

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)