TG Telegram Group Link
Channel: ዲያቆን ዳዊት ናሁሠናይ (ዘደብረ ብሥራት)
Back to Bottom
አንድ መንፈሳዊ ፊልም እንጋብዛችሁ?

ኢትዮጵያዊ ኦርቶዶክሳዊ ፊልም!

የሊቁ ፣ ሰማዕቱ ፣ ደራሲ ፣ የኪነ ሕንጻ ባለሙያ ፣ ባህታዊ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መንፈሳዊ ፊልም

የግብጻውያንን መንፈሳዊ ፊልም እያዩ "ለምን በሃገራችን እንዲህ አይሰራም?!" ብለው ተቆጭተዋል?

እንግዲያውስ ይህን ቁጭትዎን እውን ሊያደርግ ታላቁን አባታችንን ለዓለም ሊያስተዋውቅ እነሆ ዝግጅቱን ጀምሯል እና ዘመኑን በጠበቀ ጥራት ለሚያዘጋጀው ለዚህ መንፈሳዊ ፊልም የሚሆን የአቅማችሁን ያህል ከዚህ በመቀጠል በተጠቀሰው አድራሻ እንድትልኩልን በአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ስም አደራ እንላለን!!!

ዳዊት ናሁሠናይ
1000394090658
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ስልክ - 0975086302
እሮብ አርብ እና እሁድ

በአንድ ሳምንት ውስጥ ክርስቶስን በተለያየ መንገድ እንድናስብ የምታደርግ ኦርቶዶክስ ምንኛ ድንቅ ናት??!!

እሮብ እና አርብ በቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓት መሰረት በጾም እንድናሳልፋቸው የተቀመጡ ቀናት ናቸው። ግን ለምን ሌሎቹ ቀናት አልተመረጡም ብንል እነዚህ ቀናት የተመረጡበትን ምክንያት እናገኘዋለን።

እሮብ ቀን እኛን ለማዳን ከእመቤታችን በድንግልና የተወለደው ኢየሱስ ክርስቶስን ለመያዝ አይሁዳውያን የመከሩበት ቀን ነውና ይህንን እንድናስብ በየሳምንቱ እሮብን እንጾማለን። መልካም ያልሆነን ነገር ለማረግ ማሰብ ብሎም ማውራት ማቀድ ይፈልጋል። አይሁዳውያንም ጌታን ለመያዝ በዚህች ቀን ተማከሩ እኛም ደግሞ ክፋትን እናስብለን እንናገራለንና ይህንን ከኛ እንዲያርቅልን በዚህ ቀን እንጾማለን!!!

አርብ ቀን ደግሞ ጌታችን ስለኛ በደል የተገረፈበት የተሰቀለበት እጅግ የበዛ ስቃይን ተቀብሎ ስጋውን ከነፍሱ የለየበት ቀን ነው። አይሁዳውያንም እሮብ የመከሩትን ምክር እውን ያደረጉበት ቀን ነው። እኛም ቤተ ክርስቲያናችን ባስቀመጠችልን ሥርዓት መሰረት ይህንን ቀን እንደ አይሁዳውያን የሰራነውን የክፋት ተግባር ዛሬ በተቀበልከው መከራ ይቅር በልልን እያልን እየጾምን ስቃዩን እንዘክራለን!!!

እሁድ ደግሞ ከመከራ በሁላ ደስታ ከምሽት በኋላ ንጋት እንዲገለጥ ስለኛ ብሎ ስቃይን የተቀበለ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ የተነሳበት ታላቅ የደስታ ቀን ነው። በዚህ ቀን ደግሞ ቤተ ክርስቲያናችን ባዘዘችን መሰረት ሙሉ ቀናችንን በመንፈሳዊ ተግባራት ውስጥ ሆነን እንውላለን።

እንደዚህ ግን አስባችኋል? እኔ ያሰብኩትን ላጋራችሁ።

የጾም ቀናቱ ሁለት ሆኑ - የችግር ጊዜያቶቻችን ረጅም ቀን ናቸው ሲለን!

የደስታው ቀን ደግሞ አንድ ሆነ - ይህ የደስታ ቀን ግን ሙሉ ቀኑን በማረፍ የምናሳልፈው ነው። ይህን መከራ አልፈን የምናገኛው ሰማያዊ ደስታ ገደብ የለውምና!

#ይህንን ነገር ደግሞ ዘወትር እናስብ ዘንድ በየሳምንቱ በምናገኛቸው ቀናት ውስጥ ተመስጥሮ ይነገረናል።

* እሮብ እለት አንተን ለማሰቃየት ከሚመክሩት ወገን እንዳልሆን ጠብቀኝ። ዛሬ በህሊናዬ የኃጢአትን ሃሳብ ሳሰላስል እውላለሁና!

* አርብ እለት ምክራቸውን እውን አድርገው አንተን ካሰቃዩት ወገንም አታድርገኝ። ዛሬ ያሰብኩትን ኃጢአት በመተግበር አንተ የሞትክለትን ሰውነት ሳረክስ እኖራለሁና!

* እሁድ እለት የመነሳትህን ዜና ለመሸፈን የክፋትን ሃሳብ ካፈለቁት አይሁዳውያን ፣ ስለ ገንዘብ ሲሉ በዚህ ሃሳብ ከተስማሙት ወታደሮች ወገን አታድርገኝ። ዛሬ ያንተን እውነት ለመደበቅ አለም የሰጠችኝን እውነት ተቀብዬ እኖራለሁና!

🙏 ይልቁኑ

* እሮብ እለት ላይ ባንተ የመከሩብህን ኃጢአቶች አስቤ ስለኃጢአቴ ስርየት እንድጸልይ ፍቀድልኝ እርዳኝ

* አርብ እለት ባንተ የደረሰብህን መከራ ይልቁኑ ደግሞ አንተ በሞትክለት ማንነቴ ላይ ያደረሰኩትን የኃጢአት በደል አስቤ እሰግድ አለቅስ ዘንድ አግዘኝ

* እሁድ እለት ደግሞ በዳግም ምጽአትህ "ብራብ አብልታችሁኛል" ብለህ ከምትፈርድላቸው ወገን ለመሆን የሚያበቃኝን ተግባር በመፈጸም የተራቡትን አበላ ፣ የተጠሙትን ለማጠጣት ፣ የታረዙትን ለማልበስ ፣ እንግዳውን ለመቀበል ፣ የታሰረውን እንዲሁም የታመመውን ለመጠየቅ እችል ዘንድ አብቃኝ

"የኃጢአቴ ሸክም ሚዛን መክበዱ ከሰማይና ከምድር ክብደት ይበረታል፤ ከርሱ ደግሞ የምህረትህ ሚዛን ይደፋል። አቤቱ ኃጢአቴ ከሰማይ ኮከብ ከባህር አሸዋ ይበዛል፤ ከርሱም ደግሞ ቸርነትህ ይበዛል" አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

ዲያቆን ዳዊት ናሁሠናይ (ዘብሥራት)
ሐምሌ 23 2013 ዓ.ም
አዲስ አበባ

👇👇👇👇
👉 @zebisrat👈
👆👆👆👆
+ እግዚአብሔር እንዴት ይፈርዳል? +

(ጊዜ ወስደው ያንብቡት አያጥር ነገር ታሪክ ሆኖ ነው)

አንድ ግብፃዊ መነኩሴ ለገዳሙ መርጃ የእጃቸው ሥራ የሆኑትን ቅርጫቶች ሊሸጡ ወደ እስክንድርያ ለመጓዝ በጠዋት ተነሡ፡፡

በመንገድ ላይ ታዲያ ትልቅ የቀብር ሥነ ሥርዓት ለማድረግ የሚጓዝ ሕዝብ ገጠማቸው፡፡ ሟቹ ዝነኛ አረማዊ ገዢ ሲሆን በዘመነ ሰማዕታት በሺህ የሚቆጠሩ ክርስቲያኖችን የገደለ ሰው ነበር፡፡ አሁን ዕድሜ ጠግቦ ሞቶ ነው፡፡ ቀኑ ውብ ፀሐያማ ቀን ነበርና የሀገሩ ዜጎች በነቂስ ወጥተው ገዢያቸውን እየቀበሩ ነው፡፡

ይህንን ያዩት መነኩሴ ጉዳያቸውን ፈጽመው ወደ ገዳም ሲመለሱ አሳዛኝ ዜና ሰሙ፡፡ ለስድሳ ዓመታት በበረሃ በብሕትውና ቅጠልና የበረሃ ፍሬ ብቻ እየበላ የኖረ ባሕታዊ በዚያች ዕለት በጅብ ተበልቶ ሞቶ ነበር፡፡
መነኩሴው እጅግ ጥልቅ ኀዘን ውስጥ ሆነው እንዲህ ሲሉ አሰቡ ፦

‘በሺህ የሚቆጠሩ ክርስቲያኖችን የገደለው አረማዊ ሰው በታላቅ ክብር ታጅቦ ሲቀበር ሕይወቱን ሙሉ በጾምና በጸሎት ፈጣሪውን ያገለገለው ባሕታዊ በጅብ ተበልቶ የተዋረደ አሟሟት ሞተ፡፡ይህ እንዴት ዓይነት ፍርድ ነው? እግዚአብሔር ከመልካምነቱ ሁሉ ጋር ኢፍትሐዊ ነገሮች ሲሆኑ ዝም ብሎ ይፈቅዳል፡፡ በዚህ ምክንያት ብዙ ሰዎች የፈጣሪን መኖር ይጠራጠራሉ፡፡ እኔም ፍርዱን እንዲገልጽልኝ መጸለይ ይኖርብኛል’ አሉ፡፡

ከዚያች ቀን ጀምሮ መላልሰው ወደ ፈጣሪ ‘’ፍርድህን ግለጽልኝ’ ብለው ደጋግመው ጸለዩ፡፡ ብዙም ሳይቆይ እግዚአብሔር ፍርዱን እንዲህ ገለጠላቸው፡፡

ከሳምንታት በኋላ እንደተለመደው ወደ እስክንድርያ የሦስት ቀን ጉዞ ሊሔዱና ቅርጫታቸውን ሊሸጡ ተነሡ፡፡መንገዱን እንደጀመሩ ድንገት አንድ ወጣት መነኩሴ ወደ እርሳቸው ሲመጣ ተመለከቱ፡፡

‘’አባቴ ይባርኩኝ’

‘እግዚአብሔር ይባርክህ ልጄ’

‘አባቴ ወዴት ይሔዳሉ?’ አለ ወጣቱ መነኩሴ

‘ወደ እስክንድርያ ቅርጫቴን ልሸጥ እየሔድኩ ነው’ አሉት

‘ጥሩ አጋጣሚ ነው አባ እኔም ወደዛ እየሔድኩ ነው’ አለ በትሕትና

‘ጎሽ አብረን እንጓዛለና’ አሉ አባ፡፡ ወጣቱ መነኩሴ ከእጃቸው ሸክማቸውን ተቀበለ፡፡ ጥቂት እንደሔዱ እንዲህ አላቸው፡፡

‘አባ ያው እንደሚያውቁት እንደ መነኮሳት ሥርዓት ጉዞ ስንጓዝ በጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር አለብን አይደል?’’ አላቸው፡፡

‘ልክ ነው ልጄ’ አሉት

‘እንግዲያውስ ለሦስት ቀን አብረን ስንጓዝ እስክንድርያ እስክንደርስ ድረስ አንዲትም ቃል አንነጋገር ፤ ምናልባት በሦስቱ ቀን ጉዞአችን ለማየት የሚከብድ ነገር እንኳን ሳደርግ ቢያዩኝ ላይናገሩኝ ላይፈርዱብኝና የአርምሞ ቃልኪዳንዎን ላያፈርሱ ቃል ይግቡልኝ’ አላቸው፡፡

አባ እየተገረሙ ‘እሺ በሕያው አምላክ እምላለሁ ልጄ አንዲትም ቃል አልተነፍስም’ አሉት፡፡
ሁለቱ አባቶች በጠዋቱ የአርምሞ ጉዞአቸውን ጀመሩ፡፡ ቀትር ላይ ወደ አንዲት መንደር ደረሱ፡፡

ሁለት ወጣቶች እነዚህን መነኮሳት አዩአቸው፡፡ ከሁለቱ አንዱ ‘ቅዱሳን አባቶች’ እያለ ወደ እነርሱ ሮጠ ‘ቅዱሳን አባቶቼ ፀሐዩ እስኪበርድ ድረስ እባካችሁን እኛ ቤት አረፍ በሉ’ አላቸው፡፡ ፀሐይዋ እየከረረች ስትመጣ በበረሃማዋ ግብፅ ጉዞ በጠዋትና ማታ እንጂ በቀትር ስለማይታሰብ ጉዞአቸውን ማቋረጥ ነበረባቸው፡፡ ስለዚህ ሁለቱ ወጣቶች እነዚህን መነኮሳት በክብር ተቀብለው ከቤታቸው አስገቧቸው፡፡እግራቸውን አጠቧቸው፡፡ በቤታቸው ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ የኖረ የከበረ እጅግ ውድ የብር ሰሐን ላይ ምግብ አቀረቡላቸው፡፡ መነኮሳቱ በዝምታ ተመገቡ፡፡ ከዚያም ትንሽ አረፍ የሚሉበት ክፍል ተሠጣቸው፡፡

ትንሽ እንደቆዩ ወጣቱ መነኩሴ ቀስ ብሎ ወደ ምግብ ማብሰያው ክፍል ገብቶ ይበሉበትን ውድ የብር ሳህን በልብሱ ደብቆ ይዞት መጣና አባን ጠቅሶ ጠራቸው፡፡ ተሰናብተው ከወጡ በኋላ አባ በቀሚሱ ውስጥ የደበቀውን የብር ሳህን ሲያዩ ደነገጡ፡፡ መናገር ባይችሉም በልባቸው እንዲህ አሉ ፦

‘እነዚያ ደግ ወጣቶች በክብር ተቀበሉን ፤ እግራችንን አጥበው መገቡን፡፡ እውነት ለውለታቸው ምላሹ ውዱን ንብረታቸውን መስረቅ ነው?’’ ብለው አዘኑ፡፡

ጥቂት እንደተጓዙ የመስኖ ውኃ ወደተከማቸበት አንድ ድልድይ ጋር ደረሱ፡፡ ውኃውን ሲሻገሩ ታዲያ ወጣቱ መነኩሴ በብር ሳህኑ ላይ ካማተበበት በኋላ ወደ ወንዙ ወረወረው፡፡

አባ እንዲህ ብለው አልጎመጎሙ ፦
‘’እንዴት ያለ ነገር ነው? ሳህኑን የሰረቀው ሊወረውረው ነው? እዚያው አይተውላቸውም ነበር?’’ አሉ አርምሞአቸውን ሊያፈርሱ አይችሉምና ዝም አሉ፡፡

ሲመሽ ወደ አንድ ወጣት ባልና ሚስት ቤት ደረሱ፡፡ እንደ ቀኖቹ ወጣቶች እነዚህም በክብር እግር አጥበው አስተናገዷቸውና ማረፊያ ሠጧቸው፡፡ ባልና ሚስቱ የሁለት ወር ሕፃን ልጅ ነበራቸው፡፡ በጠዋት ሲነሡ ወላጆች ሳይነሡ ወጣቱ መነኩሴ ቀስ ብሎ ሔዶ የተኛውን ሕፃን ገደለው፡፡ አባ ሊያስጥሉት ቢሉም አልቻሉም፡፡ እየጎተተ ይዞአቸው ወጣ፡፡ ‘ጌታ ሆይ ምን ዓይነት ርጉም ነው ንጹሑን ሕፃን ገደለው እኮ’ እያሉ እንባቸው ወረደ፡፡ ምንም እንኳን አንጀታቸው በኀዘን ቢኮማተርም በመሓላ የገቡበትን አርምሞ አፍርሰው ከግዝት ላለመግባት አንዲት ቃል ግን አልተናገሩም፡፡

በቀጣዩ ቀን ሁለቱ መነኮሳት ወደ አንድ መጠጥ ቤት ደጅ ደረሱ ፤ የጭፈራው ድምፅ ከሩቅ ይሰማል ፤ ሰካራሞቹ መነኮሳቱን ሲያዩ ‘ቅዱሳን’ እያሉ ተሳለቁ፡፡ በሰካራም አንደበት የሚናገረው ዲያቢሎስ ነው ብለው ዝም አሉ፡፡

ወጣቱ መነኩሴ ግን ወደ መጠጥ ቤቱ አቅጣጫ በግንባሩ ተደፋና ሦስት ጊዜ ሰግዶ ተሳለመው፡፡
ጥቂት እንደሔዱ አንድ ያረጀ ፤ መስቀሉ ከጉልላቱ የተነቀለ በርና መስኮት የሌለው ቤተ ክርስቲያን አዩ
ወጣቱ መነኩሴ ድንጋዮች ለቀመና አማተበባቸው ወደ ፈረሰው መቅደስም ወረወረው

አባ ይሄን ጊዜ ፦ መጠጥ ቤቱን ተደፍቶ ተሳለመ ፤ ወደ ቤተ መቅደሱ ድንጋይ ወረወረ ! ብለው በዝምታ ተንጨረጨሩ ::

አሁን ሦስተኛው ቀን ሞላ በጠዋቱ ወደ አንድ በሸንበቆ የተሠራ ቤት ደረሱ እናታቸው የሞተችባቸውና በአጎታቸው እርዳታ ብቻ የሚኖሩ አምስት ሕፃናት ተቀምጠው ያለቅሳሉ፡፡ አባ በርኅራኄ ለሕፃናቱ ምግብ ሠጧቸው፡፡ እሳቸው ከሕፃናቱ ጋር ሲነጋገሩ ወጣቱ መነኩሴ ደሞ የሸንበቆውን ቤት በእሳት እያያያዘ ነበር፡፡ ሕፃናቱ ከሚነደው ቤት ሮጠው አመለጡ፡፡

‘ይህን ነፍሰ ገዳይ እስከመቼ እታገሰዋለሁ’ ሲሉ የቆዩት አባ እስክንድርያ ደርሰዋልና በምሬት መናገር ጀመሩ
‘’እስቲ ንገረኝ ከዚህ በኋላ ዝም ልልህ አልችልም፡፡ መልስልኝ አንተ ሰው ነው ወይስ ሰይጣን ነህ?’

‘ምነው አባ ምን አጠፋሁ?’ አለ መነኩሴው
‘በዚህ ሦስት ቀን ውስጥ ምን ያላደረግከው ነገር አለ? በበረሃ አክብረው የተቀበሉንን ሰዎች የብር ሳህን ሰርቀህ ወንዝ ውስጥ አልጨመርህም? እነርሱም መነኩሳት በቤታችን ተቀብለን ሰርቀውን ሄዱ እያሉ ይሆናል’
መነኩሴው መለሰ :- ‘አባ ትልቅ ነገር ነው እኮ ነው ያደረግሁላቸው፡፡ ያቀረቡልን የብር ሳህን ቅድም አያታቸው ከጥንታዊ ቤተ ክርስቲያን የሰረቀው ጻህል /የቅዱስ ቁርባን ማቅረቢያ/ ነበር፡፡ መላው ቤተሰብ ይህንን ሳያውቅ በዚያ ቤት ለብዙ ዘመን ሲቀባበሉት ነበር፡፡በላዩ ላይም በላቲን ቋንቋ ይህ ጻህል ለቅዱስ ኒቆላዎስ ቤተ ክርስቲያን የተሠጠ የሚል ጽሑፍ አለበት፡፡ በዚህ ምክንያት ያንን ቅዱስ ንዋይ የሚጠቀሙ ሁሉ እስካልተመለሰ ድረስ በእግዚአብሔር ላይ ድፍረት ይሆንባቸዋል፡፡ የሞቱት ወላጆቻቸውም በዚያ ቅዱስ ንዋይ የተነሣ ነፍሳቸው ትታወካለች፡፡ እነዚያም ወጣቶች በጻሕሉ እኛን በማስተናገዳቸው ነፍሳቸው እንዳትጎዳ አዘንኩላቸው፡፡ ስለዚህም ሰረቅኋቸው፡፡ የሰረቅሁት ፈልጌው አይደለምና ውኃው ውስጥ ወረወርሁት፡፡

በማግሥቱ የደብሩ ዘበኛ ሊታጠብ ወደ ውኃው ይመጣል፡፡ በውኃው ውስጥም ያገኘዋል፡፡ የላቲን ቋንቋ ስለሚያውቅ የተጻፈውን ያነበዋል፡፡ ወስዶም ለካህኑ ይሠጠዋል፡፡ ፃህሉ ከብሮ ድጋሚ ሲቀደስበት የሞቱትም ያርፋሉ የቆሙትም ከጥፋት ይድናሉ፡፡ ’ አላቸው፡፡
አባ ተደነቁ ፤ ‘እሺ ሕፃኑንስ የገደልከው ለመልካም ብለህ ነው?’

‘አባ የእግዚአብሔርን ፍርድ አይመዝኑ ፤ ሕፃኑ የተፀነሰው በኃጢአት ነው ፤ ለወደፊት ደግሞ እጅግ ጨካኝ ወንጀለኛ ሆኖ ወላጆቹን የሚገድል ብዙዎችን የሚያሰቃይ ነው፡፡ ስለዚህ ልጁን በመግደሌ ሦስት መልካም ነገሮች አደረግሁ፡፡ ሕፃኑ ከንጽሕናው ጋር ወደ ሰማይ እንዲሔድ አደረግሁት ፤ ወላጆቹንም በልጃቸው እጅ ከመሞት አዳንኋቸው፡፡በዚህ ልጅ ኀዘን ምክንያት ወላጆቹም ልባቸው በመሰበሩ የቀደመ ኃጢአታቸው ይቅር ይባልላቸዋል’

‘እሺ መጠጥ ቤቱ ደጃፍ ላይ የሰገድከው ምን ሆነህ ነው?’
‘ሦስት ሰዎች በዚያ መጠጥ ቤት ውስጥ ሆነው የፈረሰውን የከተማችንን ቤተ ክርስቲያን እንዴት እንሥራ እያሉ እየተጨነቁ ይነጋገሩ ነበር፡፡ ምንም እንኳን የተሰበሰቡበት ቦታ መጥፎ ቢሆንም በልባቸው ያለው ሃሳብ ቅን ስለሆነ እግዚአብሔር እንዲረዳቸው ወድቄ ሰግጄ ለመንሁት’’

‘ታዲያ ወደ ፈረሰው ቤተ መቅደስ ድንጋይ ለምን ወረወርህ?’
‘በፈረሰው መቅደስ ላይ እየተሳለቁ አጋንንት ሲጨፍሩ አየሁ፡፡ በመስቀል ምልክት አማትቤ ድንጋይ ወረወርሁ ፤ በዚህም ምክንያት አጋንንቱ በንነው ሸሹ’ አለ መነኩሴው፡፡

አባ ቀጠሉ ‘የእነዛን የሙት ልጅ የሆኑ ሕፃናት ቤትስ ለምን አቃጠልከው?’
‘’እነዚያ ሕፃናት እንደሚያውቁት ወላጆቻቸው ሞተውባቸዋል ፤ የቀራቸው ንብረትም ቤቱ ብቻ ነው፡፡ ቅድመ አያታቸው የቀብሩት እጅግ ብዙ ሀብት ግን ከዚያ ቤት በታች አለ፡፡ ከቃጠሎው በኋላ በቀረው ክፍል ለማደር ልጆቹ ሲገቡ የተቀበረውን ሀብት ያዩታል፡፡ በቤተ ክርስቲያን ጠባቂነት ለሚያገለግል አጎታቸውም ሔደው ይነግሩታል፡፡ በረሃብ መሞታቸው ቀርቶ በጥሩ ሁኔታ ያድጋሉ’’ አለ መነኩሴው፡፡

አባ ምንም እንኳን ነገሩ ቢያስደንቃቸውም አንድ ወጣት መነኩሴ ይህንን ሁሉ እንዴት ሊያውቅ ይችላል የሚል ጥርጣሬ አደረባቸውና ‘አንተ ማን ነህ?’ አሉት፡፡
‘የእኔ ማንነት ይቆይና እርስዎ በዚህ ሰሞን መላልሰው ፈጣሪን የጠየቁት ነገር ካለ ይንገሩኝ’ አላቸው
‘እኔማ እግዚአብሔር ሆይ ፍርድህን አሳየኝ ብዬ በምድር ላይ ስለሚደረጉ ኢፍትሐዊ ነገሮች ጠይቄው ነበር’ አሉት፡፡

‘እግዚአብሔር ‘ሰማይ ከምድር እንደሚርቅ መንገዴ ከመንገዳችሁ ሃሳቤም ከሃሳባችሁ የራቀ ነው’ ብሏልና ፍርዱ አይመረመርም፡፡ ለመላእክት እንኳን ያልተገለጸውን የእግዚአብሔርን ፍርድ እንዴት እርስዎ በሰው አቅም ሊመረምሩ ይፈልጋሉ፡፡ ጸሎትዎን ሰምቶ እግዚአብሔር ያዩትን ሁሉ እንዳደርግና ፍርዱን እንዳሳይዎት ላከኝ’’ አላቸው፡፡

ቅዱስ ዑርኤል ለዕዝራ እንዲህ አለው፦
‘የምትፈርስ የምትበሰብስ አንተ የማይፈርስ የማይበሰብስ የሕያው እግዚአብሔርን ፍርዱን ልትመረምር አትችልም’

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ሚያዝያ 24/ 2012 ዓ ም

/How God Judges People – The patristic heritage book 2 – /Elder Cleopa/ ከሚለው የዜና አበው መጽሐፍ የተተረጎመ/

ማስታወሻ ፦ ይህንን ታሪክ ትንሽ የሚመስለው ታሪክ በ1747 የተጻፈው የቮልቴር ዛዲግ ላይ አንብቤ የታሪኩ ሞራል ደስ ቢለኝም የዞራስትራኒዝም ነበርና ለቤተ ክርስቲያን አይሆንም ብዬ ነበር፡፡ ለካንስ ይህ ታሪክ አስቀድሞ በመነኮሳት ታሪክ የተመዘገበ ነበርና በዚህ መልኩ ከአራተኛውና አምስተኛው ክፍለ ዘመን ወርቃማ የምንኩስና ታሪኮች በአንዱ ተመዝግቦ አገኘሁት፡፡ ባየነውና በምናየው ሁሉ እንዳሻን የእግዚአብሔርን ፍርድ በምንደመድምና በምናብራራበት በዚህ የደፋር ዘመን እንዲህ ያሉ ታሪኮች ልጉዋም ቢሆኑ በሚል ተርጉሜዋለሁ/

ፎቶ :- ብፁዕ አቡነ አብርሃም ለኢየሩሳሌም ተጉዋዦች ጸሎተ ቡራኬ በአውሮፕላን ውስጥ ሲሠጡ ያነሣኹዋቸው::

ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ! በኮሜንት መስጫው ሥር "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)

ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like, Subscribe እና Share ያድርጉ :-

የፌስቡክ ገጽ :- https://www.facebook.com/officialHenokhaile/
የቴሌግራም ቻናል : https://hottg.com/deaconhenokhaile
የዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/channel/UCOaVsWC05aUjeqIEW3fWj7g
ወንድማችን (ይህ ቃል ባለበት ሁሉ "እህታችንንም" ተክተው ይረዱልኝ

ቅድም መንገድ ላይ አለባበሱን አይተህ ገላምጠህ ያለፍከው ወንድማችንን አስታወስከው?

ክፋት እያሰብክለት ፤ ነገር እየጠነሰስክለት ያለኸው ወንድምህንስ?

የሚበላው አጥቶ ፣ በውሃ ጥም አፉ ደርቆ ፣ አንተ ምራቅህን የምትተፋበት መንገድ ዳር ላይ ሰውነቱን አሳርፎ የሚያድረውንስ?

" እህህ! እናቴ እናቴ! ምነው መጥተሽ ባየሺኝ! ወይኔ ወይኔ!" እያለ ሃኪም ቤት አልጋ ላይ መርፌ ተሰክቶለት የሚሰቃየው ወንድማችንንም መቼም አልረሳኸውም አይደል?

ብዙዎች በጥፋታቸው ዝናና ክብር በሚያገኙበት ፍርዱ በተዛባ በዚህ አለም ባጠፋው ጥፋት ዳኛ ዘንድ ቀርቦ ተፈርዶበት ፤ በዋለበት እያደረ በአንድ ክፍሎ ተዘግቶ አመታትን የቆየው ወንድማችንንም ካየኸው ቆይተሃል መሰል!

በአባት የምንገናኝ የእግዚአብሔር ልጆች ፤ እናታችን ድንግል ማርያም/ቤተ ክርስቲያን የምትሳሳልን ፤ ከአንድ አብራክ ከመንፈስ ቅዱስ ፣ ከአንድ ማህጸን ከዮርዳኖስ የተወለድን የክርስቶስ ደም ያዋሃደን ወንድማማቾች ስንሆን ነገር ግን ለክፋት ድግስ ለሴራ ግብዣ እንቀጣጠራለን።

ከወንድማችን ጋር በአካል/በመንፈስ አብረን መዋል አብረን ማደር ሲገባን ከእርሱ ጋር የሚያራርቀንን ምክንያት ያላመሳሰለንን ነገር ስንቆጥር ስንዘረዝር ውለን እናድራለን። አዎን መቼም መንታ አይደለንምና በመልካችን በትውልድ ስፍራችን በአስተሳሰብችን በሌላም ነገር አንመሳሰል ይሆናል። ነገር ግን ወንድማማቾችነታችን የማይካድ ሃቅ የማይታጠፍ እውነት ነው።

ባይገርማችሁ የኛን የወንድም ፍቅር ተመልክቶ በአንድ ወቅት "የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ ወንድሜ ነው" ማር 3፥35 ሲል የተናገረው ክርስቶስ እንዴት ይመለከተን ይሆን። ለነገሩ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የምናደርግ ቢሆን ወንድማችንን ማሰቡ አይሳነንም ነበር።

*በርግጥ ይህኛው ወንድምህን መንገድ ላይ ስታገኘው አትጠመጠምበት ይሆናል!

*ስሙን አሳምረህ መጥራቱ ቀርቶ ጭራሹን ላታውቀው ትችላለህ!

*እሱም ወንድሜ ብሎ አይጠራህ ሰላምታ ብትሰጠውም አይመልስልህ ይሆናል!

ግን ይሄ ሁሉ ቢሆን ይህኛው ወንድምነት ስጋዊ ሳይሆን መንፈሳዊ ነውና ከአንድ አባት ከአንድ እናት እንደተወለዱ ልጆች ቢያንስ ቢያንስ እንኳን በጸሎት እንዳታስበው ሊያደርግህ አይገባም።

ወንድሜ! ምን መሰለህ የረሳነው "አይሁድ ብንኾን የግሪክ ሰዎችም ብንኾን ባሪያዎችም ብንኾን ጨዋዎችም ብንኾን እኛ ዅላችን ባንድ መንፈስ አንድ አካል እንድንኾን ተጠምቀናልና ዅላችንም አንዱን መንፈስ ጠጥተናልና" 1ኛ ቆሮ 12፥13 ሲል ሐዋርያው ጳውሎስ የነገረንን ኃያል ቃል ነው። አይሁድና ግሪክ ብዙ ልዩነቶች አሉባቸው ባርያዎችም ከጨዋዎች ጋር እንደ ሰው ሰውኛው አብረው አይቀመጡን ይሆናል። ግን ከወንድምነትም አልፈው አንድ አካል የተለያዩ ብልቶች ናቸው።

አንድ አካል መሆናችን "እንደ...." ተብሎ የቀረበ አይደለም። ይልቁና ማስረጃው አድርጎ ሁላችንም የአንዱ ክርስቶስ አካል መሆናችንን የሚጠቅስ ነው። አየህ ወንድምዓለም! አንተ ያ ልብሱ ያደፈው ችግር ያቆሳቆለው ግን በመንፈሱ አምላክ ጋር የተጣመረው በምግባሩ ክርስቶስን የገለጸውን ወንድምህን ወንድምነት መቀበል ሲይቅተህ ራስህን ከክርስቶስ አካልነት ለማራቅ እየሞከርክ ነው።

እዚያ ጋር ወንድምህ ሲራብ እጅህን የተመታህ ያህል የሚሰማህ ቢሆን ኖሮ ፣ እዚያ ጋር ወንድም በህመም ሲሰቃይ ውስጥህ ሰላም አልሰጥ ቢልህና የወንድምህን ችግር ብትረዳው የታመምከው እገሌ የሚባለው የወንድምህን ህመም ሳይሆን ላንተ የሞተው የክርስቶስን ህመም እንደሆነ ታስብ ነበር።

አባታችን እኛን ለማስተሳሰር በቅድሚያ ሳይለያየን ለሁላችንም የአባትነት ዋጋ እቃ ገዝቶ ሳይሆን ራሱ ተሽጦ ምድራዊ ምግብና መጠጥ ሳይሆን ዘለዓለማዊ መብልና መጠት አብልቶ አባታዊ ውለታውን ከማንም አባት የበለጠ አድርጎ ከፈለለን። ከዚያም የርሱን ውለታ ደግሞ እንከፍል ዘንድ ስንነሳ "ወንድማችሁን እንደእናንተ ዋጋ የከፈልኩለት ልጄን አግዙት" አለን። ህመሙን ታማችሁ ጠይቁት፣ ውሃ ጥማቱን ውሃ ሆናችሁ አርኩለት ፣ ለረሃቡ ምግብ ሁኑለትና ይመገባችሁ ፣ ርቃኑን ልብስ ሆንችሁ ሸፍኑ ፣ እንግዳ ሆኖ ቢመጣ ቤታችሁ ቤቱ ይሁን ፣ ቢታሰር ተስፋን በእናንተ ያግኝ ሲል አንድነታችንን የሚያጸና አባታዊ መመሪያ ሰጠን። ይህንን መመሪያውንም " ከወንድሞችህ የምታደርገው ለእኔ አደረግኸው ለወንድምህ ይላደረግኸው ለእኔ አላደረግኸውም" ሲል አጠናክሮ እርስ በርስ አስተሳሰረን። እኛ ግን ይህንን አለማድረጋችን ሳያንስ ወንድም እንዳለንም ማስታወስ ካቆምን ቆይተናል።

በሉ እንነሳ ወንድማችንን እንዴት ነህ እንበለው!

ዲያቆን ዳዊት ናሁሠናይ (ዘብሥራት)
ህዳር 8 2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ

👇👇👇👇
👉 @zebisrat👈
👆👆👆👆
በቁጥጥር ስር ውሏል

ሃገራችን ላይ ባለው ጦርነት ምክንያት ከሁለቱም ወገን የምንጠብቀው አንድ ዜና አለ። ይህንን ዜና ፍለጋ ጋዜጠኞች ያሉትን እናደምጣለን አይናችንን በማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ላይ እናደርጋለን።

ይኸውም ዜና "..... ከተማ በመከላከያ/ህዋሃት ቁጥጥር ስር ውሏል የሚል ነው። በአሁኑ ሰአት ጠላት ያደረግናው የትናንትናው መንግስታችን አንድ ከተማን ሲቆጣጠር በይበልጥ አዲስ አበባ የምንገኝ ሰዎች በመቀጠል የምናደርገው ድርጊት አለ።

ይሄኛው ተግባራችን ደግሞ አዲስ አበባ ሊገባ ምን ይህል ቀረው የሚለው ነው። ከኢንተርኔት አማራጮች አሊያም መረጃውን ካቀበሉን ሰዎች አዲስ አበባ ለመድረስ ምን ምን ከተማን ማለፍ እንደሚጠበቅብን እናደርጋለን።

ከመንግስት በተሰጠው መመሪያ መሰረት በአሁኑ ወቅት ሃገራችን በአስቸኩይ ጊዜ አዋጅ እየተመራች ትገኝለች። ይህ ቅድመ ጥንቃቄም ብዙ ሴራዎችን ሊያከሽፍ እንደሚችልም ታምኖበታል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ እስቲ ራስዎን የሚጠይቁት አንድ ጥያቄ ላጋራዎት። "የትኛው የሰውነቴ ክፍል በኃጢአት/በሞት ቁጥጥር ስር ውሏል?" ዛሬ ላይ ይሄን ጥያቄ መጠየቅ አለብን። የትኛው የሰውነታችን ብልት ነው ለኃጢአት ተገዢ ሆኖ በጠላት ቁጥጥር ስር የዋለው? አንደበታችን ይሆንን የማይረባ ነገር የስድብን ቃል የሚናገረው? ህሊናችን ይሆን ለኃጢአት ሃሳብ አሳልፎ የሚሰጠን? የቱ የሰውነታችን ክፍል ነው ኃጢአት ለመስራት የተጣደፈው?


በእግዚአብሔር ቁጥጥር ስር የዋለው የሰውነታችን ክፍል አለ? ካለስ የትኛው ክፍል ነው? ለጽድቅ ታምኖ መልካም ምግባርን ለመጸፈም የሚተጋ ለራሳችን ታማኝ የሆነው የሰውነታችን ክፍል ይሆን?

የሰው ልጅ በህመምም ይሁን በአደጋ አሊያም በድንገት የደም ዝውውሩ/የልብ ምቱ ሲቋረጥ ህይወቱ ያልፋል። በመንፈሳዊ አይን ደግሞ የደም ዝውውርም ሆነ ልብ ምቱ ሳይቆም መላ ሰውነቱ በኃጢአት ቁጥጥር ስር ሲውል ሞቷል ማለት ይቻላል።

እኔ አልታመምኩም የሚል ቼክ ለማድረግ ፣ የታመመው መድሃኒት ለማግኘት ፣ ሰውነቱ በጠላት ቁጥጥር ስር ውሎ የሞተው ደግሞ ከሞት ለመነሳት ወደሚችልበት መምህረ ንስሓ/ ንስሓ አባታችን ጋር እንዝመትና ሰውነታችንን ከጠላት ቁጥጥር ወደ ራሳችን እንመልሰው እግዚአብሔር ይነግስብን ዘንድ እንፍቀድ።

ዲያቆን ዳዊት ናሁሠናይ (ዘብሥራት)
ህዳር 11 2014 ዓ.ም
ወለቴ

👇👇👇👇
👉 @zebisrat👈
👆👆👆👆
ስንት ሰው ገደልክ?

ባላወቁት ጉዳይ ባልተሳተፉበት ተግባር ምክንያት የሞቱትን ነፍስ ፈጣሪ በክብር ይኑረው።

በቁም ሞተው ፥ "የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም" በሚሉት ብሂል የነፍስን ሞት ያልፈሩ ገድሎአደሮች ፤ እጃቸውን በሰው ደም ታጥበው ከስብዕና ከነጹ በኋላ ለሚኖሩለት ስጋ መደንደን ሲሉ በላቡ ደረቅ መሬትን አርሶ አለምልሞ ጥሬ ለገበያ የሚያበቃውን ገበሬ ፣ እሳት ጋር ታግላ እንጀራ የምትጋግረውን እናት ገድለው የእጃቸውን ፍሬ እየበሉ ነው።

በዚህ መሃል አንዱ ገድሎአደር "ስንት ሰው ገደልክ?" የሚል ጥያቄውን ወደ ሌላኛው ገድሎአደር ወረወረ። ጥያቄውን የሰማው ገድሎአደር መመገቡን አቁሞ መሳርያውን እየወለ የገደለውን ሰው ቁጥር ተናገረ። ጠያቂው ገድሎአደር በንቀት አይኑ እየተመለከተው "የገደልከው ሰው ትንሽ ነው" ብሎ ወቀሰው። ገድሎ አደሩ እንዲያማ ካልከኝ አለና የገደለው ሰው ቁጥር እንዲበዛለት ወደ ተለመደ ገድሎአደርነቱ ሄደ።

ለነገሩ ልክ ነው ገድሎአደር አይደል! ለወሬውም በመቶ የሚቆጠር ሰው ሲገድል ይሻለዋል። ሲናገርም አፉ ላይ ሞላ ያለ ይሆናል። ጀማሪ ገዳይ ይመስል የምን ትንሽ ሰው መግደል ነው ከገደሉ አይቀር ገድሎአደርነትን በሚያሳይ መልኩ በዛ አደርጎ ነው እንጂ...

ብዙ ሰው የመግደል ጉዳይ በአንድ ወቅት አንድ ታላቅ ንጉስና አንድ ታናሽ ብላቴናን አጣልቶ ለመጋደል አድርሷቸው ነበር። ንጉሱ ሳውል እና ታናሹ ብላቴና ዳዊት "ሳውል መቶ ገደለ ዳዊት እልፍ ገደለ" በሚል ሙገሳ ተነሳስተው "እንዴት እሱ ከኔ በላይ ይገድላል?" ቅንዓት እርስ በርስ ሰይፍ ተማዘዋል።

የእነርሱን እንተወውና የዘመናችንን ገድሎአደሮች እናስባቸው እስቲ! እንዴት ነው ግን ሰው እንደዚህ የተጨካከነው? ምንም እንኳን ገድሎአደር ቢሆንም ስራንም በአግባቡ መወጣት እኮ መልካም ነው። እንስሳ እንኳን ሲገደል ላለማሰቃየት ይሞከራል እኮ! ይሄ ሁሉ ክፋት ምን ያደርጋል?!

ግን እኛንስ ማን እነርሱ ላይ ፈራጅ አደረገን! እነሱስ አንደኛውን ገድሎ አደር ሆነው ከአምላካቸው የሚሰጣቸውን ፍርድ ይቀበላሉ። እኛ ስንቱን ሰው ነው በነፍስ የገደልነው?

ወዳጄ አትደናገጥ መልሼ ልጠይቅህ
እኔና አንተስ ስንት ሰው ገደልን?
ለስንቱ ሰው ሞት ጥይት የሆነ መግደያ መሳርያን በማህበራዊ ሚዲያ እና በሌላ አማራጭ ላይ አቀረብን?
ስንቱ ሰው በኛ ድርጊት ተሰናክሎ ሞተ?

መቼም "አትግደል" የሚለው የፈጣሪ ትዕዛዝ ትርጉሙ ስጋን መግደል ብቻ እንዳልሆነ "ስጋን የሚገድሉትን አትፍሩ ነፍስን የሚገድሉት ፍሩ" ሲል ፈጣሪ በተናገረው ቃል በግልጽ አስረድቶናል።

በስጋ መግደሉ እኮ ቀስ በቀስ እያደገ የሚመጣ የገድሎአደርነት ብቃት ነው። እኔ እና እናንተ ዛሬ ላይ ገድሎአደር ለመሆን እንችል ዘንድ ራሳችንን ከጸልዮአደርነት ፣ ከአመስግኖ አደርነት ፣ ከአስቀድሶ አደርነት ፣ ከአንብቦ አደርነት. .... አውጥተን ወደ ገድሎ አደርነት ለማደግ እየሞከርን ነው። ለዚህም ነው መሰል እውነታውን የገድሎአደርነት ጉብዝና ከመረጃ እና ከፊልም (የውሸት ነው እያልን) ስናጠናው የምንውለው!

አዎን ገድሎ አደርነት ብቃት ነው ነገ "ይህን ያህል ሰው ገደልኩ" ብለን በኩራት እንድንነጋገር ዛሬ ላይ ብዙ ጥሩአደርነቶችን ትተን ገድሎአደርነትን መለማመድ አለብን። እኛ ግን ይበልጥ ልንፈራ የሚገባን ስጋን ሳይሆን ነፍስን የምንገድል ገድሎ አደሮች ነን። ዛሬ ላይ ሞት የማይቀርላት ስጋን የገደሉትን ሰዎች እየኮነንን ነፍስን የምንገድል ራሳችንን ማመጻደቃችን "በአይንህ ያለውን ግንድ ሳታወጣ በወንድምህ አይን ላይ ያለው ጉድፍ እንዴት ሊታይህ ይችላል" ያስብላል።

ጠላት ዲያቢሎስም ራሳችን የገደልናቸውን ሰዎች ደም ከእጃችን በንስሃ እንዳናስለቅቅ በማሰብ ዘወትር ሰው የገደለው ላይ እንድናተኩር አድርጎናል። በሌሎች ገድሎ አደሮች ላይ መፍረዳችንን ትተን እያንዳንዷን ቀን ውለን ከማደራችን በፊት ምን እንደምናደርግ እናስተውል! ውሏችንን በአግባቡ እንፈትሽ። በስተመጨረሻ ከገድሎ አደሮች ጋር ከመሰለፍ እንድን ዘንድ ዛሬ ላይ አዋዋላችንን አኗኗራችንን ከጽድቅ ሰርቶ አደሮች ጋር ፣ ከእውነትን መስክሮ አደሮች ጋር.... እናድርግ። ሰው ነንና ደግሞ ለስጋችንም ለነፍሳችንም መብል የሆነ የጌታችንን ክቡር ስጋና ቅዱስ ደም ከመቀበል ወደ ኋላ አንበል። እንዴት ሳይበላ ይኖራል! ያውም በኛ ስንፍና!

ለማንኛውም እስካሁን "ስንት ሰው ገደልክ?" "ስንት ሰው ገደልሽ?" "ስንት ሰው ገደልኩ?" በሉ ተነሱ ቶሎ ንስሃ እንግባ።

ዲያቆን ዳዊት ናሁሠናይ (ዘብሥራት)
ሐምሌ 2014 ዓ.ም
ወለቴ

👇👇👇👇
👉 @zebisrat👈
👆👆👆👆
ወዳጄ ለፍቅር ጓደኛህ እና ላንተ ትልቅ ስጦታ ማበርከት ታስባለህ?

እህቴ ለወደፊት ትዳር አጋርሽና ላንቺ ትልቅ ስጦታ ለመስጠት ትፈልጊያለሽ?

በፍቅር ቆይታ ብዙ ስጦታዎች እርስ በርስ መሰጣጣት ፣ አብሮ አስደሳች የፍቅር ጊዜያትን ማሳለፍ የተለመደ ትክክለኛም ተግባር ነው።

በፍቅር ቆይቶ ወደ ትዳር መሸጋገር ከዚያም ደግሞ የአንድነት ውጤት ልጅ መውለድ የብዙዎቻችን ምኞት እንደሆነ አይካድም።

በጣም የሚገርመኝ ለዚህ ፍላጎታችን ትልቅ ዋጋ ያለውን እጅግ ታላቅ ስጦታ ዘንግተነዋል።

ከእግዚአብሔር የሚሰጥ አንድነት

ከዚህ በላይ ምን አይነት ስጦታ ይኖር ይሆን?

በቅድሚያ ሔዋንን ለአዳም ፈጥሮ ትዳርን የጀመረ ፤ አዳም በሔዋን ላይ ቂም ይዞ ሊርቃት ባሰበ ወቅት "ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ" የሚል ቃልኪዳንን በመስጠት ዳግመኛ ወደ ሔዋን ሄዶ የትዳርን ሕይወት ወደ ቀደመ ክብሩ እንዲመለስ ያደረገን አምላክ በኛ ሕይወት ላይ ቦታ ሰጥተነዋል?

አላስተዋልነውም እንጂ ከፍቅር አልፎ ወደ ትዳር እንዲያድግ ለምንፈልገው ሕይወት ከምንም በላይ የሆነው ታላቁ ስጦታ ከፈጣሪ የተሰጠን ምስጢር ተክሊል (ቁርባን ለመዐስብን ወይም ደናግላን ላልሆኑ) ነው።

አንድ ለመሆን ለሚፈልጉ አንድ የመሆኛ መንገድ ይኸው ተክሊል (ቁርባን) ነው። የተለያዩ አካላትን ለማጣበቅ ብዙ ማጣበቂያ መንገዶች ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ ግን በእግዚአብሔር ፈቃድ በዚህ ምስጢር የሚደረገው መጣበቅ አይደለም። ፍፁም መዋሃድ ነው እንጂ!

በትዳር አብሮን ከሚኖር ሰው ጋር ከመዋሃድ የዘለለ ምን ማድረግ እንችል ይሆን? ግን ይሄን ዘንግተን በተለያዪ መንገዶች ለመጣበቅ እንሞክራለን። ያልተዋሃደ/የተጣበቀ ነገር ቢላቀቅ ብዙም አይገርምም። በክርስቶስ አንድ የሆነን ግን ማን ሊለየው ይችላል?

እግዚአብሔር ለኛ ካለው ፍቅር የተነሳ እርሱ ለኛ ያለውን ፍቅር ለፍቅር አጋራችን እንድንሰጥ ይፈልጋል። ይህንንም ደግሞ በታላቁ ምስጢር ያፀድልናል። ይህ ድርጊት ግን የአንድ ቀን ተግባር ብቻ እንዳልሆነ ልብ ይሏል!

አንዳንድ ጊዜ ተክሊል ልክ የሰርጋችን ቀን ቤተ ክርስቲያን ተገኝቶ ስርዐቱን መፈፀም ብቻ ይመስለናል። ልክ ይመስላል ግን ፈፅሞ ስህተት ነው። እግዚአብሔር እንዲኖረን የሚፈልገው የአንድነት ሕይወት እውነት የሚያደርገው በየጊዜው በምናደርገው የሕይወት ልምምድ ነው።

ብዙ እያወቅን ዕለት ዕለት የምናዳብረው በደስታ የምንኖረው እግዚአብሔር ተገኝቶ ያለቀውን ወይን ተመልክቶ ውሃ ወደ ወይን ቀይሮ የሚሞላው ሕይወት አለ።

ወዳጄ
እህቴ
ይሄን ስጦታ እንዴት መስጠት እንደምንችል ዕለት ዕለት ማሰብ አለብን። የፈጣሪን ትዕዛዝ እያከበሩ ፣ ከሚያፈቅሩት ሰው ጋር እየኖሩ ፣ በትንሿ ቤተ ክርስቲያን ኦርቶዶክሳዊ ልጆችን ወልዶ መኖር በዐለም ሳለን ልንፈፅመው የምንችለው ለምንወዳቸው ለሚወዱን ስንል የምንከፍለው ዋጋ ሊሆን ይገባል።

ስለዚህ ስጦታ የሚያብራሩ መፃህፍት ተፅፈዋል ፣ ትምህርቶች ተሰጥተዋል ፣ በርካቶች በዚህ በተቀደሰ መንገድ እየሄዱ ፈጣሪያቸውን አክብረውበታል ታሪካቸውም ትውልድን ተሻግሮ ለኛ ደርሷል። እውነት የፍቅር ጓደኛችንን ከልብ የምንወድ ከሆነ ይህንን ከስጦታ የሚበልጥ ስጦታ ለመስጠት መትጋት ያለብን ይመስለኛል!

ዲያቆን ዳዊት ናሁሠናይ
ጥቅምት 14 2015 ዐ.ም
አራት ኪሎ


👇👇👇👇
👉 @zebisrat👈
👆👆👆👆
እረኛ ካህን

ይገርምሃል እኛ የእግዚአብሔር በጎች ነን (ፍየል አለመሆናችንን እንኳን እርግጠኛ አይደለሁም) የምንበላውን የምንበላበትን ቦታ የማናውቅ በጎች ፣ ጠላት በፈለገ ጊዜ አርዶ አወራርዶ ለክፋት ተግባር የሚያውለን በጎች ፤ ለዚያም ነው እግዚአብሔር ያለ እረኛ በዚህ አለም ላይ ሊተወን ያልፈቀደው።

የእኛ በግነት በእድለኝነት ነው። ምክንያቱም በርካታ በጎ እረኛዎች አሉንና። ነገር ግን ይህን እድለኛነታችንን አገናዝበን በአለም ውስጥ ያለ ምክንያት ከመቅበዝበዝ የዳነው ስንቶቻችን እንሆን?!

የኛን በግነት እንያዘውና ስለ እረኞቻችን እናውጋችሁ። እኒህ እረኞቻችን ስለ እኛ እጅግ ብዙ ዋጋ ይከፍላሉ። ለነገሩ ዕለት ዕለት ታላቅ እረኛ የሆነ የዳዊት መዝሙር እየደገሙ እንዴት ዋጋ የማይከፍል እረኛ መሆን ይቻላል።

እረኞቻችን እኛን ለመመገብ ዘወትር የጌታችንን ስጋና ደም ይዘው በቅዳሴ ይሰየማሉ ፣ ነፍሳችንን ንፁህ ለማድረግ ለማሰብ የከበደ ኃጢአታችንን እያራገፍንባቸው እነሱ ግን ለኛ ድህነት ይፀልያሉ ለድህነታችንን የሚጠቅመንን ነገር ይነግሩናል ፣ እኛ ለራሳችን የተወሰነች ደቂቃ በጸሎት መቆም ተስኖን ሳለ እነሱ ግን እኛ በምንተኛበት ለሊት ክርስትና ስማችንን እየጠሩ ይጸልዩልናል ፣ በህመም ውስጥ ሆነው እንኳን ከስጋ በሽታ የነፍስ በሽታ ይከፋልና የኛን የነፍስ በሽታ ለማከም ይጥራሉ ፣ . . . .

ካህናት የነፍስ እረኛ ናቸው። በግ ያለ እረኛ ሲሄድ አውሬ እንደሚበላው ሁሉ እኛም ያለ ካህናት እርዳታ ስንሄድ የአውሬ ምግብ መሆናችን አይቀርም። ለዛ ነው አውሬው ቅድሚያ ልብላችሁ ከሚለን ይልቅ ከካህናት ጋር የሚያጣላን። ከካህናት ጋር ተጣልተን ያለ እረኛ ስንቀር ያኔ እኛን መብላት ቀላል ነው።

እኛ ያለ ካህናት ስንሄድ የአውሬው ምግብ ከመሆናችንም በላይ በረሃብ እንሞታለን። ነፍሳችን ምግቧ የእግዚአብሔር ቃል ብሎም ስጋ ወደሙ ነው። ያለ ካህን ደግሞ የጌታን ስጋና ደም ማግኘት አይቻለንም። አሁን እኮ ስጋችንን ሸፍኗት ነው እንጂ ነፍሳችን ብትታይ በታሪክ በ77 ድርቅ ተብሎ እንደሚታዩ ሰዎች የሚታዘንልን በረሃብ ውስጥ ያለን ምስኪኖች ነን።

ታዲያ ወዳጄ አሁን ተነስ አትዘግይ እረኛህን ፈልጋቸው። ከስራቸው ቁጭ ብለህ ያለ እረኛ የኖርክባቸውን ቀናቶች አስታውሰህ መሳሳተህን ንገራቸው። አይዞህ እንደ ዘመናችን ፍርድ ስፍራ ጥፋትህን ብታምንም ቅጣት አይቀርልህም አይሉህም ይልቁኑ አይዞህ ልጄ ብለው ያፅናኑሃል። እርግጥ በሚያዝን ልባቸው አስታውሰው የተወሰነ ስግደት የተወሰን ምፅዋት የፆም ቀንም ይሰጡህ ይሆናል። ግን እኮ ይሄ ሁሌ ማድረግ ያለብን ነገር ነበር ያው በዚህ ምክንያት ቀስ በቀስ መንፈሳዊነቱን ይለምድ ይሆናል ብለው እንደሆነ አትዘንጋ።

ለማንኛውም የብዙዎች እረኛ የሆኑ አባቶቼ እነሆ
#መምህር #ቀሲስ ናሁሠናይ ተሾመ
ነፍሰ ሄር #ቄሰ ገበዝ ሠርገወርቅ ተሾመ እና
ክብርት ባለቤቱ ወ/ት አልጋነሽ ተሾመ

አንድ ቀን ደግሞ ስለ ካህናት ሚስቶች የመጣልኝን እፅፍ ይሆናል

ዲያቆን ዳዊት ናሁሠናይ
ጥቅምት 19 2015 ዐ.ም
ብስራተ ገብርኤል
ድንቅ በሆነ መንገድ የተሰናዳ ዐውደ ርዕይ ስለሆነ በብዙ ታተርፉበታላችሁ

ጎራ በሉ
የቤት ስራ ሲበዛ

በተለያዩ የክፍል ደረጃዎች በተማርንበት ዘመን እኒያ "ለኛ የቤት ስራ ከመስጠት ውጪ ስራ የሌላቸው" የሚመስለን መምህራን home work ብለው በነጩ ቾክ ጥቁሩ ሰሌዳ ላይ የሚሞነጭሩት የቤት ስራ አሰልቺ ነበር።

ታዲያ ከትምህርት ቤት ውሎ ተመልሰን ጨዋታ እንደጀመርን ሰአቱ እንዴት እንደሄደ ሳናቅ ጨለምለም ሲል በወላጆቻችን ጥሪ ወደቤት እንገባና ተጣጥበን ቦርሳችንን አውጥተን የቤት ስራ ጋር እንፋጠጣለን።

አንዳንድ ጊዜ የተለያዩ መምህራን የቤት ስራ ሰጥተውን የቤት ስራውን መስራት ከመጀመራችን በፊት ያለንን የቤት ስራ ብዛት ስናረጋግጥ የቤት ስራው ይበዛና ተስፋ በመቁረጥ አንድ አማራጭ እንጠቀማለን። ኹሉንም የቤት ስራ አለመስራት

ወይ ልጅነት! ለማይቀር የቤት ስራ ኹሉንም አለመስራት መፍትሔ ሆኖ ለብዙ ጊዜ አገልግሎናል። ከዚያም ደግሞ አንግ የተለመደች ጸሎታችንን እናደርሳለን። የጸሎታችን ጽንሰ ሃሳብ መምህሩ ወይ ቀርቶ ወይ በሌላ መንገድ ብቻ የቤት ስራ መስራት አለመስራታችንን እንዳያረጋግጥ የሚቀርብ ልመና ነበር።

ልጅነት የዋህ ነውና ስንፍናችንን በመምህራችን ክፍተት ለመሸፈን የምናቀርበው ጸሎት አለመሳመቱም ያናደደን ጊዜ በርከት ያለ ነው።

የሚገርመው ነገር አመታት አልፈው ጊዜያት ተቆጥረው ይሄንን ነገር ለመተው አለመቻላችን ነው። ይህ ባህሪ የጋራ ሆኖ እንደ ሃገር ያሉብን የቤት ስራዎች ከመብዛታቸው የተነሳ ኹሉንም እየሰራን አይደለም! እንደ ግለሰብ ለመንፈሳዊ ሕይወታችንም ሆነ በምድር ለሚኖረን ቆይታ መስራት ያለብንን ብዙ የቤት ስራ እየሰራን አይደለም! እንደ አንድ ክርስቲያን ለቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን መስራት ያለብንን በርካታ የቤት ስራ ላለመስራት ኹሉንም አጣጥፈን አስቀምጠን ባተሌ ሆነናል!

የበዛ የቤት ስራ ቢኖርም የሚሰራ የቤት ስራ ግን የለም። ትልቅ ተቃርኖ! የቤት ስራውን ባለመስራታችን ለሚመጣው ችግር ደግሞ ተጠያቂ ልናደርግ የምንችለውን ሰው እንፈልጋለን።....

እስቲ ያሉንን የቤት ስራ እናስታውሳቸው እንደ ሃገር እንደ ቤተ ክርስቲያን እንደ ግል... ብዙ ናቸው።

እንደው መስራቱ እንኳን ቢቀር አንዳንድ ቅዱሳንን ጀግኖችን ስናከብር የቤት ስራቸውን ከሚገባው በላይ ሰርተው ያለፉ እንደሆኑ አንዘንጋ። ክፍሉ ውስጥ የቤት ስራውን በአግባቡ የሰራ ሰው እንደሚጨበጨብለት በሕይወት ጎዳና የቤት ስራቸውን ለሰሩ ሰዎች ጭብጨባ ከማቅረብ አንድከም።

ምናልባት አንድ ቀን ለጭብጨባ የሚጣደፉ እጆቻችን የራሳችንን የቤት ስራ ለመስራት ተግተው ሌሎችን ማስጨብጨብ ይቻላቸዋል።

ዲያቆን ዳዊት ናሁሠናይ (ዘብስራት)
ሐምሌ 7 2015 ዓ.ም
4 ኪሎ


@zebisrat
አንዳንድ በደሎች

አንዳንድ ጊዜ ውስጣችንን እንደ ብረት ዝገት የቀየሩ ፣ ማንነታችንን እንደተበከለ ውሃ ያሳደፉ በደሎች ተፈጽመውብናል። እህ ብሎ የሚሰማን ካገኘን ዕለት ዕለት ደጋግመን ብንናገራቸው አይወጣልንም....

የበደሉን ሰዎች እግራችን ድረስ ዝቅ ብለው ይቅርታ ቢጠይቁንም ለተጎዳው የልቦናችን በረሃ የውሃ ጠብታ ያህል እንኳን ጥቅም አልነበራቸውም ....

ለአመታት ተሸክመናቸው ያጎበጡን አልፎም በሽታ ላይ የጣሉን በዙሪያችን ላይ ያሉ ሰዎች ሊረዱት ያልቻሉት እኒያ በደሎች....

ደካማው መንፈሳዊ ሕይወታችን በፊታቸው ቆሞ ሊረታቸው የማይችላቸው ፣ ለደነደነ ልባችን የተሻለ ጥንካሬን ሰጥተው ልባችንን ያጸኑ በደሎች...

ለተበደለው ሰው ይቅርታ ብናደርግለትም ፣ ዕለት ዕለት ይቅር ማለታችንን የሚገልጽ ጸሎት ብንጸልይም ፤ ባሰብነው ቁጥር ያልዳነ የውስጣችንን ቁስል እየሸነቆረ ህመማችንን የሚያብስ ፣ ልናስበው ባንፈልግም ልንረሳው ያልቻልነው ያ በደል....

ከብዙ በደሎች ልቆ እንደ ተራራ ግዘፍ ነስቶ በህሊናችን መልክዓ ምድር ላይ ሰፊውን ቦታ የያዘ ታልቅ በደል....

ከብዙ ንግግር አዋቂዎች በሚወጣ ምክር ሊናድ ያልቻለ ፣ በጠንካራ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት ተነቅንቆ ያልፈረሰ ዘመናትን በማሳለፉ ከቶ የማያረጅ በደል.....

ከብዙዎች ጋር የነበረንን ፍቅር ያደፈረሰ ፣ ከወዳጆቻችን ጋር የነበረንን አንድነት ዳግም እንዳይቀጥል አድርጎ የጎመደ በደል....

በኛ ልክ የተጎዳ እንደሌለ አስመስሎ ያሳየን ፣ የተገፋን ሰዎች ለመሆናችን ማስረጃ አድርገን ልናቀርበው የምንችል በደል.....

!!! ሲገርም !!!
እሱን በደል ፈጣሪያችን ላይ ፈጽመነው ምሮናል ፣ ከኛ በደል በከፋ ሁኔታ አምላካችን ላይ ግፍ ፈጽመን በአንዲት ንስሃ እንደ ቸርነቱ ይቅር ብሎናል ፤ ይቅርታ እስክንጠይቀው ድረስ እንኳን ፍቅሩን አልቀነሰም ነበር!!!

!!! ደግሞም ከዛ በላይ !!!
እኛ የሰውን በደል ሳንረሳ ከዚያ ለማሰብ ከከበደው በደል የሚበልጥ ጥፋት ከመስራት ዛሬም አልተቆጠብንም!!!

#አምላካችን_ሆይ_እንደ_ቸርነትህ_ማረን!!! እንጂ እንደ ኹሉን አዋቂነትህ አትመራመረን። ከተመራመርከን አንተ ደጋግመህ ከማርከን በደሎቻችን የሚያንሱ የበርካታ ሰዎች በደል በልቦናችን ሰፊውን ቦታ ይዘው ተቀምጠዋል። አንተ ይቅርታችንን ሰምተህ ብትምረንም በኛ በበዳዮቹ ህሊና በደማቁ የተሳሉ በደሎች እያንጸባረቁ ነው። እኒያን ከመዘንክ ምህረትህ አይደረስንምና እንደ ቸርነትህ በደላችንን ሳትመለከት ማረን!!!!

ዲያቆን ዳዊት ናሁሠናይ (ዘብስራት)
ለመስከረም 7 ለሊት
በቅርቡ በልዩ ገቢ ማሰባሰቢያ ስራውን እንጀምራለን እስከዚያም ማህበራዊ ሚዲያ ገጾችን በመከተል ይጠብቁን
HTML Embed Code:
2024/04/25 03:16:56
Back to Top