አልጄሪያዊው /Hacker/ "ሃምዛ ቢንድላጅ"
በአለም ላይ አሉ ከሚባሉት እጅግ አደገኛ አስር የኮምፒውተር ሃከሮች አንዱ የሆነው አልጀሪያዊው ሃምዛ ቢንድላጅ ኮምፒውተሮችን ሃክ ለማድረግ የሚረዳ ቫይረስ ሰርቶ ኦንላይን መሸጥ ከጀመረበት ግዜ አንስቶ የአሜሪካኑ FBI ከኢንተርፖል ጋር በመተባበር በጥብቅ ሲፈለገው ቆይቶ 2013 ታይላንድ ውስጥ ተይዞ ነበር ወደአሜሪካ የተላከው!
ይህ ወጣት የፔንታገኑን ምክርቤት ቢሮም ሆነ የእስራኤሉን የስለላና የደህንነት ቢሮ ኮምፒውተሮች ሳይቀር ሃክ እንዳደረገና አሜሪካኖች ቀይ መስመር (Red line) የሚሉትን መስመር እንዳለፈ ነው የሚነገረው!
ከዚህ በተጨማሪም ይህ ተአምረኛ ወጣት እስራኤልና አሜሪካ ፍልስጤም ላይ ያላቸውን የተንሸዋረረ አቋም በፅኑ ከመቃወሙም ባለፈ የባንኮቻቸው ኮምፒውተር ውስጥ እንዳሻው እየገባ ከ 4 ቢሊየን ዶላር በላይ በመዝረፍ ለአልጄሪያውያንና ለፍልስጤም የእርዳታ ድርጅት አከፋፍሏል! (4 ቢሊዮን የአንዲት ደሃ አገር አመታዊ በጀት እንደሆነ ልብ ይሏል)
ከዚህ በተጨማሪም የተለያዩ የአውሮፓ ሃገራት ኤምባሲዎችን ሃክ በማድረግ ለአልጄራውያን ወጣቶች ቪዛ በመስጠት የተለያዩ የአውሮፓ ሃገሮች ላይ መኖር እንዲችሉ አድርጓል!
ይህ ወጣት ከ 8 ሺህ በላይ የፈረንሳይ ዌብሳይቶች ፣ ከ1.4 ሚሊየን በላይ ኮምፒውተሮችንና ከ217 በላይ የባንክ አካውንቶችን ሃክ ከማድረግ አልተመለሰም! ራሱም ቢሆን የፈለገበት ሃገር ውስጥ እንደፈለገ እየገባና እየወጣ እንደኖረ ነው እየተነገረ ያለው!
በዚህና በመሰል ከፍተኛ ወንጀሎቹ አማካኝነት ነው የአሜሪካው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሞት የፈረደበት! አልጄሪያውያን ግን ሃምዛን ብሄራዊ ጀግናና የአሜሪካውያንና የእስራኤል የቁም ቅዠት ነው በማለት በማህበራዊ ሚዲያዎች ያሞግሱታል !
የሞት ፍርድ የተፈረደበት የሃያ ሰባት አመቱ ሳቂታው ሃምዛ ቢንድላጅም የታይላንድ ፖሊሶች እጅ ሲገባ እንዲህ ነበር ያለው «I am not a terrorist!»
>>Click here to continue<<