የዘይቱኗ እመቤት መነጋገሪያ ሆናለች ደግሞ ሰሞኑንም😁😁
በዘይቱን የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ከ50 ዓመት በፊት አካባቢ እመቤታችን ለ3 ዓመት ሙሉ በተከታታይ መገለጧ እና በቦታው በነበሩ ሙስሊሞችም ጭምር የተመሰከረለት የፈውስ እና ሌሎችም ተአምራት ምናምን መፈጠሩ እጅግ አነጋጋሪ ነው.. በሰዓቱ የነበሩ የዓይን ምስክሮች አሁንም ድረስ አሉ.. እና ሰዎች ከዚህ ነገር 2 ነገሮችን እያስቀመጡ ነው:
1. ክርስትና እውነትና ሕያው መሆኑን አስረጂ ከሆኑ ብዙ ምስክሮች ውስጥ አንዱ መሆን ይችላል ይሄ.. ያው የተገለጠችው የጌታ እናት እንጂ ሙሃመድ አይደለምና.. እና ኤቲስቶችንም አፍ ያስይዛል ተብሎ ይታሰባል..
2. ከክርስትናም ደግሞ የግብጽ ቤተ ክርስቲያን እውነተኛ የጌታ ቤተ ክርስቲያን ለመሆኗ አንዱ ማሳያም ጭምር ነው ይህ የሆነው በግብጽ ቤተ ክርስቲያን ላይ ነውና..(ያው እኛም በግብጽ በኩል ስለሆነ የመጣነው ፍትት በሉ ሎል)
ይህንን ተአምር ካቶሊካውያኑ ሳይቀር ተቀብለውታል በነገራችን ላይ.. ያው መርማሪዎችን ልከው አጣርተው ምናምን ማለተው ነው። እንዲህ ዓይነት የገነነ ተአምር በነገራችን ላይ የትም ያለ አይመስለኝም በካቶሊክም በኢስተርን ኦርቶዶክስም..
@Apostolic_Answers
>>Click here to continue<<