TG Telegram Group Link
Channel: Addis Ababa Education Bureau
Back to Bottom
በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ በተካሄደ አስተዳደራዊ ሱፕርቪዥን የመልካም አስተዳደራዊ ግኝቶች ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡

(ሚያዝያ 8/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ 328 አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ በተደረገ አስተዳደራዊ ሱፕርቪዥን የመልካም አስተዳደራዊ ግኝቶች ላይ ውይይት አካሄዳል፡፡

በውይይቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስትራቴጂክ ካውንስል አባላት ፣ የክፍል ከተማ ት/ጽ/ቤት ሀላፊዎች እና ጉዳዩ የሚመለከታቸዉ አካላት የተገኙ ሲሆን በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ የተካሄደ አስተዳደራዊ ሱፕርቪዥን የመልካም አስተዳደራዊ ግኝቶች ሰነድ በቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ በአቶ አሊ ከማል ቀርቦ ውይይት ተካሄዳል፡፡

በውይይቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ የተካሄደው አስተዳደራዊ ሱፕርቪዥን ያገኛቸው የመልካም አስተዳደራዊ ክፍተቶች እንዲታረሙ ሁሉም ወስዶ እንዲሰራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡


መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
ዛሬ የትንሳዔ በዓልን ምክንያት በማድረግ በሁሉም ክፍለ ከተሞች እና ወረዳዎች 200 ሺህ ለሚሆኑ የኑሮ ጫና ላለባቸውና ለተለያዩ ማህበራዊ ችግር ለተጋለጡ የኅብረተሰብ ክፍሎች ማዕድ አጋርተናል።

ማዕድ ማጋራት ለነዋሪዎቻችን ፍቅራችንን እና አክብሮታችንን የምንገልፅበት እዲሁም እርስበርስ መተሳሰብን የምናዳብርበት የሰዉ ተኮር እሳቤያችን ተግባራዊ ማሳያ ነዉ።

እንደ ሁልጊዜው ሁሉ ዛሬም ‘መስጠት አያጎድልም’ ብለው ከጎናችን የቆሙ የከተማችን ባለሃብቶችን፣ ተቋማትን እና ወጣት በጐ ፍቃደኞችን በራሴ እና በነዋሪዎቻችን ስም ከልብ ላመሰግናቸው እወዳለሁ።

መልካም በዓል !
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የትምህርት ግብዓት ፍላጎት አቅርቦትና ስርጭት ዳይሬክቶሬት የ9ወር እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ አካሄደ::

(ሚያዝያ 8/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት ግብዓት ፍላጎት አቅርቦትና ስርጭት ዳይሬክቶሬት የ9ወር እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ አካሂዷል::

የትምህርት ግብዓት ፍላጎት አቅርቦትና ስርጭት ዳይሬክተር ወ/ሮ ምስራቅ ብርሀነመስቀል የ9 ወር እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት እንዳሉት በዘጠኝ ወራት ከቁልፍና አበይት ተግባራት አንፃር በርካታ ሥራዎች መከናወናቸውን ገልፀዋል ፤ በመንግስት ቅድመ አንደኛ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የመማሪያ ቁሳቁስ ፣ የደንብ ልብስና የመማሪያ መፅሐፍ ስርጭትን ጨምሮ የምገባ ስርዓትን ተግባራዊነት በክትትልና ድጋፍ በመታገዝ በርካታ ሥራዎች መሰራታቸውን ያብራሩት ዳይሬክተሯ በቀሪ ወራት ሥራዎችን ከግብ ለማድረስ የቀደሙ ሥራዎችን መገምገም አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል:: አያይዘውም የቀሪ ወራት የስራ አቅጣጫም አስቀምጠዋል ::

በተያያዘም ከስርአተ ትምህርት ለውጥ በኃላ የተከናወኑ የመፅሐፍ ህትመትና ስርጭት ሪፖርት የግብዓት አቅርቦት ከፍተኛ ባለሙያ በሆኑት በአቶ አሸናፊ ደጀኔ ቀርቦ በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ ውይይት ተደርጎበታል::

በውይይቱ የስራ ክፍሉ ባለሞያዎችና የቢሮው የሁለቱ ስርዓተ ትምህርት ሱፐርቫይዘሮች እንዲሁም የክፍለ ከተማ የትምህርት ቤት መሻሻል ፣ የልዩ ፍላጎትና ዘርፈ ብዙ ቡድን መሪዎችና የግብዓት ባለሙያዎች ተሳትፈዋል::

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል ግንቦት 23 እና 24 የትምህርት ቤቶች ፌስቲቫል (school festival) እንደሚካሄድ ተገለጸ።

(ሚያዝያ 8/2017 ዓ.ም) ቬስቲቫሉ ትምህርት ቤቶች ራሳቸውን እንዲያስተዋውቁ እና እርስ በእርስ ልምድ እንዲለዋወጡ የሚያስችል መርሀግብር መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፌስቲቫሉን በአጋርነት ከሚያዘጋጀው ቅሩንፉድ ዲጂታልስ ከተሰኘው ድርጅት ጋር በጋራ በመሆን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዲናኦል ጫላ በፌስቲቫሉ በከተማ አስተዳደሩ ከሚገኙ 1,500 በላይ ትምህርት ቤቶች መካከል የተመረጡ 500 ተቋማት እንደሚሳተፉ ጠቁመው መርሀግብሩ ትምህርት ቤቶች ራሳቸውን ለህብረተሰቡ በአግባቡ የሚያስተዋውቁበት እና ልምድ የሚለዋወጡበት እንደመሆኑ ቢሮው የቅርብ ክትትል የሚያደርግ መሆኑን አመላክተዋል።

በፌስቲቫሉ የመንግስት ከግል እንዲሁም አለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች እንደሚሳተፉ የቅሩንፉድ ዲጂታልስ ስራ አስካሄጅ አቶ መቅድም ደረጀ ጠቁመው በፌስቲቫሉ ከትምህርት ቤቶች ባሻገር በትምህርት ዘርፉ የተለያዩ ተግባራትን የሚያከናውኑ ተቋማት የሚሳተፉ መሆኑን በመግለጽ በመርሀ ግብሩ ታላቁ አትሌት ሻለቃ ሀይሌ ገብረስላሴን ጨምሮ የተለያዩ ተጽኖ ፈጣሪ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎችን የሚያበረታቱበት ፕሮግራም መዘጋጀቱን አስታውቀዋል።
በተያያዘ የትምህርት ፌስቲቫሉ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ እና በትምህርትና ስልጠና ቁጥጥር ባለስልጣን ዕውቅና የሚካሄድ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ኡመር መርሀግብሩን አስመልክቶ ከግል ትምህርት ቤት ባለቤቶች ጋር በተካሄደ ውይይት ገልጸው ፌስቲቫሉ ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደመካሄዱ ትምህርት ቤቶች ራሳቸውን ለህብረተሰቡ በአግባቡ የማስተዋወቅ አጋጣሚውን መጠቀም እንደሚገባቸው አስገንዝዋል።

ተማሪዎች ፌስቲቫሉን ያለምንም ክፍያ በነጻ የሚታደሙ መሆኑን እና ወላጆች ለመግቢያ የሚከፍሉት 100 ብር ለሜቄዶንያ የአረጋውያን እና አእምሮ ህሙማን መርጃ በጎ አድራጎት ድርጅት ገቢ እንደሚደረግ በጋዜጣዊ መግለጫው ተገልጿል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
HTML Embed Code:
2025/04/16 12:05:09
Back to Top