ድብ ወይስ የሚደፍርና የሚገድል ወንድ..??
ምንም ጥያቄ የለውም እንዲህ ያለው ወንድ ምንም እንኳን ክቡር ሆኖ ቢፈጠርም እንደ እንሰሳ ሆኗልና(መዝሙረኛው ዳዊትም እንደሚናገረው) ከድብ ጋር ቢነጻጸር ምንም አይገርመንም..
ከእንደዚህ ዓይነት “ሰው” ጋር በተለይ ክርስቲያን ከሆነ እንደውም መብል እንኳን አብረነው እንዳንበላ በመጽሐፍ ታዝዘናል.. ያው በንስሐ እስካልተመለሰ ድረስ ማለት ነው..
—————//////————-
ድብ ወይስ ማንኛውም የማናውቀው ወንድ..??
ይሄ ህክምና የሚያስፈልገው ነው በእውነት.. በቃ አብዛኛው ወይም ሁሉም ወንድ ገዳይና ደፋሪ ነው የሚል አሳብን ይዘው የተነሱ ፌሚኒስቶች አሳብ ነው ይሄ.. ስለዛ ክርስቲያኖች ከዚህ ከሁለተኛው እንጠንቀቅ.. እህቶች ከጥቃቶች መጠበቅ አለባቸው ግን በየመንገዱ ያለውን ክርስቲያን ወንድሞቻቸውን ሁሉ ይሄም እንደዛው ነው በሚል ዓይን እያየች መሆን የለበትም.. አብረሽው ምትቆርቢው ወንድምሽ ነውና ነገሩን ጠቅላላ እንዳናቦካው..
@Apostolic_Answers
>>Click here to continue<<