ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የቅዱስ ወንጌል ክፍል:
“ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም..”
[ዮሐንስ 14: 18]
ጌታችን ኢየሱስ ሊሞት በሚቃረብበት በዛን ወቅት ተከታዮቹን ሲያጽናና “ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም..” አላቸው.. ስለዚህም ሞቶ አይቀርም ይልቁንም ተነሥቶ ተመልሶ ወደ እነርሱ ይመጣልና ነው..
ከዛ በኋላም ግን ወደ አባቱ ይሄዳል ያርጋል.. ያኔስ ተከታዮቹን ወላጆች እንደሌላቸው ልጆች ተዋቸው..?? በፍጹም “ለዘላለም ከእናንተ ጋር ይኖር ዘንድ መንፈስ ቅዱስን እልክላችኋለሁ” አላቸው.. ስለዚህም ቤተ ክርስቲያን ሁሌም ቢሆን በመንፈስ ቅዱስ ከኢየሱስ ጋር ትኖራለች..
ጌታ ሁሌም ከእኛ ጋር ነው..
መልካም የጌታ ቀን
@Apostolic_Answers
>>Click here to continue<<