TG Telegram Group Link
Channel: የዘማሪ ትንሣኤ ፍቃዱ ግጥሞች ቻናል
Back to Bottom
የዘማሪ ትንሣኤ ፍቃዱ ግጥሞች ቻናል
ሰላም እንዴት ናችሁ የየዙሩ አሸናፊዎች እና የ12 ኛው ዙር ከአንድ እስከ አምስት የወጣችሁ በሙሉ የሽልማት ማጣሪያ ውድድሩ ስለተጀመረ ግጥማችሁን ላኩ። የላኩት ትንሽ ልጆች ናቸው።
እስከ ነሐሴ 7 እንጠብቃለን ከእዛ በኋላ አንቀበልም ሌላ አዲስ ተወዳዳሪ በእናንተ ቦታ እንዲገባ 13ኛ ዙር እንቀጥላለን 16 ሰው እስኪሞላ

1) ቃለአብ ተስፋዬ
2) ዕሌኒ
3) ዘማሪ ደረጀ
4) ዐቢይ ዓለሙ
5) ብሌን ስንትአየሁ
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.

12 አሸናፊዎች ገና ግጥማችሁን አልላካችሁም እስከ ነሐሴ 7 ብቻ ነው የምንጠብቀው
🏆 🏆 🏆
የአሸናፊዎች ማጣሪያ ግጥም ውድድር

ከህመሜ ጉዳይ አለህ?

ተይኝ፣እርሺኝ፣በቃሽ እያልክ አትወትውተኝ
እንደአመልህ እርሳኝ እንትፍ እርግፍ አርገህ ተወኝ
አንተ ነህ ቆራጡ ያኖርነውን ፍቅር ረግጠህ የሄድከው
የፈቀድክ ገላህን መንገደኛ እዲያቅፈው
አንተ ነህ ጨክነህ የካብነውን ፍቅር በአንዴ የናድከው

ያላቅሜ እርሺኝ አትበል
ስለበቃህ በቃሽ አትበል
እወቅበት መንገድህን
እንድተውህ አትዘዘኝ
ከሄድክ ሂድ በናፍቆትህ ልንደድ
አትፍረድ በእንባዬ ባትታደል ለማባበል
ሂድ ዝም ብለህ......
ገፍትረህ አልጣልከኝ ብሞትም ፈቅጄ
አይሰማህ ሸክም አይግባህ ትካዜ
አንተ ምን አጠፋህ?
የወወደድኩህ እኔ ያመለኩህ እኔ
አታልቅሺ አትበለኝ ህመም ሰተህ ለገላዬ

ሂድ ዝም ብለህ...

በናፍቆትህ ብዛት ይኸው ልጎናበስ አቀርቅሬ ላዝግም መሄድ እስኪያድለኝ
ሰብረህ ስታበቃ ምርኩዝ እንቺ ብለህ ደርሰህ አትደልለኝ
አንዴ ጥለኸኛል ለማንሳት አትምጣ
አትመለስ ልኑር ከትዝታህ ጋራ

ተይኝ፣ጥይኝ፣እርሺኝ አትበለኝ ስር የያዘ ልብ አይላላም
ልውደድ ብለው ያልወደዱት ልጥላ ተብሎ አይጠላም

በቃህ አትወትውተኝ

ማን ነህ አንተ ልቤን ምታዝበት?

ሂድ ዝም ብለህ.....
ከህመሜ ጉዳይ አለህ?
ሂድ .....

Ⓒብሌን ስንታየሁ ✍️

ግጥሟን ከወደዳችሁላት ላይክ እና ሼር ተባበሯት

🏆🏆🏆🏆🏆
ግጥም ለመላክ
👇👇👇
. @Tins7

🏆🏆🏆
ለመቀላቀል
👇👇👇
hottg.com/zemaritnsae
🔴አዲስ አበባ
ይህንን ቤተክርስቲያን ለኮሪደር ልማት በሚል ምክንያት እንደ ሱቅ መንገድ ላይ ቤተመቅደሱን ብቻ ባዶውን ሊያስቀሩት ነው።
በማንኛውም ማሕበራዊ ሚዲያ ድምፅ ሆነን ከመፍረስ እናድነው።
➟ከኪነ-ጥበብ
🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆
13ኛ ዙር ግጥም ውድድር ተጀምሯል
             እስከ መስከረም 1

አትቸኩሉ መጀመሪያ ሙሉውን እስከ መጨረሻው አንብቡት
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇



ሽልማቱ
👇👇👇

1ኛ  የወር 2000 mb ይሸለማል እና ወደ ትልቁ ውድድርም ያልፋል

2ኛ 1000 mb ይሸለማል ወደ ትልቁ ውድድር አያልፍም ድጋሚ መሞከር ይችላል

3ኛ የቀን 250+250 mb ይሸላማል ወደ ትልቁ ውድድር አያልፍም ድጋሚ መሞከር ይችላል


🏆🏆ሪከርድ የሰበረ ደግሞ ጭማሬም ያገኛል

ለማሸነፍ ጥረት ያስፈልጋል መልካም እድል

  ለተሞክሮ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇
( የ2014 አመት የአሸናፊዎች አሸናፊ ገጣሚ አዶተና ንቤኒ እስከ አሁን 11,000 ብር ሰርታለች ስራዋም ይቀጥላል የቻናሉ ፉል አድሚንም ነች
( ለ2015 አመት የአሸናፊዎች አሸናፊም ገጣሚ ሔለንም ለአሁን  3000 ብር በማግኘት የእዚህ ዕድልም ተካፋይ ሆናለች ይህ ዕድል አያምልጣችሁ ለአሁን mb መሆኑን አትዩ ቀጣዩን በትዕግሥት አስቡ


በምታገኙት ላይክ መጠን 50%
በዳኛ ውጤት 50%
ቦነስ ደግሞ ከ10
ይሰጥበታል

ግጥሙን የምትልኩበት ሊንክ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@Tins7 @Tins7 @Tins7 👈
የግጥማችሁን ውጤት የምትከታተሉበት የቻናሉ  ሊንክ ደግሞ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@zemaritnsae
@zemaritnsae

የውድድሩ ህግ
1) የሰው ግጥም ይዞ የቀረበ ከውድድሩ ይሰረዛል
2) የስነ ምግባር ጉድለት የታየበት ከውድድሩ ይሰረዛል

የውድድሩ መስፈርት
1) ማንኛውም ሰው መወዳደር ይችላል

2)ግጥሞቹ ከሀጥያት ከብልግና ውጪ መንፈሳዊም አለማዊም ቢሆን ችግር የለውም ግን እያዝናና የሚያስተምር መሆን አለበት
ሼር በማድረግ ጋብዙ

ውጤት አሰራር
👇👇👇👇👇👇👇👇
የተወዳዳሪው ላይክ x 50% ------------------------------------- + የዳኛ
       ከፍተኛው ላይክ
🙏🙏🙏🙏🙏
መልካም ውድድር
🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆
. 13 ኛ ዙር ግጥም ውድድር

ፀሎት ስጠኝ

በነጭ አሸብርቄ በረዶ መስዬ
ነጠላ አደግድጌ ዳዊትም አዝዬ
ከደጅህ ብመጣም የምለው ስላጣሁ
ምንም ሳልጠይቅህ እንደሄድኩት መጣሁ
ያው ከነሸክሜ
ከሀጥያት ጭንቀቴ ምንም ሳላወጋ'
የሆዴን ሳልነግርህ ቃላት ሳልዘረጋ
ላንተ የማቀርበው የምለው ስላጣሁ
ምንም ሳልል ሄጄ ምንም ሳልል ወጣሁ
ተደጋገመብኝ ይሄ ፀሎት ማጣት
እንደ በድን ሄደው እንደ በድን መምጣት
ከፊትህ የሚቀርብ ቃላት ስላቃተኝ
ለኔ የሚገባ እግዜር ፀሎት ስጠኝ።

ዕዝራ ግጥሙን ከወደዳችሁለት ላይክ እና ሼር ተባበሩት

🏆🏆🏆🏆🏆
ግጥም ለመላክ
. 👇👇👇
. @Tins7

🏆🏆🏆
ለመቀላቀል
👇👇👇
hottg.com/zemaritnsae
🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆
. 13 ኛ ዙር ግጥም ውድድር

ና ውረድ እግዜሩ እግርህ መሬት ይንካ
ሰው ማምለክ ዘንግቶ በገንዘብ ተመካ
መዳኛ መንጫውን
ተቀምጦ ሰቅሎት በጥፋት መንገዱ
ዛሬ ተንጠራርቶም አቃተው ማውረዱ
ምን ትላለህ እግዜር?
የሰማነውን ቃል ህግጋት ወንጌሉን
ሰው የመሆን ምስጢር የመፈጠር ውሉን
ሻርነው በጣጠስነው ሸሸነው ርቀን
ድፍረት አደረግነው ምህረትህን አውቀን
ምን ትላለህ እግዜር?
ሰው ለሆዱ አደረ ገንዘብ አናወዘው
ለመብላት ብቻ ነው የሚወዛወዘው
ጌታ ሆይ ና ውረድ
እንደባቢሎን ግንብ መዳፈርን አፍርስ
ለሚገባው ሁሉ የህግህን አድርስ
ውረድልን አምላክ
የራበውን አለም ወርደህ አንበሽብሸው
ለሆዱ ነው መሰል ከቤትህ የሸሸው
ና በል ድረስና
ለሆድ የሸሸውን በሆዱ መልሰው
መቼም ያንተ ቤት ነው
ከመጡት መካከል ይፀድቃል ጥቂት ሰው
ና ፍረድ እግዜሩ
መሬት ትለስልሰን ይከፈል ባህሩ
እልፍ ሙሴ ይምጣ ፍጠር ከነበትሩ
ዳዊት ይንገስ ዳግም ትነሳ ወንጭፉ
በአለም በዝቶልሀል ጎልያድ ግዙፉ
ዮናስን ላክልን ይለምን ወደ አንተ
ፆምን ያውጅልን ሰው ተሳሳተ
ሁሉም ያንተ ሰዎች ይፈጠሩ ዳግም
አለም ከህመሟ ችላ እንድታገግም
ምህረት ላክ ንጉሱ
አምሳያህ ክቡሩ ረክሷል መንፈሱ
በደም ተካብተዋል ሰይፍን እያነሱ
ያንን ሰው ንገረው
የሞት ሞትን ሞተ ሰይፉን ይመልሰው
ሌላውስ መልካም ነው
ሞሞቱም ሰርጉ ነው ጥንቱንም ላንተ ሰው።

ይታያል ጌቴ

🏆🏆🏆🏆🏆
ግጥም ለመላክ
. 👇👇👇
. @Tins7

🏆🏆🏆
ለመቀላቀል
👇👇👇
hottg.com/zemaritnsae
🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆
. 13 ኛ ዙር ግጥም ውድድር

ይቅርታ
በደልን ይዞ መኖር ቂም ቁአጥሮ
የህሊና ህመም ነው የብቸኝነት ኑሮ
በጉአደኝነት ዘመን ሰንቱን አሳለፍፌ
መሸሽ መሸነፍ ነው ነገርን አልፌ
ከፍቅሩም ቀረብ ከእውነቱም ጠጋ
መቻል እና ምህርት ነው ከፈጣሪ ፀጋ
ልቤና እሊናዬ እውነት ሲፈጥራቸው
ውጫዊ ማንነት መቶ በገዛቸው
እስቲ መልሱልኝ ከዛው ከቤታችው
ጥላቻ ሚመጣው ከውጪው ማንነት
ፈጣሪማ ያደለን ከንፁህው በረከት
ተመክሮ መካሪ መሆን ስላለበት
ማግኝት መታደል ነው ከገፀ በረከት
ልቤ አትዘን ቢበድለኝ ጉአዴ
መክሬ ላስተምረው በጠንካራው ክንዴ
ሁሉም ቆም ብሎ ካሰበ እውነት
ተመልሶ ይመጣል የኛም አንድነት
ነውና ነገሩ ከክፋት ደግነት
መኖረ ይበጃል በንፁህ ቅንነት.

አንዱዓለም ወርቅነህ

ግጥሙን ከወደዳችሁለት ላይክ እና ሼር ተባበሩት

🏆🏆🏆🏆🏆
ግጥም ለመላክ
. 👇👇👇
. @Tins7

🏆🏆🏆
ለመቀላቀል
👇👇👇
hottg.com/zemaritnsae
የዘማሪ ትንሣኤ ፍቃዱ ግጥሞች ቻናል
🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆 13ኛ ዙር ግጥም ውድድር ተጀምሯል              እስከ መስከረም 1 አትቸኩሉ መጀመሪያ ሙሉውን እስከ መጨረሻው አንብቡት 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 ሽልማቱ 👇👇👇 1ኛ  የወር 2000 mb ይሸለማል እና ወደ ትልቁ ውድድርም ያልፋል 2ኛ 1000 mb ይሸለማል ወደ ትልቁ ውድድር አያልፍም ድጋሚ መሞከር ይችላል 3ኛ የቀን 250+250 mb ይሸላማል ወደ ትልቁ ውድድር አያልፍም…
ሰላም እንዴት ናችሁ ግጥም ውድድሩ በሐዘን ምክንያት በመቋረጡ ይቅርታ እየጠየቅን ዛሬ ካቆምንበት እንቀጥላለን የላካችሁ የተለቀቀላችሁ ሌላ መላክ አይጠበቅባችሁም እስከ ጥቅምት 7 ስለተራዘመ ወደላይ በመሄድ የተመቻችሁን ግጥም ላይክ በማስደረግ ተባበሩ ግጥም ያልላካችሁ ደግሞ ከአሁን ጀምሮ መላክ ትችላላችሁ መልካም ቀን
Forwarded from ዘ-ተዋሕዶ ቦት
1⃣7⃣ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል


የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!

በኢትዮጵያ በጣም አስቸጋሪ የነበረዉ  ረሀብ መች አመተምህረት ነበረ
HTML Embed Code:
2024/09/24 00:36:31
Back to Top