TG Telegram Group Link
Channel: Wina Islamic post
Back to Bottom
Channel created
Channel photo updated
#እውነተኛ ታሪክ ነው!
{ ሼር በማድረግ ያዳርሱ
"እንቁላሉ ስንት ስንት ነው?" ስትል ጠየቀቻቸው…
"አንዱ እንቁላል 4 ብር ነው " ልጄ በማለት መለሱ፣ አበባ …
"አምስቱን እንቁላል በ10 ብር ልወሰደው?…" ስትል ደግማ
ጠየቀቻቸው …

"አይጎዳኝም ብለሽ ነው ልጄ?"…በማለት ደከም ባለ ድምፅ
መለሱላት… "ከፈለጉ ይሽጡ፣ ካልፈለጉ ግን በቃ መሄዴ ነው…" አለች ጠንከር ባለ ድምፅ… አበባ ትንሽ አሰቡና ቀና ብለው አይተዋት… "እስካሁን ምንም አልሸጥኩም ባያዋጣኝም እንደ መጀመሪያ ገድ ልቁጠረውና ልሽጥልሽ።

የፈለግሺውን ያህል እንቁላል በፈለግሺው ዋጋ ውሰጂ…" ሲሉ በደከመ ድምፅ ተናገሩ… ዘንቢሏን አውጥታ 5 እንቁላል መርጣ አስገባች፣ ከበርካታ 100 ብሮች መካከል ነጠላ 10 ብር አውጥታ ወርውራላቸው እየተጣደፈች የሚያምረው ዘመናዊ መኪናዋ ውስጥ ገባች… የአሸናፊነት ስሜት ተሰምቷታል…።

ከጓደኛዋ ጋር ወደ አንድ ዘመናዊ ሬስቶራንት ገብተው
የሚፈልጉትን አዘዙ…ትንሽ በልተው ብዙ አተረፉ ። ተዝናኑ ሂሳቡ ሲመጣ ቢሉ ላይ 1420 ብር ይላል ። ከቦርሳዋ ውስጥ 1500 ብር አውጥታ ሰጠች ። መልሱን ለሪስቶራንቱ ባለቤት ቲፕ እንዲሆነው ነግራው ወጥተው ሄዱ …

ይህ ድርጊት ለሬስቶራንቱ ባለቤት አዲስ አይደለም ለእንቁላል ሻጮ ግን አስደንጋጭና ልብ ሰባሪ ነው…

ከድሆችና ከምስኪኖች የምንፈልገውን ለማገኘት የበላይነታችንን ለማሳየት የምንጥረው ለምንድን ነው? የእኛን እርዳታ ለማይፈልጉትስ ቸር ሆነን ለመታየት ለምን
እንፈልጋለን ? #ለሚገባው እንስጥ ።

ለሌሎችም ሼር በማድረግ ያስተላልፉ ።
@Wina_islamic_post
The account of the user that owns this channel has been inactive for the last 1 month. If it remains inactive in the next 10 days, that account will self-destruct and this channel may no longer have an owner.
HTML Embed Code:
2024/04/19 19:49:01
Back to Top