TG Telegram Group & Channel
ሐዋርያዊ መልሶች | United States America (US)
Create: Update:

ቅዱስ ሚካኤል

መልአክ ማለት መልእክተኛ ማለት ነው.. ስለዚህ መላእክት የእግዚአብሔር መልእክተኞች ሲሆኑ እንደሚታወቀው ሥጋ የሌላቸው መናፍስት ናቸው.. ከእነዚህም አንዳንዶች የእግዚአብሔር ዙፋኑ የተባሉ በዚያ ዙሪያ ያሉ ወደ እኛ የማይላኩ አሉ.. አጠቃላይ በጠፈር ላይ ሚሰሩ ይኖራሉ.. ወደ እኛ ደግሞ የሚላኩ በእግዚአብሔር ፊት የሚቆሙ ሊቃነ መላእክት እና መላእክት አሉ.. ቅዱስ ሚካኤል ያለው ከዚህ ከሦስተኛው ነው።

እነዚህ ወደ እኛ የሚመጡ መላእክት በኑሯችን ውስጥ በድኅነታችን ውስጥ ትልቅ ቦታ አላቸው.. በተለይ ቅዱስ ሚካኤል በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔርን ሕዝብ እስራኤልን ከእግዚአብሔር እየተላከ የሚረዳ መልአክ ነበር.. አሁን ደግሞ በሐዲስ ኪዳን እውነተኛውን የእግዚአብሔር ሕዝብ እኛን ያግዛል.. በሐዲስ ኪዳንም ስለ መላእክት እንዲህ ተብሏልና፡ "ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን?"(ዕብ 1፡14)

ይህ ተወዳጅ የጌታ መልአክ አሁንም ያግዘን ዘንድ ጠላቶችንም ይዋጋልን ዘንድ ጸሎታችንንም ያሳርግልን ዘንድ ምንም የማይገባን ዓይነት ሰዎች ስለሆንን እግዚአብሔር በምህረቱ መልአኩን ይላክልን።

@Apostolic_Answers

>>Click here to continue<<

ሐዋርያዊ መልሶች

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)