ቤተ ክርስቲያን በጣም ልትሰራ ሚገባው ብዬ ማስበው ሌላው ነገር በባልና ሚስት መካከል ያለው ግንኙነት ላይ ነው..
በተለይ ባል አምባገነን መሆን የለበትም.. በጣም ብዙ ባል እየሰከረ የሚገባ ሚስቱን የሚያስመርር ጭራሽ የሚማታም በአጠቃላይ ሕይወቷን የሚያከብድ አለ.. ጭራሽ ልጆች ደግሞ ሲኖሩ አስቡት ምን ያህል እንደሚያሳቅቅ..
እና ያው የብዙ ሰው አስተዳደግ እግዚአብሔርን በመፍራት እና በማፍቀር ውስጥ ስላልሆነ የሕይወት መንገዱ እንደ ስሜቱ እንጂ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ አይደለም.. እና እንደው እናቶችን/ሚስቶችን የሚያሳቅቁ ዘግናኝ ባሎች መስመር እንዲይዙ ቤተ ክርስቲያን ያው የራሷ ሃላፊነት አለባት..
@Apostolic_Answers
>>Click here to continue<<